Sunday, August 5, 2012

ሐመረ ኖህ(በቅዱስ ኤፍሬም)



ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
29/11/2004
ቅዱስ ኤፍሬም በዚህ ቅኔያዊ ድርሰቱ ኖህ ከጥፋት ውኃ የዳነባትን መርከብ በቤተክርስቲያንና በመስቀሉ እንዲሁም በእምነት መስሎ ድንቅ በሆነ መልኩ አቅርቦት እንመለከታለን፡፡   
የኖህ ተምሳሌትነት በዘመኑ ከነበሩት ሕዝቦች ጋር ሲነጻጸር እንዴት ታላቅ ነበር፤ንጽሕናን እንደጥሩር ከለበሰው ኖህ ጋር በፍትሕ ሚዛን ሲመዘኑ እንደማይጠቅሙ እንደማይረቡ ሆነው ተቆጠሩ፡፡ፈጽሞ የማይነጻጸሩ ነበሩና በጥፋት ውኃው ሥር ዘቅጠው ቀሩ፡፡የኖህን ንጽሕና ከፍታ ለማሳየትም ኖህ በመርከብ ሆኖ ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡ በኖህ ንጽሕና ደስ ለተሰኘህ ለአንተ ለእግዚብሔር ክብር ይሁን፤ ለገዢነትህም ምስጋና ይገባል፡፡