Saturday, January 19, 2013

እኛ ታቦት ስንል መሠዊያ ማለታችን ነው


በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ 
11/05/2005
በብሉይ ይፈጸም የነበረው ለሐዲስ ኪዳኑ ጥላ ነው፡፡ ስለዚህ ስለታቦት በተጻፈው ላይ እንደምናነበው በታቦቱ የላይኛው ክፍል ላይ ዙሪያውን አክሊል የሆነለት በግራና በቀኝ እንደሚናቸፉ አውራ ዶሮዎች ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ በወርቅ የተሠሩ የኪሩቤል ምስሎች ያሉበት የስርየት መክደኛ ወይም mercy seat የሚባል ሥፍራ እንዳለ እንመለከታለን፡፡ በዚህ ላይ እግዚአብሔር ለሙሴና ለእስራኤላውያን በደመና አምድ ይገለጥላቸው ነበር፡፡(ዘፀ.2522338-11)

Monday, January 14, 2013

ክርስትና ለእኔ እና እኔ አልስማማም እንዲሁም….



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
07/05/2005
ለእኔ ክርስትና ማለት ምን ማለት ነው ቢሉኝራስ መሆንብዬ እመልሳለሁ፡፡ በምን ሲባል ከኃጢአት በቀር በሁሉ ብዬ እመልሳለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ዕረፍት አለን፡፡ ክርስትና ድህነት ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ስለፍቅርና ስለቅንነት እኛ ያለንን እንደ ችሎታችን የጠየቁንን ስለምንሰጥ ለሥጋዊው ድህነት የቀረብን ነን፡፡ ቢሆንም በሥራ ያን ጉድለት እንደፍነውና ለምጽዋት እጃችንን እንዘጋለን፡፡ ነገር ግን ለሁሉ ማለትም ለምድራዊውም ለሰማያዊውም ሀብታችን ምንጩዋ ቤተክርስቲያን ብትሆን መልካም ነበር፡፡ በእርሱዋ በኢኮኖሚም ሆነ በሥነ ልቡና የደከሙት ተጠነካክረው ለዓለም እንደ ብርሃን በመሆን በእነርሱ መልካም ሥራ የእግዚአብሔር ስም ሊመሰገን ይገባው ነበር፡፡

Friday, January 11, 2013

ፍትሐት በቤተክርስቲያን እንዴት?




በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
05/05/2005
“ስለሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ ስለእነርሱ የሚጠመቁ ስለምንድር ነው”(1ቆሮ.15፡29)
ጥምቀት ሰውን ከኃጢአት አንጽቶ የእግዚአብሔር ልጅነት ሥልጣንን በመስጠት ዳግም የሚወለዱበት ጌታችን የመሠረተልን ሥርዐት ነው፡፡ ነገር ግን ጥምቀት ስንል በመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት ትርጉም ብቻ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ስለሌሎችም መከራን መቀበል በራሱ ጥምቀት ነው፡፡ ጌታችን ስለእኛ የተቀበለውን ሞት ጥምቀት ብሎት እናገኘዋለን፡፡ “እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላለችሁን፡፡”(ማቴ.20፡22)

Wednesday, January 9, 2013

የጥር ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም




 በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
01/05/2005


በዚህ ወር ምንባብ 2ኛ ሳሙኤልንና ፊልጵስዩስን እንጀምራለን፡፡ 1ኛ ሳሙኤልን ፣ ማቴዎስን፣ ማርቆስን ሉቃስን ሮሜን 1ኛና 2ኛ ቆሮንቶስን፤ ገላቲያንን፣ ኤፌሶንን እንፈጽማን፡፡ ሉቃስን፤ ግብረ ሐዋርያትን፣ሮሜን አንብበን እንፈጽማለን፡፡ ማቴዎስን እንጀምራለን፡፡ 

Sunday, January 6, 2013

“በአፉ መሳም ይሳመኝ”



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
28/04/2005
በአፉ መሳም ይሳመኝ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና፡፡”(ማኃ.1፡1) የሚለው ቃል በይሁዳ ቤተልሔም እነሆ ተፈጸመ፡፡ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰዎች የሚሰጠውን  ሰላምና ፍቅር እንዲሁም እርቅ የሚናፍቁ የነቢያትና የቅዱሳን የናፍቆት ቃል ነበር፡፡ “በአፉ” ሲል “በእግዚአብሔር ቃል” ሲለን ሲሆን “ይሳመኝ” ሲልም የእግዚአብሔር ቃልን ሰው መሆን መናፈቃቸውን የሚናገር ነው፡፡ እንዲህ ካልሆነ እንዴት በአፉ ሊስመን ይቻለው ነበር? ይህ ቃል እርቅ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል መፈጸሙ የማይቀር መሆኑን የሚያውጅ የናፍቆት ቃል ነው፡፡

ለነፍሳችን ሁለተኛዋ ነፍስ (በቅዱስ ኤፍሬም)



ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
28/04/2005
ወዳጄ ሆይ! እምነት ለነፍስህ ሁለተኛዋ ነፍስ እንደሆነች መርምርና እወቅ፡፡ ሥጋ በነፍስ እንድትቆም የነፍስም በሕይወት መኖር በእምነትህ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ እምነትህን ብትክድ ወይም ከራስህ ብታርቃት ነፍስህ ምውት ትሆናለች፡፡ በዚህም መሠረት የሚሞት ሥጋችን በነፍስ ላይ ጥገኛ እንደሆነች ነፍሳችንም በእምነት ላይ ጥገኛ ናት፡፡ እምነትም በእግዚአብሔር አብና በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ባደረገን በእውነተኛ ልጁ ላይ ጥገኛ ናት፡፡
በዚህም እውነት ሰው ነፍሱን በሰማያት ካሉት ጋር ያገናኛታል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው በነፍሱ በሕይወት ይኖራል፡፡ በሥጋ ሰውነቱም ያያል ይመለከታል፡፡ እንዲሁ እኛም በእምነት በፍቅርና በጥበብ የእግዚአብሔር መልክ ገንዘባችን አድርገን ከመለኮቱ ተካፋይ እንሆናለህ፡፡ ስለዚህም በነፍሳችን የሞትን እንዳንሆን ይህን ድንቅ የሆነ ማሰሪያ እንዳንበጥስ ወይም ነፍሳችን ከእምነት ባዶ እንዳናደርጋት እንጠቀቅ፡፡ ጌታችን ይህን አስመልከቶ እንዲህ ብሎ አስተምሮናልና “ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው”(ማቴ.8፡22)

Tuesday, January 1, 2013

የፍጥረት ሁሉ ናፍቆት እነሆ ከሴት ብቻ ተወለደ



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
24/04/2005
የፍጥረት ሁሉ ናፍቆት የሆነውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዐይነ ሥጋ ለማየት ዘመነ ዘመናት ተቆጥረው ለልደቱ 15 ዓመታት ሲቀሩት በቅድስት ድንግል ማርያም እድሜ የልደቱ ዘመን ተካቶ ተቆጠረ፡፡ የሰው ልጆች ሁሉ የድኀነትን ቀን ናፍቀው ዐይኖቻቸው በዚህች ድንግል ብላቴና መወለድና ማደግ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ነበር፡፡
እነሆ ከላይ ከአርያም የምስራቹ ቃል በመልእክተኛው በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም መጣ፡፡ እርሱዋም “እነሆኝ የጌታዬ ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ” ብላ በድንግልና ጸንሳ ዘጠኝ ወር በማኅፀኗ ተሸክማ በድንግልና ወለደችው፡፡ እረኞች የእረኞችን አለቃ ተመልከተው ደስ አላቸው፡፡ ሰብአ ሰግል በደስታ ለአምላክ የሚቀርበውን ወርቅ እጣን ከርቤ አቀረቡለት በፊቱም ወድቀው ሰገዱለት፡፡ መላእክትም “ስብሐት ለእግዚአብሔር ሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ” እያሉ አመሰገኑ ሰማያውያን ከምድራውያን ጋር ምስጋናን አቀረቡ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ሰከረ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም በቀደሞይቱ ሔዋን ምትክ የሕያዋን ሁሉ እናት ሆነችልን፡፡ እኛም በጥምቀት እርሱን በመልበስ የእርሱ ወንድሞችና እኅቶች ተባልን፡፡ በእርሱም የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች ተሰኘን፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ ሃሌ ሉያ!!!