ትርጉም ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
25/12/2007
ይህቺ ድህነት ሙሉ ትኩረትን እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚረዱ ተግባራት መኖርን ትጠይቃለች።ይህ ነው ለቅዱስ ኤፍሬም ድህነት የሚለው ቃል ትርጉሙ። ድህነት የሥጋ ድህነት ማለት አይደለም ለቅዱስ ኤፍሬም ይህ እንዳልሆነ እርሱ ራሱ በቃሉ "ለሥራ ከመትጋት አትለግም ምንም እንኳ ባለጠጋ ብትሆን፥ ሰነፍ ሰው በሥራ ፈትነቱ የተነሣ ቁጥሩ የበዛ ኃጢአትን ይፈጽማታልና" ብሎ ይመክራል። ስለዚህ ድህነት ማለት ለቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ከሆነ ድህነት ሳይሆን ድኅነት ነው።