በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
06/06/2004
ፆታዊ ፍቅር ክርስቶስን በማወቅ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ እጅግ ጣፋጭና ማራኪ ይሆንልናል፡፡
እንዲያ ከሆነ ባል በሚስቱ ተፈጥሮ በኩል የጌታውን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ እኛን መንፈሳዊያን ያደረገንን መንፈስ ቅዱስን
እንዲሁም ቤተክርስቲያንን ይመለከትባታል፡፡ ሚስትም በባሎዋ መስታወትነት ለሔዋን እናትም አባትም የሆነውን ቀዳማዊ አዳምንና እርሱዋን
ከጎኑ በፈሰሰው መለኮታዊ ውኃ አንጽቶ ከጎኑ በፈሰሰው ክቡር ደሙ ተቤዥቶ የወለዳትን ዳግማዊውን አዳም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን ትመለከተዋለች፡፡ በሚወልዱአቸው ልጆቻቸው ውስጥም በሥጋ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም እቅፍ የነበረውን፣ እንደ እግዚአብሔር
የባሕርይ ልጅነቱ ግን ከአባቱ እቅፍ የሆነውን ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስን በአንድነት በልጆቻቸው ይመለከቱታል፡፡