Saturday, September 15, 2012

ክርስትና ማለት እነኋት፡-


በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
05/01/2005
ክርስትና በመንፈስ ቅዱስ እገዛ የሚረዱዋት እምነት ናት፡፡ ብዙዎች ግን በአእምሮ ጠባያቸው ተደግፈው ክርስትናን ከተፈጥሮአዊ ሥርዐት ጋር አቆራኝተው ለመረዳት ሲሞክሩ ከክርስትና ጽንሰ ሐሳብ ሳቱ፡፡ ነገር ግን ክርስትናን ሊረዳት የሚፈለግ ካለ እነኋት፡-  እግዚአብሔር በዘመን ፍጻሜ ያደርግ ዘንድ ያለው አሳቡ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ስለሆነ(ኤፌ.110)ሁሉን ወደ ራሱ ሊያቀርብ ከዚያም ሲያልፍ ሊያዋሕድ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት እናታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሱዋ ነፍስ በመንሳት ሰው ሆነ፡፡ በመስቀሉ በፈጸመው የማዳን ሥራ ሁሉንም ወደ እርሱ አቀረባቸው፡፡(ዮሐ.12፡32)
ስለሆነም በእርሱ ያመንን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከሞቱ ጋር በመተባበር በእምነትም ከትንሣኤው በመካፈል አሮጌውን ሰው ቀብረን አዲሱን ሰው ለብሰን ተነሥተናል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች ልክ እንደ ጌታችን ለዚህ ዓለም የሞትን ስንሆን በትንሣኤው ደግሞ ሕያዋን ሆነን ከቅዱሳን መላእክትና ከቅዱሳን ነፍሳት ጋር አንድ ቤተሰብ ሆነን እየኖርን እንገኛለን፡፡ ይህን በፍጥረታዊው አእምሮ ጠባይ ለመረዳት እጅግ የሚከብድ ነው፡፡ ይህን እምነት አለኝ የሚልና በጥምቀት ከክርስቶስ ሞት ጋር የተባበረ ክርስቲያን ብቻ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው መረዳት የሚገነዘበው እውነት ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ጌታችን “እኔ ግንድ ነኝ እናንተ ቅርንጫፎች ናችሁ” አለን፡፡ በዚህ መልክ ከእርሱ ጋር ካልተባበርን በቀር ስለሰማያዊቱ ዓለም ምንም ዐይነት እውቀት አይኖረንም፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኒቆዲሞስን "ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለድክ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ልታይ አትችልም አለው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ያለእርሱ በጎ መሥራትም መዳንም አይቻለንም፡፡(ዮሐ.155-6)

ወደዚህ ረቂቅና ምጡቅ ነገር ግን ፍጹም እውነት ወደ ሆነው መረዳት እንድንመጣ በክርስቶስ አንዲት ጥምቀት ተሠርታልናለች፡፡ እንዲህ እንዲልበመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፣ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት፣ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ፡፡”(ኤፌ.44) በዚህም ምክንያት አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንሆን ዘንድ ተጠምቀናል”(1ቆሮ.1213) ስለዚህምእናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁተባለለን፡፡(1ቆሮ.1227)
በእርሱምወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኩራት ማኅበር ከሁሉ በላይ ወደ ሚሆነው ወደ እግዚአብሔር ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፤ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገረው(ክስን ሳይሆን እርቅን ወደሚያመጣው) ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋልተባልን፡፡(ዕብ.1222-24) እንዴት ቢባልሁላችንም ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን”(ሮሜ.63-5) ስለዚህምበጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበራችሁ በጥምቀት ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ፡፡”(ቆላ.212)ተባለልን፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ጳውሎስከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በምድር ያለውን አይደለም፡፡ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ”(ቆላ.31-4) ሲለን ጨምሮምከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮች(ጠበኞች) አይደላችሁም፡፡ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ መጻተኞች አይደላችሁም፡፡”(ኤፌ.219) አለን፡፡
ታዲያ እኛ ከቅዱሳን ጋር ያም ማለት በአጸደ ሥጋና በአጸደ ነፍስ ካሉት ቅዱሳን ጋር እና ከቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ ቤተሰብ ከሆንን እነርሱ ስለኛ ማማለዳቸው ምን ይደንቃል? እንዴትስ የማይታመን ሊሆን ይችላል? ይህ እኮ ሊያደርጉት የሚገባ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው”(2ጢሞ.5፡8)ብሎ አላስተማረንምን? ስለዚህ ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል ሊያስብ ሊጸልይ ይገባዋል፤ ይህ የሚገባ ነውና፡፡ ባይሆን ባይሆን ከዚህ ኅብረት እንዳንወጣ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም፡፡ በእውነት የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለሆነ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን፡፡ ነገር ግን ለዚህ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱ የመንፈሱን መያዣ ሰጠን”(2ቆሮ.52-5) እንዳለው እኛም የድርሻችንን ልንወጣ፤ ከዚህ ኅብረትም ላለመውጣት ኃጢአትን ደም እስከማፍሰስ ደርሰን በመቃወም በጽድቅ ሕይወት ልንተጋ ይገባናል፡፡

3 comments:

  1. ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በምድር ያለውን አይደለም፡፡ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ”(ቆላ.3፡1-4) ሲለን ጨምሮም “ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮች(ጠበኞች) አይደላችሁም፡፡ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ መጻተኞች አይደላችሁም፡፡”(ኤፌ.2፡19) አለን፡፡
    ታዲያ እኛ ከቅዱሳን ጋር ያም ማለት በአጸደ ሥጋና በአጸደ ነፍስ ካሉት ቅዱሳን ጋር እና ከቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ ቤተሰብ ከሆንን እነርሱ ስለኛ ማማለዳቸው ምን ይደንቃል? እንዴትስ የማይታመን ሊሆን ይችላል? ይህ እኮ ሊያደርጉት የሚገባ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው”(2ጢሞ.5፡8)ብሎ አላስተማረንምን? ስለዚህ ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል ሊያስብ ሊጸልይ ይገባዋል፤ ይህ የሚገባ ነውና፡፡ ባይሆን ባይሆን ከዚህ ኅብረት እንዳንወጣ ቅዱስ ጳውሎስ “በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም፡፡ በእውነት የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለሆነ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን

    ReplyDelete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  3. ቃለ ሕይወት ያሰማልን !

    ReplyDelete