Saturday, December 1, 2012

"እነኋት ክርስትና" አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ









በተግባራዊ ክርስትና ላይ የሶርያ ቅዱሳን አባቶችን አስተምህሮ የያዘችው "እንኋት ክርስትና" መጽሐፌ በአማዞን ላይ ለኦን ላይብ ግዢ ለአንባቢያን ቀርባለች ገዝተው አንብቧት በመንፈሳዊው ሕይወቶ ብዙ ይጠቀማሉ፡፡




በምዕራፍ አንድ ላይ የተቀነጨቡ

 ምሥጢረ ጥምቀትና ምሥጢረ ቁርባንን አስመልክቶ በሶርያ ቅዱሳን አባቶች በጥቂቱ


እነዚህ የሶርያ ቅዱሳን አባቶች ይህን ፅንሰ አሳብ በማዳበር ብዙ የጻፉ ሲሆኑ ባለራዕይው ዮሴፍ የተባለው ቅዱስ አንድ ክርስቲያን በውስጡ ላደረው መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሲታዘዝ በሰውነቱ የሚከሰቱ ለውጦችን ደረጃ በደረጃ ጽፎልን እናገኛለን ፡፡

……..“አንድ ክርስቲያን በሰውነቱ ውስጥ ያደረው መንፈስ ቅዱስ ሥራ መጀመሩን የሚረዳው  በልቡ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ እሳት መቀጣጠል ሲጀምር ነው፡፡ ይህ ክርስቲያን እግዚአብሔር ከፍቅሩ የተነሣ ዓለማትን እንደ ፈጠረ ወደ ማስተዋል ይመጣል፡፡ ከዚህም ስለእግዚአብሔር ፍቅር ሲባል ለእግዚአብሔር መለየትና የትህርምት ሕይወትን ወደ መምረጥ ይመጣል፡፡ እነዚህ ሁለቱ የመልካም ሥነምግባራት እናቶች ናቸው፡፡ ወንድሜ ሆይ ሁለተኛው መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ ሥራ መሥራቱን የምትገነዘበው እውነተኛ የሆነው ትሕትና በአንተ ሲወለድ ነው፡፡ እንዲህ ስልህ ለታይታይ በሥጋ የሚገለጠውን ትሕትና ማለቴ ግን አይደለም ፡፡ በእኛ ባደረው መንፈስ ቅዱስ ድንቅ የሆነ ሥራ እየተፈጸመ ነገር ግን ራሳችንን እንደትቢያና አመድ የተናቅን አድርገን የምንቆጥርና ከሰው ተርታ የማንመደብ አድርገን  የምንመለከት ከሆነ በእርግጥ እውነተኛይቱትሕትና በእኛ ውስጥ ተወልዳለች ፡፡ (መዝ.፳፩፥፮) ይህ ትሕትና ራስን በእግዚአብሔር ፊት በመመልከት የሚወለድ ትሕትና ነው፡፡