ክብር ለእርሱ ለወደደን ይሁንና እርሱ እግዚአብሔር በእርሱ አርአያና አምሳል የፈጠረውን ሰውን ሊያልቀው በወደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ ሞት የሚስማማውን የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ ሰው ሆኖ ተወለደ፡፡ ከእርሷ የነሣውንም ሥጋና ነፍስ ባሕርይውን ሳይቀይር አምላክ አደረገው፡፡ በእርሱም በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ በጸጋ እኛ የእግዚአብሔር አብ ልጆች፣ የእርሱ የጌታችን ወንድሞች የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕፃናት ሆንን፡፡ በእርሱ በጌታችንም አማልክት ተሰኘን፡፡ ይህን ክብራችንን በትሩፋት ሥራዎች ከደከምን በዓይናችን ለማየት እንበቃለን፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊ ከጌታ ጋር መዋሐዷ ስለተገለጠላት ትጉህ ነፍስ ሲጽፍልን፡-