በዙሪያችን ያሉ መምህራን
አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ልማር ካለ በዙሪያው የሚያስተምሩት አሉለት። ከዋኖቹና ከማይሳሳቱ ሊሳሳቱ እስከሚችሉት መምህራን በቅደም ተከተል ልንገራችሁ ፥-
የመጀመሪያው መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱ ልጅነትን ከተቀበልንበት ጊዜ አንስቶ መምህራችን ነው። ሁለተኛው ሥጋው ወደሙ ነው። ሥጋው ወደሙን የሚቀብል ሰው ሁሌም ወደላይ ወደ መላእክት ጉባኤ በመነጠቅ ክርስቶስን ወደ ማወቅ ከፍታ እያደገ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ለሰዎች ሊነገር የማይገባውን ሰምቶ ይመለሳል። ያም ማለት ክርስቶስ ባለበት እርሱ በዚያ ይኖራል። ሌላው ከጠባቂ መላእክት ነው። እነርሱ ከእኛ አይለዩም ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ እንድን ዘንድ ያለንን ማስተዋልንንና እውቀትን በመስጠት ይረዱናል። ያዕቆብን በመከራው ጊዜ የተራዳው እርሱ ጠባቂ መልአኩ ነበር። አብርሃምን ያስተማረው ለዳንኤል እውቀትንና ማስተዋልን የሰጠው እርሱ ነው ሌላው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው እነዚህ ለአንድ ኦርትዶክስ ክርስቲያን ከተጠቀመባቸው መምህራኖቹ ናቸው። ከዚያ በኋላ ልንሳሳት የምንችለው እኛ መምህራን እንከተላለን።
ቢሆንም ግን ክብር ይግባውና የእግዚአብሔርን ድምጽ እናውቀዋለንና አዲስም ቢሆን ከእግዚአብሔር የሆነውና ያልሆነውን የምንለይበት ሕሊናና መንፈስ ቅዱስ አለን። በዚህ ሁሉ ውስጥ ሆኖ ከእውቀት ባዶ ሆኖ መገኘት ይከብዳል።