ለፍቅር መምህር የሆነ ፍቅር እና ወዳጄ ሆይ .....
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
14/11/2004
ጾታዊ ፍቅር በራሱዋ ንጽሕትና ቡርክት እንዲሁም ቅድስት ናት፡፡ በዚህ ፍቅር የወደድካትን ካገኘሃት፤ ይህች ፍቅር በልብህ ውስጥ ርኅራኄን፣ አክብሮትን፣ትዕግሥትን፣ አርቆ አሳቢነትን ስትዘራብህ ታገኛታለህ፡፡ ከአጣሃት ግን ከልብህ ስለማትወጣ እስከ ነፍስህ ህቅታ ድረስ በልብህ ሃዘንን ተክላ ትኖራለች እንጂ ፈጽማ አትጠፋም፡፡ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁ ባለገንዘብ እንዲሆኑ ከመድከም ይልቅ ወደ እግዚአብሔር ባሕርይ የምታቀርባቸውን ይህችን ፍቅር በሕይወታቸው አግኝተዋት አእምሮአቸው ብሩህ ሆኖ ፍቅር የሆነውን አምላካቸውን እንዲያውቁትና እንዲያፈቅሩት ለዚህ ሕይወታቸው ትጉላቸው!!! እናንተ በእውነተኛይቱ ፍቅር ተጣብቃችሁ አንድ አካል ወደ መሆን የመጣችሁ ጥንዶች ሆይ! ንጽሕት፣ ቡርክት፣ ቅድስትና የእግዚአብሔር ፍቅር ፍጣሬ ብርሃን በሆነችው በዚህች ፍቅር ታግዛችሁ “ራስን ለሚወዱት አሳልፎ እስከመስጠት ወደሚያደርሰው” የክርስቶስ ፍቅር ታድጉ ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡ ለዚህች ፍቅር እንደ መጥምቁ ዮሐንስ አዋጅ ነጋሪዎች ትሆኑም ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡ አቤቱ አንተነትህን በዚህች በማንነታችን ውስጥ በጥልቀት በተከልካት ፍቅር እንድናውቅና በእንባ ሆነን በፍቅር እንድናመልክህ ይህችን ፍቅር በተፈጥሮአችን የሠራሃት አንተ ለዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን፡፡ በዚህች ፍቅር ጠብን እንድናጠፋትና ፍቅርህን ለብሰን እንድንገኝ ጌታ ሆይ እርዳን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ወዳጄ ሆይ መልካም ወዳጅ ትባል ዘንድ ምክር አለኝ
እግዚአብሔር አምላክህን ካላወቅክና ካልመሰልከው በቀር ባልንጀራህን፣ ወንድምህን፤ እኅትህን ከዛም አለፍ ሲል እናትህን አባትህን ከዚህም ሲከፋ የገዛ ሚስትህን ጤናማ በሆነ መውደድ ልትወዳቸው አትችልም፡፡ ስለዚህ ወዳጄ ይህን እርከን ተከትለህ ወደ እውነተኛው ወዳጅነት እለፍ፡፡ “በእምነት ላይ በጎነትን፤ በበጎነት ላይ እውቀትን፤ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፤ ራስንም በመግዛት ላይ መጽናትን፤ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፤ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማች መዋደድ፤ በወንድማማች መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ”(2ጴጥ.1፡7) እንዲህ አድርጎ ራሱን በቅድስና ያበቃ ሰው ራሱን ከራስ ወዳድነት በጠራ መልኩ ይወዳል፡፡ ስለዚህም ባልጀራውንም መውደድ ለባልንጀራው መልካም ወዳጅ መሆን ይቻለዋል፡፡

ReplyDelete