በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
08/12/2004
አንባቢው እዚህ ላይ እንዲያስተዋልልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር በሐዲስ ኪዳን ክብር
ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ በመስቀሉ በፈጸመው የድኅነት ሥራ እኛ በጥምቀት ስንተባበርና የተሰጠንን የልጅነት ጸጋችንን ጠብቀን ስንገኝ የምንድን መሆናችንን ነው፡፡ ድኅነቱ አሁን ተሰጥቶናል፡፡ የመዳንና ያለመዳን ምርጫው የተያዘው በእኛው እጅ ነው፡፡ ስለዚህም አንዴ በተቋጨና በተደመደመ ጉዳይ ዙሪያ ነው የምንነጋገረው፡፡ በመሆኑም ይህን ጽሑፍ ሳቀርብም ለእውቀት ያህል ብቻ እንደሆነ አንባቢው እንዲረዳኝ በትሕትና እጠይቃለሁ፡፡
ነቢዩ ዳዊት ኃጢአት ከእናት ማኅፀን እንደሚጀመር ሲጽፍልን
“ኃጥአን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፤ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፤ ሐሰትንም ተናገሩ፡፡”ሲለን(መዝ.57፡3-4) ኢዮብ ደግሞ ሕፃናት ገና
ከማኅፀን ሳሉ ጽድቅን እንደሚጀምሩ ሲናገር “ደሃውን ከልመና ከልክዬ፣ የመበለቲቱን ዓይን አጨልሜ እንደሆነ፤ እንጀራዬን ለብቻዬ
በልቼ እንደ ሆነ፣ ደሃ አደጉም ደግሞ ከእርሱ ሳይበላ ቀርቶ እንደ ሆነ፤ እርሱን ግን ከታናሽነቱ ጀምሬ እንደ አባቱ ከእኔ ጋር
አሳድጌው ነበር፡፡ እርሱዋንም ከእናቴ መኅፀን ጀምሮ መራኋት”አለን፡፡(ኢዮ.31፡16-18)