በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
07/11/2007
እንደ መንፈሳዊ መረዳት ድንቅ የሚለኝና የሥነ ተፈጥሮአችን አንዱና መሠረታዊ ክፍል ስለሆነው ነገር ልንግራችሁ። ከእናት ማኅጸን ሥጋችን ከነፍሳችን ጋር ተዋሕዳ ከተፈጠረችበት ጊዜ አንስቶ ወደ እርጅናና ሞት ስታዘግም ነፍሳችን ግን እለት እለት እየታደስችና በእውቀት ሙሉ እየሆነች በመምጣት ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው እርሷ በእግዚአብር ዘንድ እንደታወቀች እስክታውቅ ድረስ ደርሳ ፍጹም ወደ መሆን ታድጋለች። የዛኔ እግዚአብሔር አምላኩዋን አባ አባ ስትለው በፍጹም ልጅነት መንፈስ ሆና ነው። እንዲህ በመሰለ መንፈሳዊ ከፍታ እያደገ የሚመጣው ግን ሰሎሞን "ጥበብ" ያለው ሲወድቅም ሲነሣ ያልራቀው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእርሱም ጋር የሆነለት ሰው ብቻ ነው።