በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
04/07/2004
ይህን ጽሑፍ አንድ ወንድሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን በተመለከተ ለጠየቀኝ ጥያቄ
የሰጠሁት መልስ ነው፡፡ ይህም በዚህ ድኅረ ገጽ ላይ ይገኛል ነገር ግን ለሁሉ አንባቢያን እንዲደርስ በመፈለጌ ርእስ ሰጥቼ
እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡፡
ውድ ወንድሜ ሆይ እርግጥ ነው መጽሐፍ ቅዱስን ወዲያው ለመረዳት አስቸጋሪ
ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ ምዕራፍ ውስጥ ብዙ በይዘታቸው የተለያዩ መልእክቶች ስለሚተላለፉ ነው፡፡ ይህ የአንድ መንፈሳዊ
መጽሐፍ ጠባይ ነው፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ዓይነት አጻጻፍ በጥንት ቅዱሳን አባቶች መጻሕፍት ላይ ይገኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
እንደ አንድ ዛፍ ነው፡፡ ግንዱ አንድ ሲሆን ብዙ ቅርንጫፎችና እጅግ ብዙ ቅጠሎች ያሉት ሲሆን ፍሬው ግን ምንም በቁጥር አንዱ
ቅርንጫፍ ከአንዱ ቅርንጫፍ ይበልጥ የሚያፈራ ቢሆን አንድ ነው፡፡ ይህን ላስረዳህ፡፡ ግንዱ አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡ ወይም
ሥሩ እግዚአብሔር አብ ነው ግንዱ ክርስቶስ ነው ለዛፉ ሕይወት የሚሆነውና ፍሬ እንዲሰጥ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
ቅርንጫፎቹ እኛ ነን ቅጠሎቹም ፍሬ እንድናፈራባቸው የተሰጡን ጸጋዎች ናቸው፡፡ ሌላም አለ የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል ከአንድ ጉዳይ ይነሣና ከተነሣበት ጭብት ጋር ፈጽሞ የተለየ ሃሳብን ምናልባትም ብዙ
ሃሳቦችን አንስቶ ሊሆን ይችላል ከዚያ በኋላ ወደ ተነሣበት ርእሰ ጉዳይ ይመለሳል፤ ግንዱን ግን አይለቅም፡፡
ይህን የአንድ
የዛፍን ባሕርይ በመመልከት መረዳት ትችላለህ፡፡ አንድ ዛፍ ምንም እጅግ ቅርንጫፎች ቢኖሩት ከግንዱ የተቀበለውን ከተጠቀመ በኋላ
በምላሹ ለግንዱ የሚያደርሰው የራሱ የሆነ ሥርዐት አለው፡፡ ተመልከት ወዳጄ፡-ዛፉ ከግንዱ ምግቡን የሚያዘጋጅበትን ውኃና ሌሎች
ንጥረ ነገሮች ሲያገኝ ከባቢ አየሩንና ፀሐይን በቅጠሉ ወደ ግንዱ በማድረስ ምግቡን ያዘጋጃል፡፡ ይህንን ሲፈጽም
ከግንዱ ያገኘውንም በአንድነት በመጠቀም ነው እንጂ ከፀሐይና ከከባቢ አየሩ ያገኘውን ብቻ በመጠቀም አይደለም፡፡ ስለዚህ ግንዱ
ይህ ቅርንጫፍ ፍሬ እንዲያፈራ ያደርገዋል፡፡ ቅርንጫፉ እርሱ የሚፈጽመው የራሱ የሆነ ሚና ቢኖረውም ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርገው
ግንዱ ነው፡፡
ስለዚህ የዚህ ሒደት ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለግህ ዛፉን በትክክል ማወቅ
ይኖርብሃል፡፡ ያም ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ከሀ - ፐ ማለትም ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ዮሐንስ ድረስ አንብበህ መጨረስ አለብህ፡፡
ያለበለዚያ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት አትችልም፡፡ አንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንብበህ ሌላውን መተው ማለት ሥሩን አውቀህ
ግንዱንና ቅርንጫፉን አለማወቅ ወይም ግንዱን አውቀህ ሥሩንና ቅርንጫፉን ብሎም ቅጠሉንና ፍሬውን አለማወቅ ማለት ነው፡፡ ይህ
ደግሞ ተሰነካክለህ እንዳትወድቅ አይታደገህም፡፡ ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አስኳሉና መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን ግንዱ ያላደረገ የትኛውም ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፕሮግራም አውጥተህ መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ ለሙሉ
ቢያንስ በዓመት ሦስቴ መላልሰህ ልታነበው ይገባሃል፡፡ ያለበለዚያ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ልትቆም አትችልም፡፡
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ አሳቦችንም መረዳት የምትችለው ከዚያ በኋላ ነው፡፡ ምሳሌ እንዲሆን እኔ የምጠቀምበትን ፕሮግራም ልስጥህ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ መርሐ ግብር
መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልማድን ለማዳበር ሲባል የወጣ የምንባብ መርሐ
ግብር፡፡ በዚህ መልክ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነብ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን በዓመት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ ከማንበብ ባለፈ በየቀኑ
በሕሊናችን የምናኖረው እግዚአብሔራዊ እውቀት ይኖረናል፡፡
Ø የንባብ ሰዓቶቹ
በቤተክርስቲያን የፀሎት ሥርዐት መሠረት ሰባት ሰዓታት ሲሆኑ እነርሱም ከጠዋት12 ሰዓት፣ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፣ እኩለ ቀን 6ሰዓት ፣ከሰዓት 9 ሰዓት
፣ከምሽቱ 12 ሰዓት፣ ከሌሊቱ 6 ሰዓት፣ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ናቸው፡፡
Ø የንባብ መነሻ
ክፍሎች የሚሆኑት ዘፍጥረት (ብሔረ ኦሪት)፣ ኢዮብ ( የጥበብ መጻሕፍት)፣ ኢሳይያስ (የትንቢት መጻሕፍት)፣ ማቴዎስ(
ወንጌላት)፣ ሮሜ (መልእክታት)፤ እነዚህ መነሻ የምንባብ ክፍሎችና ዋና ዋናዎቹ የመጽሕፍ ክፍሎች ናቸው፡፡
Ø ከእነዚህ
በተጨማሪ በቀን ውስጥ አንድ ጊዜ የዮሐንስ ወንጌል በሦስት በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ ይነበባል፡፡
lለምሳሌ፡-
l
የዕለቱ ምንባብ ክፍል
|
የምንባብ ቀን
|
የቀን ምንባብ
ከተሰጡት የምንባብ ክፍሎች በቀን ውስጥ
|
የማታ ምንባብ
|
|||||
12 ሰዓት
|
6ሰዓት
|
9 ሰዓት
|
12ሰዓት
|
12 ሰዓት
|
6ሰዓት
|
9 ሰዓት
|
||
1
|
መስከረም1
|
ዘፍ.1-3፣ ኢዮ.1-3
|
ኢሳ.1-3፣
|
ማቴ.1-3
|
ሮሜ.1-3
|
ዘፍ.4-6፣ ኢዮ.4-6
|
ኢሳ.4-6፣
ማቴ.4-6
|
ሮሜ.4-6
|
2
|
መስከረም2
|
ዘፍ.7-9፣ ኢዮ.7-9
|
ኢሳ.7-9
|
ማቴ.7-9
|
ሮሜ.7-9
|
ዘፍ.10-12 ፣ኢዮ.10-12
|
ኢሳ.10-12፣ማቴ.10-12
|
ሮሜ.10-12፣
|
kal hiyiweti yaemalini rezizshim yageligiloti edima yisitilini
ReplyDeletekezi befet teyekih neber endit manbeb endalebeg kastwesk wendm ? ena betamm new dess yaleg endineb betam eyaberetahegg new ameseginalew.
ReplyDelete