Friday, January 11, 2013

ፍትሐት በቤተክርስቲያን እንዴት?




በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
05/05/2005
“ስለሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ ስለእነርሱ የሚጠመቁ ስለምንድር ነው”(1ቆሮ.15፡29)
ጥምቀት ሰውን ከኃጢአት አንጽቶ የእግዚአብሔር ልጅነት ሥልጣንን በመስጠት ዳግም የሚወለዱበት ጌታችን የመሠረተልን ሥርዐት ነው፡፡ ነገር ግን ጥምቀት ስንል በመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት ትርጉም ብቻ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ስለሌሎችም መከራን መቀበል በራሱ ጥምቀት ነው፡፡ ጌታችን ስለእኛ የተቀበለውን ሞት ጥምቀት ብሎት እናገኘዋለን፡፡ “እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላለችሁን፡፡”(ማቴ.20፡22)