በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
05/06/2004
ዘመኑ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ አንድ ቫላንታይን የሚባል ቅዱስ እንደሆነ የሚነገርለትና
በሰማዕትነት ያረፈ ቄስ ነበር፡፡ በእርሱ ስምም በአውሮፓ ፌብሯሪ ዐሥራ ዐራት ቀን በእኛ አቆጣጠር የካቲት ስድስት የፍቅረኞች
ቀን ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ ነገር ግን የኋላ ኋላ ይህ በዓል በሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አንዳይከበር ታገደ፡፡ ነገር ግን አንደገና
ይህ በዓል ሕይወት ዘርቶ በአውሮፓውያን ዘንድ ይከበር ያዘ ፡፡ ቀስ በቀስም በዓሉ የአውሮፓውያን መሆኑ ቀርቶ የመላው ዓለም ሆነ፡፡
በሀገራችንም የፍቅረኞች ቀን መከበር ከጀመረ ሰነባብቶአል፡፡ ይህን እስከዚህ ካልኩ ይበቃኛል፡፡ ምክንያቱም ከእኛ ትውፊት ጋር ፈጽሞ የማይዛመድ ስለሆነ ትቼዋለሁ፡፡ ነገር ግን አልነቅፍም፤ ዓላማዬም ይህ አይደለም የኔ ትኩረት ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ
ክቡር ስለሆነው ጾታዊ ፍቅር አንድ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ጾታዊ ፍቅር ሰማያዊ፣ ድንቅና ግሩም ነውና፡፡