በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
10/06/2004
ፍቅር የሆነው አምላካችን ስለእርሱ የመከራ ወቅትና ትንሣኤ በአስተማረን ወቅት “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊያዝኑ ይገባቸዋልን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፡፡ በዚያን
ጊዜ ሚዜዎች ይጦማሉ” ብሎ ነበር፡፡ ጌታችን የእርሱን ልደትና የስብከት ዘመንን የሙሽርነት ወቅት ይላቸዋል፡፡ በእውነትም ልደትህ
በአንተ ያመኑትን ለአንተ ታደርጋቸው ዘንድ በእነርሱ አርአያ ለተገለጥከውና የሰዎች ልጆች መዳን ደስ ለሚያሰኝህ ላንተ ለጌታችን
የደስታ ቀን ናት፡፡ ጌታ ሆይ ላንተ ከነፍሱዋ ትገዛልህ ለነበረችውም ለቅድስት ድንግል ማርያምም የአንተ ከፅንሰት እስከ ልደት ያሉት
ቀናት የደስታ ቀናቶቹዋ ናቸው፡፡ የስብከትም ዘመን ለአንተ ራሳቸውን ለማጨት የፈቀዱ ሐዋርያት ወደ አንተ የቀረቡበት ወቅት ነውና
በእርግጥም የደሰታ ቀን ነው፡፡