Sunday, December 30, 2012

“ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ”



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
22/04/2005
ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ የተለቀቀ ጽሑፌ ነው፡፡
በዛሬው ቀን ዓለም ለመዳን የቅድስት ድንግል ማርያምን ይሁንታን የፈለገበት ቀን ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከምንም በላይ የሰውን ነጻ ፈቃድ ስለሚያከብር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲልከው ፈቃዱዋን ይጠይቃት ዘንድ ነበር፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት መሰላችሁ “እነሆ በደጅህ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል”(ራእ.3፡20) እንዳለው ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን በይዘቱ የቅድስት እናታችን  ይሁንታ በጣም የተለየ ነው፡፡ ስለዚህም የዓለም መዳን በእርሱዋ ይሁንታ ላይ ነውና እግዚአብሔር በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በኩል የቅድስት ድንግል ማርያምን ፈቃድ ጠየቀ፡፡ ለእርሱዋም በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አንደበት እግዚአብሔር ቃል ለሰው ልጆች መዳን ከእርሱዋ ተፀንሶ ለመወለድ ፈቃዱ እንደሆነ፣ እርሱዋንም የዘለዓለም እናቱና የሰው ልጆችን ፍጹም የመውደዱ ምልክት ሊያደርጋት እንደወደደ አበሰራት፡፡ ቅድስት እናታችንም ፍጹም ትወደውና ታመልከው የነበረው እግዚአብሔር ከእርሱዋ ተወልዶ ዓለምን ለማዳን መፍቀዱን ስትሰማ በፍጹም ደስታ ተሞልታ ግሩም በሆነ ትሕትና “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ” “እንደቃልህ ይደረግልኝ” በማለት ዓለምን እፎይ አሰኘቻት፡፡ እስከዛች ጊዜ ድረስ ዓለም በጭንቀት ተውጣ የእርሱዋን መልስ በጉጉት ትጠባበቅ ነበር፡፡

Saturday, December 29, 2012

“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ” በቅዱስ ኤፍሬም



ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ
20/04/2005
ቅዱስ ኤፍሬም “እንዳይፈረድባቸሁ አትፍረዱ” የሚለውን ኃይለ ቃል እንዲህ ይተረጉመዋል፡፡(ማቴ.7፡1-2) “ጌታችን አትፍረድ ሲል ኢፍትሐዊ ፍርድን ማለቱ ነው፡፡ ስለዚህም ኢፍሕታዊ ፍርድን ብትፈርድ ባንተ ላይ ይፈረድብሃል፡፡ በመሆኑም ፍርድን የሚለይ መንፈሱ ሳይኖርህ አትፍረድ፡፡ ፍትሐዊ መስሎህ ፍትሐዊ  ያልሆነ ፍርድን ልትፈርድ ትችላለህና፡፡ እንዲህም በማድረግህ ከፍርድ አታመልጥም፡፡
በመሆኑም ይህ ቃል “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ  የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይላችኋልና”(ማቴ.6፡4) ከሚለው ኃይለ ቃል ጋር መጣመር አለበት፡፡ ይህ ኃይለ ቃል አትፍረድ ከሚለው ሕግ ጋር እንዴት ይጣመራል? ፍትሐዊ የሆነ ፍርድን በአንድ ሰው ላይ ስትፈርድ በጸጋው ሕግ ደግሞ ይቅር ልትለው ይገባሃል፡፡ ቅን የሆነ ፍርድን ፈርዶ በጸጋ ግን ይቅር ላለ ሰው እግዚአብሔር አምላክም ይቅር ይለዋል፡፡ ስለዚህ ጌታችን ቅን ፍርድን ምክንያት አድርገው ለበቀል ለሚነሳሱ ሰዎች  “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ” ብሎ አስተማረን፡፡ ይህም ማለት “ራሳችሁ አትበቀሉ” ማለቱ ነው፡፡ “በቀል የኔ ነው እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ” እንዲል ጌታችን፡፡(ሮሜ.12፡19) ሌላው ደግሞ በመልክ ወይም ስለወደዳችሁ እንዳው በከንቱ አትፍረዱ ነገር ግን ከጥፋታቸው ይማሩ ዘንድ ምከሩዋቸው ገሥጾአቸው ሲለን ነው፡፡

Friday, December 28, 2012

እኔ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ራሱ መንፈሱ የእምነት ምንጭ ነው እላለሁ



ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
19/04/2005
በመጽሐፍ ብቻ የሚለው አመለካከት ለእኔ  ትክክል አይመስለኝም፡፡ ከመጽሐፍ ይልቅ በልብ ሰሌዳ በመንፈሱ የተጻፈ የመንፈስ ቅዱስ መልእክት አለ፡፡ መንፈሱ ያደረበት ሰው የማይመረመረውንና የማያልቀውን የእግዚአብሔርን ሃሳብና ፈቃድ ወደ መረዳት ይመጣል ሁሌም መንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ የሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልሰፈሩ ወይም ያልተብራሩ እውነታዎች ይገልጥለታል፡፡
 በብሉይም በሐዲስም የእግዚአብሔር ፈቃድና ሃሳብ በወረቀት ላይ በብዕር ቀለም መጻፍ ያስፈለገበት ምክንያት ሰዎች አስቀድሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ በልባቸው ጽላት ላይ የጻፈውን ፈቃዱንና ሕጉን በኃጢአት ምክንያት ፈጽመው በመዘንጋታቸው ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ፈቃዱን አውቀው በጽድቅ ይመላለሱ ዘንድ የተሰጠ ሁለተኛው እድል ነው፡፡ ለዚህ ማሳያው ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ያሉ ቅዱሳንና ሐዋርያት እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ሳይጻፍላቸው በሐዋርያት ትምህርት ይኖሩ የነበሩ ቅዱሳን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡

Thursday, December 27, 2012

በዓለ ክብሩ ለቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
19/04/2005
ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ የተለቀቀ ጽሑፍ

ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም  አነሣሁ” ካለ በኋላ አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ  ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፡5-9)

ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ይህን ለመረዳት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ መለኮቱ ለወንጌላዊው ዮሐንስ የተገለጠበትን መገለጥ መመልከት በቂ ነው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ በራእይ ስለተመለከተው የክርስቶስ ግርማ ሲናገር፡- “ከኋላዬም እንደ መለከት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅን ሰማሁ፡፡…የሰው ልጅ የሚመስልን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ልብስ የለበሰ ፣ ወገቡንም በወርቅ ዝናር የታጠቀ ነበር፡፡ ራሱና የራስ ጠጉሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፡፡ እግሮቹም በእሳት የነጠረና የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙህ ውኃ ድምፅ ነበረ፡፡”… ባየሁትም ጊዜ ከእግሩ ሥር ወደቅሁ አንደ ሞተ ሰው ሆነሁ” አለ፡፡(ራእይ.1፡2-17) በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ቅዱስ ገብርኤል በግርማው አምላኩን እንደሚመስል አንረዳለን፡፡  የስሙም ትርጓሜ የሚያስዳው ይህን እውነታ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነውና፡፡

Monday, December 24, 2012

ወንድሞቼና እኅቶቼ በጋብቻ መነኩሳት ትሆኑ ዘንድ ምኞቴ ነው!!



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
15/04/2005
ፍጹም አንድ መሆን፡፡ የራስን አካል የሚያውቁትን ያህል ማወቅ ምንኩስና የሚለውን ቃል ፍቺ ይሰጠናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መንፈሳዊ ጋብቻ የሚለው በመለኮትና በሥጋ መካከል የተፈጸመውንና በልደት የተገለጠውን ተዋሕዶን ነው፡፡ ይህን ጋብቻ ይለዋል፡፡ አንድ ክርስቶስ፣ አንድ ኢየሱስ፣ አንድ የእግዚአብሔር ልጅ፣ እርሱ የመለኮትና የሥጋ ተዋሕዶ ውጤት ነው ይህን ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተነሣ በገዛ ሥልጣኑ አደረገው ፡፡ ፍጹም የተዋሐዱ ፈጽሞ የማይለያዩ አንድ አካል ብቻ የሆነ፡፡ መነኮስ ማለትም አንድ ብቻ፤ ብቸኛ ማለት ነው፡፡ሁለቱ አንድ ይሆናሉ” የሚለው ቃል ሲፈጸም አንድብቸኞች ይሆናሉ ግን ሙሉ ናቸው፡

Friday, December 21, 2012

አርምሞ (ለአንድ ወንድሜ የጻፈኩት)



ከዲ/ን ሽመልስ መርጊ
12/04/2005
አርምሞ ከራስ ጋር ለመሆን ጊዜን ከመስጠት የሚጀምር ነው፡፡ እንዲያው በባዶ ግን አይደለም፤ አስቀድሞ የግል ጊዜ ሊኖረን  ግድ ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ዐይን ውስጥ ትንሽ ብናኝ ብትገባ እንደምትረበሽና እንደምትታወክ ከዚያም በላይ አንደምታለቅስ እንዲሁ ሕሊናም ጥቃቅን በምንላቸው ኃጢአቶች መረበሹና መታወኩ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ ሕሊናችን በኃጢአት ከተያዘ መረጋጋትን ገንዘባችን ማድረግ አይቻለንም፡፡
ነገር ግን ሕሊናችን ከኃጢአት ነጽቶ እርጋታን ገንዘቡ ሲያደርግ በጥሙና ሆነን ያለ አንዳች መደነቃቀፍ መንፈሳዊውን ዓለምና ምሥጢር ወደ መረዳት እንመጣለን፡፡ ስለዚህ ወደ ጥሙና ሕይወት ከመግባታችን በፊት አስቀድመን ለንስሐ ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን በኋላም ንስሐ መግባት፡፡ በንስሐ የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ይቀጣጠላል፡፡ በዚህም ምክንያት ስለእግዚአብሔር በጥልቀት ለማወቅ እጅግ እንጓጓለን፡፡ በዚህ ሰዓት ነው እንግዲህ የምናነባቸውን ምንባባትና የምንጸልያቸውን ጸሎታት መምረጥ ያለብን፡፡ ያለበለዚያ ፈጽሞ አርምሞን ገንዘባችን ማድረግ አይቻለንም፡፡ ስለዚህ ሌላውን የሚነቅፉና ለጠላት ጥፋትን የሚለምኑ ምንባባትንና ጸሎታትን ከማንበብ መከልከል ተገቢ ነው፡፡

Saturday, December 15, 2012

የሞቴ ማስታወሻ



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
06/04/2005
ሰው ማለት እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ከንቱ የሆነች አንዲትም ሰከንድ የለችም፡፡ ሰውም እንዲሁ ዘመኑን ሁሉ በጥንቃቄና ያለዝንጋዔ እግዚአብሔርን መስሎ ሊኖር ተፈጠረ፡፡ የሰው ደስታው እውነት፣ ጽድቅ፣ ቅን ፈራጅነት፣ ከእውቀት ያልተለየ ፍቅር ናቸው፡፡ እነዚህን በተመለከተ አዳም አባታችን፣ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና እርሱን በቅርበት ያወቁት ሐዋርያት ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ከጌታችንና ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርትም የምናስተውለው ሰው ሊጸድቅ የሚችለው ልቡን በቃሉ ሞልቶ የሥነ ምግባራችን ቁልፍ በሆነው ማስተዋል የተመላለሰ  እንደሆነ ነው፡፡ ይህን ግን ምናልባት በቀን ውስጥ ሁለት ደቂቃ ግፋ ቢል አምስት ደቂቃ ሰጥተን ብናስበው ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ስለእግዚአብሔር እውቀቱ ካለው ነው፡፡ የሌለው ግን ዘመኑን ሁሉ እንደ ነዌ ያሳልፈዋል፤ አንድም ሰከንድ እንኳ እግዚአብሔርን የሚያስብበት ጊዜ የለውም፡፡ ከዚያ ይልቅ በዝንጋዔ ሆኖ በስሜቶቹ ፈቃድ እየተነዳ በኃጢአት ሲንቧቸር ይኖራል፡፡ ይህ የአብዛኞቻችን ሕይወት ነው፡፡

Wednesday, December 12, 2012

ክብርት ስለሆነችው ሥጋችንና በእርሱዋ የእግዚአብሔር ፈቃድ



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
04/04/2005 ዓ.ም
ሥጋ ክብርት ናት፡፡ ገናም ከአፈጣጠሩዋ በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረች ናት፡፡(ዘፍ.9፡6) የማይታየው የእግዚአብሔር መልክና ባሕርይ የሚታየው በሚታየው በሥጋ ተፈጥሮአችን በኩል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን መልክና ክብር በክርስቶስ አይተነዋል፡፡ እኛንም ማዳኑ በሥጋው ሰውነቱ ነው፡፡ ተወለደ፣ በየጥቂቱ አደገ፣ ደከመ፣ አንቀላፋ፣ ታመመ፣ ተጨነቀ፣ ተሰቃየ፣ ሞተ መባሉ በሥጋው ነው፡፡
ሰውነታችን ከምድር አፈር መፈጠሯም በራሱ ሥጋን ቢያልቃት እንጂ የሚያሳንሳት አይደለም፡፡ ምድር በመኅፀኑዋ ሕይወትን፣ ኃይልን፣ ውበትን፣ መድኀኒትን፣ ለፍጥረት ሁሉ ምግብ የሆኑ በዓይነትና በብዛት እንዲሁም በይዘት እጅግ ብዙ ንጥረ ነገሮችን ሰውራና አቅፋ የያዘች ናት፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ከሰማይ በሚወርደው ዝናብ ምክንያት ተብላልተውና ተስማምተው በእግዚአብሔር ጥበብ ለፍጥረት ሁሉ ምግብን፣ ፈውስን፣ ውበትና ኃይልን ሲሰጡ ይኖራሉ፡፡ ይህን አስመለክቶ እግዚአብሔር “በዚያ ቀን እመልሳለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ለሰማይ እመልሳለሁ ሰማይም ለምድር ይመልሳል ምድርም ለእህልና ለወይን ጠጅ ለዘይትም ትመልሳለች፡፡”(ሆሴዕ.2፡23)ይለናል፡፡

Monday, December 10, 2012

የታኅሳስ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ፕሮግራም



በዚህ ወር ምንባብ ኢሳይያስን፣ከአንደኛው ዮሐንስ እስከ 3ኛው ዮሐንስ ፣ ሉቃስን፤ ግብረ ሐዋርያትን፣ሮሜን አንብበን እንፈጽማለን፡፡ ማቴዎስን እንጀምራለን፡፡ 
የጠዋት ምንባብ
ቀን
መዝ.ዳዊት
ከብሉይ ኪዳን
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
ከወንጌል
1
መዝ.1-4
ኢሳ.8
1ዮሐ.5
ሉቃ.10
2
መዝ.9-10
ኢሳ.10
3ዮሐ.1.
ሉቃ.11፡27-54
3
መዝ.15-17
ኢሳ.12
የሐዋ.1
ሉቃ.13
4
መዝ.19-20
 ምሳ.20
ሮሜ.10፡1-12 
 ማቴ.12፡38-42
5
መዝ.23-25
ኢሳ.15
የሐዋ.3
ሉቃ.16
6
መዝ.30-31
ኢሳ.17
የሐዋ.5፡1-16
ሉቃ.18
7
መዝ.34-35
ኢሳ.19
የሐዋ.6
ሉቃ.20
8
መዝ.38-39
ኢሳ.22
የሐዋ.7፡35-60
ሉቃ.22፡1-30
9
መዝ.42-44
ኢሳ.24
የሐዋ.8፡26-40
ሉቃ.23
10
መዝ.47-49
ኢሳ.26
የሐዋ.10፡1-29
የሐ.1
11
መዝ.53-55
ኢሳ.28
የሐዋ.11
የሐ.3
12
መዝ.59-60
ኢሳ.30
የሐዋ.13፡1-15
የሐ.5
13
መዝ.64-66
ኢሳ.33
የሐዋ.14
የሐ.7
14
መዝ.69-70
ኢሳ.36
የሐዋ.15፡13-41

የሐ.9
15
መዝ.73-74
ኢሳ.38፤39
የሐዋ.16፡16-40
የሐ.11
16
መዝ.78
ኢሳ.41
የሐዋ.19፡1-20
የሐ.13
17
መዝ.80-82
ኢሳ.43
የሐዋ.20
የሐ.15
18
መዝ.86-88
ኢሳ.45
የሐዋ.21፡17-40
የሐ.17
19
መዝ.90-92
ኢሳ.47
የሐዋ.23
የሐ.19
20
መዝ.96-98
ኢሳ.49
የሐዋ.25
የሐ.21
21
መዝ.103-104
 ሲራ.10
 የሐዋ.11፡22-30
 ሉቃ.10፡1-16
22
መዝ.106
 ዳን.8፡10-27
 ራእ.12፡7-12
 ሉቃ.1፡27-37
23
መዝ.108-110
ኢሳ.53
ሮሜ.1
ማቴ.4
24
መዝ.116-118
ጥበብ.3፡1-10
ኤፌ.5፡1-19 
 የሐ.5፡1-16
25
መዝ.119፡57-120
ኢሳ.56
ሮሜ.4
ማቴ.7
26
መዝ.120-124
ኢሳ.58
ሮሜ.6
ማቴ.9
27
መዝ.129-132
ኢሳ.60
ሮሜ.8፡1-17
ማቴ.11
28
መዝ.136-137
ኢሳ.62
ሮሜ.9
ማቴ.13
29
መዝ.140-142
ኢሳ.9፡1-6
 ዕብ.6፡1-8
ማቴ.1፡1-17 
30
መዝ.145-147
ኢሳ.65
ሮሜ.11
ማቴ.15


የማታ ምንባብ
ቀን
መዝ.ዳዊት
ከብሉይ ኪዳን
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
ከወንጌል
1
መዝ.1-4
ኢሳ.9
1ዮሐ.1
ሉቃ.11፡1-26
2
መዝ.9-10
ኢሳ.11
ይሁዳ.1
ሉቃ.12
3
መዝ.15-17
ኢሳ.13
የሐዋ.2፡1-21
ሉቃ.14
4
መዝ.19-20
ኢሳ.14
የሐዋ.4
ሉቃ.15
5
መዝ.23-25
ኢሳ.16
የሐዋ.5፡17-42
ሉቃ.17
6
መዝ.30-31
ኢሳ.18
የሐዋ.7.1-31
ሉቃ.19
7
መዝ.34-35
ኢሳ.20፤21
የሐዋ.8፡1-25
ሉቃ.21
8
መዝ.38-39
ኢሳ.23
የሐዋ.9
ሉቃ.22፡31-71
9
መዝ.42-44
ኢሳ.25
የሐዋ.10፡30-48
ሉቃ.24
10
መዝ.47-49
ኢሳ.27
የሐዋ.12
ዮሐ.2
11
መዝ.53-55
ኢሳ.29
የሐዋ.13፡16-52
የሐ.4
12
መዝ.59-60
ኢሳ.31፤32
የሐዋ.15፡1-12
የሐ.6
13
መዝ.64-66
ኢሳ.34፤35
የሐዋ.16፡1-15
የሐ.8
14
መዝ.69-70
ኢሳ.37
የሐዋ.18

የሐ.10
15
መዝ.73-74
ኢሳ.40
የሐዋ.19፡21-40
የሐ.12
16
መዝ.78
ኢሳ.42
የሐዋ.19፡1-20
የሐ.14
17
መዝ.80-82
ኢሳ.44
የሐዋ.21፡1-20
የሐ.16
18
መዝ.86-88
ኢሳ.46
የሐዋ.22
የሐ.18
19
መዝ.90-92
ኢሳ.48
የሐዋ.24
የሐ.20
20
መዝ.96-98
ኢሳ.50
የሐዋ.26
ማቴ.1
21
መዝ.103-104
ኢሳ.51
የሐዋ.27
ማቴ.2
22
መዝ.106
ዳን.8፡1-27
የሐዋ.28
ማቴ.3
23
መዝ.108-110
ኢሳ.54
ሮሜ.2
ማቴ.5
24
መዝ.116-118
ኢሳ.55
ሮሜ.3
ማቴ.6
25
መዝ.119፡57-120
ኢሳ.57
ሮሜ.5
ማቴ.8
26
መዝ.120-124
ኢሳ.59
ሮሜ.7
ማቴ.10
27
መዝ.129-132
ኢሳ.61
ሮሜ.8፡18-39
ማቴ.12
28
መዝ.136-137
ኢሳ.7፡10-17
 ሮሜ.9፡1-17
 ዮሐ.1፡1-14
29
መዝ.140-142
ኢሳ.63፤64
ሮሜ.10
ማቴ.14
30
መዝ.145-147
ኢሳ.66
ሮሜ.12
ማቴ.16