መግቢያ
ኤፍሬም አጭር የሕይወት ታሪክ
ቅዱስ ኤፍሬም በሦስተኛው ክፍለ ዘመን በመጀመሪያዎቹ ሰባት
አሥርተ ዓመታት ውስጥ የኖረ የሥነ መለኮት ሊቅ ፣ የዜማ ደራሲ ፣ ባለቅኔ ፣ ሰባኪ ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ተርጓሚ የሆነ ጻድቅ
አባት ሲሆን ፣ በጊዜው በሮም መንግሥት ሥር በነበረችው በሶርያ ንጽቢን 1 በምትባለው ታላቅ ከተማ ከክርስቲያን ቤተሰብ በ፪፻፺፱
ዓ. ም ተወለደ ፡፡
በዘመኑ ሊቀ ጳጳስ በሆነው በቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን 2፣ ባደገባት ከተማ ፣ የዲቁና ማዕረግ ተሹሞ በከተማዋ በምትገኝ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን ሆነ ፡፡