ትርጉም ዲ/ንሽመልስ መርጊያ
09/08/2004
ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ የተለቀቀ ጽሑፌ ቢሆንም ከጊዜው ጋር ተስማሚ ሆኖ ስላገኘሁት በድጋሚ አቅርቤዋለሁ
መግቢያ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዮሐንስን
ወንጌል በተረጎመበት በ፳፩ ኛው ድርሳኑ “ ጌታችን በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ጥያቄ በቃና ሰርግ ላይ ስለምን ውሃውን
ወደ ወይን ጠጅነት እንደቀየረው ከአብራራ በኋላ ከዛሬ 1500 ዓመት
በፊት በአሁኑ ጊዜ እንደ አዲስ ግኝት ተደርገው የሚታዩትን አብዝቶ በመመገብ የሚመጡትን የጤና ጉድለቶች ጽፎልን እናገኛለን ፡፡ ጽሑፉ ተተርጉሞ እንዲህ ቀርቦአል
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅነት ያኔ
እንደቀየረ ዛሬም እኛን ድካማችንንና እንደ ወራጅ ውሃ በአንድ ቦታ ጸንቶ መቆየት የተሣነውን የሥጋ ፈቃዳችንን ከመቀየር አልተቆጠበም
፡፡ ዛሬም አዎን ዛሬም ልክ እንደውሃ ቀዝቃዛ ፣ደካማና ፣ ያልተረጋጋ ጠባይ ያለቸው ሰዎች አሉ ፡፡ እነዚህን ፈቃዶቻችንን ወደ
ጌታችን አናምጣቸው ፤ እርሱ ወደ ወይንነት ይቀይራቸዋል ፡፡ ከዚያም በኋላ ውኃ ሆነው ከእንግዲህ አይቀጥሉም ፡፡ ነገር ግን ለራሳቸውና
ለሌሎች ደስታን የሚሰጡ አካላት ይሆናሉ ፡፡
በውሃ የተመሰሉት እነማን ናቸው ? ለዚህ ከንቱ ዓለም ሕሊናቸውን ያስገዙ
ወገኖች ፣ የዚህን ዓለምን ቅምጥልነት ፣ አለቅነትንና ክብርን የሚሹ አይደሉምን ? እነዚህ ፍቃዶቻችን እንደውኃ የሚፈሱ ፣ ፈጽሞ
ያልተረጋጉ ፣ ለአመፃ የሚፋጠኑ ቁልቁል የሚምዘገዘጉ ውኆች ናቸው ፡፡