በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
24/09/2005
“ስብከት ወተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም” ከተባለ መጽሐፌ
የተወሰደ
“እናንተ እውራን ሆይ ኑ ቅረቡ ያለዋጋ ብርሃንን ተቀበሉ ፡፡ እናንተ
እግራችሁ የሰለለ ኑና በጌታ ተፈወሱ፤ አንተ ድዳና ደንቆሮ ናና ቃልን ከአምላክህ ተቀበል”
በእጆቹ ጣቶች ጌታ የፈወሰው ያ ድዳና ደንቆሮ ሰው አምላክ ወደ እርሱ ቀርቦ ምላሱን
እንደፈታለት ፣ ጆሮውንም እንደ ከፈተለት ተረድቶ ነበር፡፡(ማር.፯፥፴፩-፴፯) ምላሱ ረቶ እንዲናገር
፣ ጆሮውም እንዲሰማ የጌታ ጣቶች ባይነኩት ኖሮ መለኮት እንደነካው
ባልተረዳ ነበር ፡፡ ነገር ግን በጣቶቹ መለኮት የምላሱን እስራት ፈታ የጆሮዎቹን በሮች ከፈተ፡፡
የሰውነታችን ፈጣሪ የሆነው እርሱ ወደ ሕመምተኛው ቀረበ ግሩም በሆነው ድምፁ ያለአንዳች ሕመም የጆሮዎቹን መስኮቶች ከፈታቸው፡፡ አንደበቱ ቃልን ከመውለድ መክኖ የነበረውን ይህን ድዳ ሰው የምስጋናን ቃል እንዲወልድ በማድረግ የቃል መካንነቱን አራቀለት፡፡ አዳምን ሲፈጥረው ያለ አንዳች ትምህርት እንዲናገር እንዳደረገው፤ እንዲሁ ይህንንም ድዳና ደንቆሮ የነበረውንም ሰው ተምሮ ለማወቅ አስቸጋሪ የሆነውን ቋንቋ በአንዴ እንዲናገር አበቃው፡፡