Monday, February 3, 2025

የወንጌላዊው ዮሐንስ ቅድስና

 

በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ 

27/05/2017

የጌታ እቅፍን የሞቀው ከማዕዛውም ያሻተተው በእሳት እቅፍ ውስጥ ያለ ብረት አንዳች ነውር የሌለበት ንጹሕ እንዲሆን እንዲያንጸባርቅ፣ ለዓይንም ውብና ማራኪ እንዲሆን ቅዱስ የሚለው ቃል የሚያንሰው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቅድስና እንዲህ ነው። የጌታችንም እቅፍ ለእርሱ እንደ ከውር ሆኖት ከሥጋዊ ዐሳብ ሁሉ አነጻው። እቅፉ ዮሐንስን ጌታውን እንዲመስል አድርጎ ሠራው ። ዕውቀቱም ፈቃዱም ልቡናውም  የጌታችን ዕውቀት ፈቃድና ልቡና ሆነለት። ልቡናውም በጌታችን ፍቅር ተቃጠለ ። ፍቅር የዕውቀት ሁሉ ፍጻሜ ናትና የተሰወረውን ሁሉ ጌታችን ያለመቆጠብ ገለጸለት።  ስለዚህ ይህ ወንጌላዊ "በመጀመሪያ ቃል ነበር" በማለት ሀልዎተ እግዚአብሔርን ከማወቅ ርቀን በሥጋዊ ነገራችን ተጠምደን ላለነው፣ ታውረን ለነበርነው ለእኛ የጠፋነውን እኛን ስለ መውደዱ ከቅድስት እናታችን ሰው ስለሆነው ስለ ጌታችን ቅድምና ጻፈልን። የቅዱስ ዮሐንስ ዓይኖች የጌታ ዓይኖች ሆነዋል። ፍጥረትን ሁሉ አሰተካክለው ይመለከታሉ። ቅድስት ድንግል ማርያም ለእርሱ ከእናትም በላይ ናት፣ ዘወትር የሚያነባት የፍቅር ሰሌዳው ናት። ዛሬ ግን ምንድን ነው ስለ ዮሐንስ እንድጽፍ ያተጋኝ? "በመጀመሪያ ቃል ነበር" የሚለውን ቃል የወንጌሉ መቅድም ስላደረገው ነው ወዳጆቼ።

No comments:

Post a Comment