በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
09/12/2004
ጭንቅ የሆነው የቤተ ክርስቲያን
የስደት ዘመን በንጉሥ ቆስጠንጥኖስ እስካበቃበት እስከ3ኛው ክ/ዘመን ድረስ ክርስቲያኖች ፍጹም በሆነ የቅድስና ሕይወት ውስጥ ይመላለሱ
ነበር፡፡ በውጭ በአላውያን ነገሥታትና በጣዖት አምልኮ በታወሩ ሕዝቦች እንዲሁም በአይሁድ የሚቀበሉት መከራ እርስ በእርስ ያላቸው ፍቅር እንዲጠብቅና እንዲተዛዘኑ እንጂ ከቅድስና ሕይወታቸው እንዲወጡ አላደረጋቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን ከ3ኛ ክ/ ዘመን
ጀምሮ በንጉሥ ቆስጠንጥኖስ ክርስትና የመንግሥት ሃይማኖት ስትሆንና ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ ሲገቡ ፍጹም
የተባለው ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
እየጎደፈ ሕዝቡም መረን እየለቀቀ ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ ብዙዎች ወደ ቀድሞ ግብራቸው ተመለሱ፡፡