ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
28/05/2004
ከምንባብ በፊት የእኔ መልእክት
የቅዱስ ኤፍሬም ሥራዎችን ማስተዋወቄ ብዙዎቻችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከውዳሴ ማርያም ውጪ በሌሎች ሥራዎቹ ስለማናቀው
ነው፡፡ ስለዚህም ጥቂት የቅዱስ ኤፍሬም ሥራዎችን ለማቅረብ እየሞከርኩ እገኛለሁ፡፡ ወደ ፊትም እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱስ ኤፍሬምን
ሥራዎች ለማስተዋወቅ ምኞቴ ነው፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም በቅኔያዊ
መዝሙራቱ የነቢዩ ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ሌሊት ሦስት መዓልት መሆኑን በተለያየ መንገድ የተለያዩ አሳቦቹን ለመግለጽ
ይጠቀምበታል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ
ጥቂቶቹን እነሆ ብያለሁ፡፡
v ሌጌዎን ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተገለጠው በቁጥር 2000 የሚደርሱ
የአጋንንት ሠራዊት ማለት ነው፡ እነዚህ አንድ ሰው ላይ ከትመው ይኖሩ ነበር፡፡ ጌታችንም እነዚህ አጋንንት ወደ ሰፈሩበት ሰው መንደር
በመምጣት ይህን ሰው ከእነዚህ አጋንንት ቁራኛነት አላቆታል፡፡ ይህን ቅዱስ ኤፍሬም ከዮናስ ወደ ባሕር መጣል ጋር አቆራኝቶ “ክፉ
የተባለው ሰይጣን እንዲህ አለ" እያለ በሰዎች መዳን የሰይጣንን ቁጭት ይገልጥልናል፡-
“ክፋት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ዛሬ ከቀደመው ይልቅ ታላቅ የሆነ ክፋትን ሠራህብኝ፡፡ እኛን
ማዋረድህ ሳያንስህ በነቢዩ ዮናስ ላይ የፈጸምከውን በእኛ ላይ ልትደግም መጣህ፡፡ ሌጌዎንን ወደ ባሕር ጥልቅ በመጣልም ተበቀልከን፡፡ ዮናስ
ከሦስት ቀን በኋላ ሕያው ሆኖ ከባሕር ውስጥ ቢወጣም ሌጌዎን ግን በባሕር ውስጥ ወዳለው ጥልቅ ሰጥሞ እንዲቀር አደረግህብን፡፡…