Monday, August 13, 2012

የፍቅሩ ድልድይ (በቅዱስ ኤፍሬም)



ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
07/12/2004
መግቢያ
በዚህ ርእስ ግሩም የሆነውን የቅዱስ ኤፍሬም መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት ጸጋውን እንመለከታለን ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ሲናገር  የሰውን ተፈጥሮአዊ ጠባይ በመጠቀም ነበር ፡፡ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ቅዱስ ኤፍሬም ታላቅ ገደል ወይም ጥልቁ ጸጥታ ብሎ ይጠራዋል፡፡ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም አስተምህሮ በሰው ላይ የሚታዩ ተፈጥሮአዊ ጠባዮችን ለራሱ በመስጠት በእርሱና በሰው መካከል ያለውን ሰፊ የሆነ ልዩነት ያጠበበው እግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡ እንዲህ ማድረጉ ክብር ይግባውና ለሰው ልጆች ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠውን መጠሪያና ጠባይ ለራሱ ተጠቅሞባቸው እናገኛቸዋለን፤ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የአጻጻፍ ዘይቤ ደግሞ እንደ ልብስ ለብሶአቸው እናገኛቸዋለን፡፡
በብሉይ ኪዳን በእኛ ምሳሌ በመገኘት ራሱን የገለጠልን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሚሰማን ሊያሳውቀን ስለጆሮዎቹ ነገረን፤ እኛን እንደሚመለከተን ሊያስረዳንም ስለዐይኖቹ ጻፈልን፡፡ በዚህ መልክ በምሳሌአችን ተገልጦ እግዚአብሔር እኛን ይመክረናል ይገሥጸናል፡፡ እርሱ በባሕርይው ቁጣና ጸጸት የሌለበት አምላክ ሲሆን ስለእኛ ጥቅም እነዚህንም ግብሮች ለራሱ ሰጥቶ ተናገረን፡፡

እርሱ በእኛ ምሳሌ ተገኝቶ ባያስተምረን እርሱን ባላወቅነው ነበር፡፡ እርሱ በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ በኩል ወደ እኛ ቀረበን እኛም ወደ እርሱ ቀረብን፡፡ አባት ልጁን ሲመክር በልጁ  ማስተዋል መጠንና እርሱን መስሎ እንዲመክር እንዲሁ እግዚአብሔር በእኛ ማስተዋል መጠንና የእኛን ተፈጥሮአዊ ጠባይ ለራሱ በመስጠት በእኛ ባሕርይ ስለፈቃዱ አስተማረን፡፡ ስለዚህም በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ ተገልጦ እኛን አስተማረን እንጂ በእርሱስ ባሕርይ ውስጥ ቁጣ፣ ጸጸት፣ እና የመሳሰሉት ባሕርያት የሉበትም፡፡  

እርሱ በእኛ ምሳሌ ቢገለጥልንም ባሕርይው እንደሰው ተለዋዋጭ አይደለም፡፡ቢሆንም ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ሲያስፈልግ እኛን ለማቅናት ባንዱ ጠባያችን ይታየናል ሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላኛው ጠባያችን ተገልጦ ይመክረናል ይገሥጸናል፡፡ እርሱ ስለእኛ ጥቅም ሲል  በመጀመሪያ የተገለጠበትን የእኛን መገለጫን እንደልብስ አውልቆ ሌላውን ለብሶ ይታየናል፡፡ እርሱ በምሳሌአችን ተገኝቶ ለእኛ በመናገሩ እርሱ እንዲህ ነው ማለት ግን አይደለም፤ ነገር ግን ባሕርይው የማይመረመር ነውና በምንረዳው በእኛ ምሳሌ ተገኝቶ ፈቃዱን ገለጠልን ፡፡
አፍቃሪያችን እርሱ በአንድ ቦታ በዘመን ርዝማኔ የሸመገለ አረጋዊ መስሎ ሲታየን፤ በሌላ ስፍራ ደግሞ እጅግ ብርቱ ተዋጊ ሆኖ ይገለጥልናል፡፡ በሽማግሌ አምሳል መታየቱ ፍትሐዊ መሆኑን ለማስተማር ነው፤ ብርቱ ጦረኛ ሆኖ መታየቱ እርሱን የሚቋቋመው የሌለ ኃያል እንደሆነ ሊያስዳን ነው፡፡
በአንድ ቦታ እንደሚዘገይ በሌላ ቦታ የሚቀድመው የሌለ ፈጣን እንደሆነ መጻፉ፤ በአንድ ቦታ እንዳዘነ በሌላ ቦታ ደግሞ እንዳንቀላፈ ሰፍሮ እናገኛለን ፤ በሌላ ቦታም ሁሉን እንዳጣ ምስኪን ሆኖ ለእኛ ይገለጣል፡፡ ይህ ሁሉ ስለእኛ ጥቅም የተደረገ እንጂ እርሱ ሁሉ የእርሱ የሆነ ባለጠጋ ነው፡፡ በእውን በእኛ በፍጡራኑ ላይ የሚታዩት ጠባያት በእርሱ ላይ አሉን? በፍጹም እንዲህ የምንል ከሆነ እርሱን ፍጡር እያደረግነውና እንፍራ፡፡
ቸር የሆነው ፈጣሪ አንዳች ሳይቸገር፣ ያለፈቃዳችን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሥራን እንድንፈጽም ማስገደድ ይቻለዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ማድረግን አልፈቀደም፡፡ ከዚህ ይልቅ በፈቃዳችን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሥራን እንድንሠራ ይሻል፡፡ ስለዚህ እርሱ የሚወደውን የጽድቅ ሥራ እንድንሠራና በጽድቅ ተጊጠን እንድንገኝለት በእኛ አምሳል ተገልጦ ይምክረናል፡፡ ሠዓሊ የሣለውን ሥዕል በቀለማት እንዲያስውበው፤ አምላካችንም በአምሳላችን ለእኛ በመገለጥ በጽድቅ ሕይወት ያስጌጠናል፡፡
አንድ ሰው በቀቀንን ንግግር ለማስተማር ቢፈልግ ራሱን በመስታወት ጀርባ ይሰውራል፡፡ በቀቀኑዋን ግን ከመስታወቱ ፊት በማድረግ የሰውን ቋንቋ ያሰማታል፡፡በቀቀኑዋም ድምፁን ወደሰማችበት አቅጣጫ ስትዞር የራሱዋን ምስል በመስታወት ውስጥ ታገኘዋለች፤ ምስሏን ስትመለከት ሌላ በቀቀን እርሱዋን እያነጋገረቻት ይመስላታል፤ ስለዚህም አጸፌታውን ትመልሳለች፡፡በዚህ መልክ ሰውየው በበቀቀን አምሳል በመገኘት ለበቀቀኑዋ ንግግርን ያስተምራታል፡፡
ይህች በቀቀን ከሰው ጋር ተግባብታ የመኖሩዋ ምሥጢር በእርሱዋ አምሳል የሰው ቋንቋን በመማሯ ነው፡፡ እንዲሁ ከሁሉ በላይ በባሕርይው ረቂቅ የሆነውና ማንም በማይደርስበት ብርሃን ውስጥ የሚኖር  መለኮት ስለፍቅር ከላይ ከከፍታው ራሱን ዝቅ በማድረግ በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ ተግኝቶ ፈቃዱን አስተማረን፤ ሁላችንንም ወደ ጽድቅ ሕይወት ለመምራት በደካማው በሰው ተፈጥሮአዊ ጠባይ ተገለጠ፡፡
እርሱ አንድ ጊዜ በእድሜ ርዝማኔ ያረጀ ሽማግሌ መስሎ ሲታይ ሌላ ጊዜ በተዋጊ ተመስሎ ይገለጥልናል፡፡ በአንድ ቦታ የማያንቀላፋ ትጉህ እረኛ ሆኖ ሲታይ፤ በሌላ ስፍራ ደግሞ እንዳንቀላፋ ሆኖ ይገለጥልናል፤ በአንድ ቦታ እንደሚጸጸት ሆኖ ሲገለጥልን፤ በሌላ ስፍራ ደግሞ ጸጸት የሌለበት ጌታ እንደሆነ ያስተምረናል፡፡
በፈቃዳችን ራሳችንን ለማስተማር እንድንበቃ  እርሱ በሚወሰንና በማይወሰን አምሳል ለእኛ ተገለጠልን፡፡ በአንድ ስፍራ ብሩህ በሆነ የሰንፔር ድንጋይ በሚመስል ወለል ቦታ እንደቆመ ሆኖ ሲታየን፤ በሌላ ቦታ ደግሞ ሰማይንና ምድርን የሞላ ፤ ፍጥረት ሁሉ በመሃል እጁ የተያዘች እንደሆነች ነገርን፡፡…..
በአንድ ስፍራ በአምሳላችን ሲገለጥ ቦታ የሚወስነው ይመስለናል፤ እርሱ ግን በሁሉ ስፍራ ነው፡፡ በሌላ ስፍራ እኛን በቅድስና ሕይወት የበቃን ያደርገን ዘንድ ራሱን ዝቅ በማድረግ ለእኛ አርዓያ በመሆን ይመራናል፤ በሌላ ስፍራ ጌትነቱንና ባለጠግነቱን በመግለጥ በእርሱ ብቻ እንድንመካ ያስተምረናል፤ በዚህ መልክ እኛን በክብር ለማላቅ ሲል አንዴ ታናሽ ሌላ ጊዜ ታላቅ ሆኖ ይገለጥልናል፡፡እርሱ ታናሽ ሆኖ እንደተገለጠው ታላቅ ሆኖ ባይገለጥልን ኖሮ ደካማ ማስሎን በናቅነውን እርሱን ከመታዘዝ በተመለስን ነበር፡፡ እንዲህ እንዳይሆንም አንዴ ታናሽ ሌላ ጊዜ ታላቅ ሆኖ ይታየናል፡፡
  የእኛን ታናሽ የሆነን ተፈጥሮ ለማላቅ ሲል ታናሽ መስሎ የተገለጠልንን አምላክ እናድንቅ፡፡…እርሱ አይደለም በታላቅነቱ በእኛ አምሳል ተገልጦልን እንኳ ስለእርሱ መለኮታዊ ባሕርይ መረዳት አልተቻለንም እንዴት ታዲያ እርሱ ለእኛ በማይመረው ባሕርይ ተገልጦ ቢናገር ፈቃዱን ልንረዳ ይቻለን ነበር፡፡ ነገር ግን በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባያችን በኩል ፈቃዱን ለእኛ በመግለጡ እጅግ እየረቀቅን በእውቀትም እየተነጠቅን መጣን፡፡ ከእርሱ ስንርቅና በኃጢአታችን እየታወርን ስንመጣ በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ  በመገለጥ ከኃጢአትና ከጨለማ ሕይወት እንድንወጣ ያደርገናል፡፡ ስለዚህም ስለበደላችን በመጸጸት በንስሐ ወደ እርሱ እንቀርባለን፡፡
በብሉይ ኪዳን እንዲህ በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ በመገለጥ ሕዝቡን የመምከሩና የመምራቱ ምክንያቶቹ  ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በሰው አምሳልና አርዓያ እንደሚታይ ሲያስገነዝባቸው ሲሆን ሁለተኛው ግን የሰውን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ ሲገለጥ ሰውነቱ አምላክነቱን እንደማያጠፋው ሊያስተምራቸው በመፈለጉ ነው፡፡
አፍቃሪያችን እግዚአብሔር ለእኛ ለባሮቹ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በሚታይ አካል ተገለጠ፤ ነገር ግን በሰው አምሳል በመገለጡ እርሱን በማሣነስ እንዳንጎዳ፣አንዴ በሰው ባሕርይ ተገኝቶ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ አምላክነቱ ተገልጦ አስተማረን፤ በዚህም እርሱን የሚመስለው እንደሌለ ተረዳን፡፡ እርሱ በሰው አምሳል መታየቱ በአምላክነቱ እንዳይገለጥ አልከለከለውም፡፡ ጌታ ሆይ ተፈጥሮአዊ ጠባያችንን የፍቅርህ ድልድይ በማድረግ ፍቅርህን ስለመገብከን እንወድሃለን እንገዛልሃለን፡፡ 
ለወደደን በእኛ አርዓያ ተገልጦ ወደ መንግሥቱ ላቀረበን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!!!
    

5 comments:

  1. እርሱ በእኛ ምሳሌ ተገኝቶ ባያስተምረን እርሱን ባላወቅነው ነበር፡፡ እርሱ በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ በኩል ወደ እኛ ቀረበን እኛም ወደ እርሱ ቀረብን፡፡ አባት ልጁን ሲመክር በልጁ ማስተዋል መጠንና እርሱን መስሎ እንዲመክር እንዲሁ እግዚአብሔር በእኛ ማስተዋል መጠንና የእኛን ተፈጥሮአዊ ጠባይ ለራሱ በመስጠት በእኛ ባሕርይ ስለፈቃዱ አስተማረን፡፡ ስለዚህም በእኛ ተፈጥሮአዊ ጠባይ ተገልጦ እኛን አስተማረን እንጂ በእርሱስ ባሕርይ ውስጥ ቁጣ፣ ጸጸት፣ እና የመሳሰሉት ባሕርያት የሉበትም፡፡
    እርሱ በእኛ ምሳሌ ቢገለጥልንም ባሕርይው እንደሰው ተለዋዋጭ አይደለም፡፡ቢሆንም ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ሲያስፈልግ እኛን ለማቅናት ባንዱ ጠባያችን ይታየናል ሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላኛው ጠባያችን ተገልጦ ይመክረናል ይገሥጸናል፡፡ እርሱ ስለእኛ ጥቅም ሲል በመጀመሪያ የተገለጠበትን የእኛን መገለጫን እንደልብስ አውልቆ ሌላውን ለብሶ ይታየናል፡፡ እርሱ በምሳሌአችን ተገኝቶ ለእኛ በመናገሩ እርሱ እንዲህ ነው ማለት ግን አይደለም፤ ነገር ግን ባሕርይው የማይመረመር ነውና በምንረዳው በእኛ ምሳሌ ተገኝቶ ፈቃዱን ገለጠልን ፡፡

    ReplyDelete
  2. kaleheyewete yasemalen segaw yebezalehe gerum yehone yeheyewete megebe newe

    ReplyDelete
  3. Amen:)+ Geta Hoy tefeteroawi tebayachenen yefeqereh deledey aderegeh feqeren selemegebeken enewedehalen enegezalehalen zarem zeweterem Amen Wendemachen Qale Hiwot Yasemalen Tebarek:)

    ReplyDelete
  4. kale hiwot yasemalgh sile ,satanism,sile misterawi amlkowoch ena misterawi menafste gar selemidrgu ginghnetoch ,symbols bebith orthodoxawi blogs lay ayweram......yih neger betam wesagh yebithwochen wetatochin lib yashefete yenen chemro guday newna silzih mereja yemiset blog endtayew gabezkuh..........................http://antiglobalconspiracy.blogspot.com/

    ReplyDelete
  5. yihen lemegebiya gabezkuh ... ..ሶስት-መዓዝን (ትሪያንግ) በኢሉሚናቲ የተለያዩ መገለጫዎች፡- በሮዚክሩሽያኖችም ሆነ በሜሶኖች ወይም በመተተኞች፣ ኮከብ ቆጣሪዎች እና ጥቁር አስማት /ጠቋዮች እና ሌሎችም ኢሉሚናቲ ተከታዮች ዘንድ በበዓላት አከባበር ግዝያት ወሳኝ ስፍራ ይይዛል፡፡

    ሴጣናውያንና መተተኞች፣ ጥንዱ ሶስት መዓዝን፣ የሰለሞን ማህተም (ሄክሳግራም) የሚባለው ሰፊ ቦታ አለው፡፡ ይህ ማህተም በተጨማሪም የአይሁዶች “ማገን ዴቪድ” ይባላል፣ ይህ ኮከብ ከሁለት ትሪያግሎች የተሰራ ነው፡፡ አንዱ ትሪያግል ወደ ላይ የሾጠጠው ስጋ ወይም ቁሳዊውን አካልና የወንድ የመራባት ተግባርን ይወክላል፤ ወደ ታች የሚጠቁመው ትሪያግል የሴት ወሲባዊነትንና መንፈሳዊ አለምን ይወክላል፡፡ ስለዚህም እዚህ የወንዴውና የሴት ትሪያግሎች ተጠላልፈው እናያለን፡፡ ይህ ወሲባዊ ውህደትን ይወክላል፡፡ በተጨማሪም የተቃራኒዎች መጣጣምን /መታረቅን፣ ዪን እና ያንግ (በሩቅ ምስራቆቹ)፣ እግዚአብሄርና ሴጣንን ያሳያል፡፡ ይህ መገዳደር የበዛበት የምልክቱ ትርጉም ግልፅ ሆኗል፡፡

    ReplyDelete