Thursday, September 13, 2012

ከራኬብ ምን እንማራለን? እስቲ እንወያይ



በዲ/ን ሽመልስ መርጊ
03/01/2005
ወገኖቼ እስቲ ዛሬ ይክበር ይመስገንና የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅም ቅም አያት ስለሆነችው ስለራኬብ ትንሽ እንወያይ፡፡ ራኬብ ቤቱዋን በኢያሪኮ ቅጥር ላይ ሠርታ በሴተኛ አዳሪነት ብዙዎችን ታወጣና ታገባ የነበረች በዚህም ቤተሰቡዋን የምትመራ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ ግብጻውያንን በበረታ ክንዱ እንዳጠፋቸው በተረዳች ጊዜ የእስራኤላውያን አምላክ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ የተገነዘበች ሴት ነበረች፡፡ ይህች ሴት ኢያሱ ኢያሪኮን ይሰልሉ ዘንድ የላካቸውን ሁለት ሰላዮችን በቤቱዋ የተቀበለችና እነርሱን ከሚያሳደዱ ወታደሮች በመሸሸግ ያዳነቻቸው ሴት ነበረች፡፡ እንዲህም ማድረጉዋ በእምነት የእስራኤል አምላክ እውነተኛ አምላክ መሆኑን ስለተረዳች እርሱዋንና ቤተሰቡዋን ለማትረፍ ስትል የፈጸመችው ነበር፡፡ ኢያሪኮ በእስራኤላውያን ከጠፋች በኋላ ግን ሰልሞን ሚስቱ አድርጎ አገባት፡፡ ከእርሱዋም ቦኤዝን ወለደ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ እሴም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡ ከዳዊት ወገን ከሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያምም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ አዳነን፡፡

እኔን የገረመኝና አንዳች ነገር የጠቆመኝ ይህች ሴት ብዙዎችን በሴተኛ አዳሪነት ስታወጣና ስታገባ ያለመውለዱዋ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ብቻ ግን አይደለም፤ ሰልሞን እርሱዋን ከእነ ሙሉ ውበቷ ያገኘበት ምሥጢር እጅግ ይደንቀኛል፡፡ ይህች ሴት ልጅ ወልዳ ጡቶቹዋ አልወደቁም፣ በዝሙት ጠንቅ የሚመጠውም ሕማም አግኝቶአት ውበቱዋ አልረገፈም ነገር ግን በዚያን ጊዜ ሰልሞንን ማርኮ የሚይዝ ውበት ነበራት፡፡ ታዲያ ምሥጢሩ ምንድን ነው ትላላችሁ? እኔ ግን በጊዜው ራሱዋን ከበሽታና ከወሊድ የምትከላከልበት አንዳች ነገርን እየተጠቀመች እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ያለበለዚያማ ወደ እርሱዋ እንደሚገባውና እንደሚወጣው ሰው ቁጥር መጠን የብዙ ልጆች እናትና የሕመም ጎሬ በሆነች ነበር እላለሁ፡፡ እናንተስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላላችሁ?

2 comments:

  1. Selam lante yihun bekrstos selamawi endit senebetk memher yikrta melsu binegerg des yilegal lakew alchalkum eni ???

    ReplyDelete
  2. selam lante yehune deakon bemeketel ene melew ye egziabhier neger denke new hayalem new selezi lena leyastemer belo new melew ene

    ReplyDelete