Wednesday, April 4, 2012

በመስቀሉ የተፈጸመው ጋብቻ (በቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ)



 ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
27/07/2004
ከእኛ ጌታ በቀር ለእጮኛው ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው ማን ነው? ከቤተ ክርስቲያንስ በቀር የሞተ ሰው ለእርሱዋ ባልዋ ይሆን ዘንድ የምትሻ ሴትስ ማን ናት? ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ደሙን የጥሎሽ ስጦታ አድርጎ ያቀረበ ሰው ማን ነው? በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ  ከአንድዬ በቀር ጋብቻውን በሕማሙ ያተመ ሰው ማን ነው ? ከሞተ አካል መጽናናት ታገኝ ዘንድ በእቅፎቹዋ ይዛ በሰርግዋ በዓል ላይ የተገኘች ሙሽራ ከዚህ በፊት ታይታ አትታወቅም ? በየትኛውስ የሰርግ በዓል ላይ ነው ሙሽራውን ሥጋ በመቁረስ በሰርጉ ለታደሙት እንግዶች መብል ይሆን ዘንድ የተሰጠው?
ሚስት በባሏ ሞት ምክንያት ፍቺን ትፈጽማለች ፡፡ ይቺ ሚስት ግን በውድ ባሏ ሞት ምክንያት ከእርሱ ጋር ፍጹም ተዋሕዶን አደረገች፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ራሱን በመሠዋት ቅዱስ የሆነውን ሥጋውን ሁሌም ትመገበው ዘንድ  ክብርት ለሆነችው ሙሽራው መብል አድርጎ አቀረበላት ፡፡ ጉኑንም በመወጋት ቅዱስ ደሙን በጽዋው ሞልቶ ሰጣት ፡፡ በዚህም ምክንያት በልቡዋ ያኖረቻቸው ጣዖታት ሁሉ ተወገዱላት ፡፡ በእርሱም ቅዱስ ቅባት ከበረች ፤ እርሱንም በጥምቀት ውኃ ለበሰችው ፤ በሕብስት መልክ ተመገበችው ፤ እንደ ወይንም ጠጣችው ፡፡ በዚህም ምክንያት ሁለቱ በፍጹም ተዋሐዱ  አንድ እንደሆኑ ዓለም ሁሉ አወቀ ፡፡
ሙሽሪት ውዱዋ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ በመሞቱ ምክንያት በማንም አለወጠችውም ፡፡ በእርሱ ሞት ሕይወትን አግኝታለችና ለእርሱ ትልቅ ፍቅር አደረባት ፡፡ ባልና ሚስት ለዚህ ምሥጢር ዋነኞቹ ምሳሌዎች ናቸው ፡፡ እነርሱ ለእውነተኛው ጋብቻ እንደ ምሳሌና እንደ ጥላ የሚያገለግሉ ናቸው ፡፡ በእነርሱ መስሎ ሙሴ ይህን ታላቅ ምሥጢር ተናገረ ፡፡ ሙሴ ይህን ምሥጢር በመሸፈኛ ከልሎታልና ተሰውሮን ነበር ፡፡ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ገለጠልን፡፡ ሙሴ “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ”በማለት በምሥጢር የተናገረውን “እኔ ግን ይህን ስለክርስቶስና ስለቤተክርስቲያን ይላለሁ” (ኤፌ.5፡32)በማለት ተረጎመው፡፡”   

3 comments:

  1. kale hiwot yasemaln tsegawn yabzalh memeher!!! eni bebekuli buzu tmhert agichebet alew .ye manbeeb lmdi endidabr redtogal .ke hulum bebelete demo ye kedmo kudusan Abow mnga gurum ena dink sera sertewlun endalefu lesit lij yalachewn kber minga gurum endeneber tegenzibalehug...

    ReplyDelete
    Replies
    1. እግዚአብሔር ይስለጥልኝ ጸጋ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ልክነሽ ጸጋ በእውነትም ሴት ልጅ እጅግ ድንቅ የሆነች ፍጥረት ናት፡፡ ውበቱዋ ዓለም ለእርሱዋ ተፈጠረች፣ ጥበብ ውበቱዋ ነው ፍቅር ደግሞ ተፈጥሮአዋ ነው እምነት ሕይወቱዋ ነው፡፡ ሴት ልጅን መበደል ማለት አምላክን መበደል ማለት ነው፡፡ሴትን ልጅ አክብሮ ከእርሱዋ ብቻ ተወልዶአልና፡፡ እርሱዋ እውነት ናት ሌላም ሌላም ጸጋ

      Delete