ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
23/02/2005
ክብር ይግባውና ስለ ድንቅ እምነቱ
እግዚአብሔር አብርሃምን ለአሕዛብ አባት አደረግሁ አለው፡፡(ዘፍ.17፡7-8፤ሮሜ.4፡12) ድንቅ ስለሆነውም በእምነት መታዘዟ እግዚአብሔር
ሣራን የአሕዛብ እናት አደረጋት፡፡ ስለእርሱዋ
እግዚአብሔር “እባርካታለሁ ደግሞም ከእርሱዋ ልጅ እሰጥሃለሁ እባርካታለሁ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፡፡”(ዘፍ.17፡16)ብሎ ተናገረላት፡፡
ንጉሥ ዳዊትም እንዲሁ ከልጅነቱ
ጀምሮ ልቡን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ አንደበቱን የመንፈሱ አገልጋይ በማድረጉ እንደ ልቤ ተባለ፡፡ ከእርሱም ዘር ክርስቶስ እንዲወለድ
“ዘርህን ለዘለዓለም አዘጋጃለሁ፤ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ፡፡”(መዝ.88፡4) እንዲሁም “ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን
ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ መንግሥቱንም
አጸናለሁ፡፡ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል የመንግሥቱም ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ” አለው፡፡ ይህን ቅዱስ ዳዊት በመንፈስ አስተውሎ
“ጌታዬ ሆይ! እግዚአብሔር ሆይ ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው? ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ በፊትህ
ጥቂት ነበረ፤ ስለባሪያህም ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ የሰው ሕግ ነው፡፡(2ሳሙ.7፡12-4፤
18-19)
ብሎ ጌታውን አመሰገነ፡፡ በዚህ ቦታ ይህ “የሰው ሕግ ነው” ያለው “ክርስቶስን መምሰል” ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ለማስረዳት "የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ
ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና” ብሎ ጽፎልናል፡፡(ሮሜ.10፡4)
“ድንቅ ግን እውነት” የሆነው እውነታ
፡- እነዚህ በድንቅ እምነታቸው እና በእምነት መታዘዛቸው የተመሰከረላቸው እንዲሁም ከነፍሳቸው ጌታን የሚወዱና እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ
ያወርሳቸው ዘንድ ያዘጋጃትን መንግሥቱን በመንፈስ የተረዱ ሁሉ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ምሳሌ መሆናቸው ነው፡፡
ይህን ለመረዳት ስለነቢዩ ኤልያስና ስለመጥምቁ ዮሐንስ ማወቁ ሳይቀድም አይቀርም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ለመጥምቁ ዮሐንስ አካላዊው ምሳሌ
እንደ ነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል፡፡ ይህን አስመልክተው ጌታችን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ግርማ መለኮቱን ለሦስቱ ሐዋርያት
ካሳየ በኋላ ሐዋርያት “እንግዲህ ጻፎች፡- ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባል ስለምን ይላሉ?” ብለው ጌታን በጠየቁት ጊዜ “ኤልያስማ
አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል ነገር ግን እላችኋለሁ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም”(ማቴ.17፡
10-12) ብሎ መለሰላቸው፡፡ በዚህም ኤልያስ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አካላዊ ምሳሌ እንደነበረ መረዳት እንችላለን፡፡
እንዲሁ ለአብርሃም በዘርህ አሕዛብ
ይባረካሉ የሚለው የተስፋ ቃል እውን የሆነው በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ ስለዚህም አብርሃም ለእናታችን ለቅድስት
ድንግል ማርያም አካላዊ ምሳሌ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህም አብርሃም የሁሉ አባት እንደሆነ ቅድስት ድንግል ማርያምም ክርስቶስን
ወልዳ እውነተኛይቱ አብርሃም ሆናለችና
በእምነት እርሱዋን ለመሰሉዋት ሁሉ አባት ናት፡፡ እንዲሁ በእምነት በመታዘዝ “የአሕዛብ እናት አደርጋታለሁ” በማለት ተስፋ የተሰጣት
ሣራ ለእናታችን አካላዊ ምሳሌ ነበረች፡፡ ለአብርሃም “ከእርሱዋ ልጅ እሰጥሃለሁ አባርካታለሁ የአሕዛብም እናት ትሆናለች” የተባለው
በእውነት የተፈጸመው በድንግል ማርያም ነው፡፡ ስለዚህ አማናዊቱ የሕዝብና አሕዛብ ሁሉ እናት የተባለችው እናታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ናት ማለት ነው፡፡ ሣራ ግን ለቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ምሳሌዋ ነበረች፡፡
እንዲሁ ንጉሥ ዳዊት ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ምሳሌ
ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለዳዊት “ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፡፡ የመንግሥቱም ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ፡፡”
ብሎ አስቀድሞ ተናግሮለት ነበር፡፡ ይህም በእርሱ ዘመን የሚፈጸም እንዳልሆነ በመንፈስ በመረዳቱ “ስለባሪያህም ቤት ደግሞ ለሩቅ
ዘመን ተናገርህ” አለ፡፡ ይህ የተስፋ ቃል በቅድስት ድንግል ማርያም እውን ሆኖአል፡፡ ስለዚህም በአብሣሪው መልአክ በቅዱስ ገብርኤል
አንደበት ስለልጁዋ ስለክርስቶስ “የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም
ፍጻሜ የለውም፡፡”(ሉቃ.1፡32-33)ተባለላት፡፡ ስለዚህ አማናይቱ ዳዊት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ስለዚህም ልጁዋ በእርሱዋ የዳዊት
ልጅ ተባለ፡፡ እንዲሁ የጌታችን ቅም ቅም አያቶች ሁሉ በቅድስት እናታችን በኩል የእርሱ አባትም እናትም ሆኑ፤ በልጁዋም የእግዚአብሔር
ልጆች ተሰኙ፡፡
በቀዳማዊው አዳም ሰውነት የሰው ዘር ሁሉ አንድ እንደ ነበረ እንዲሁ ለክርስቶስ
የተገቡ ቅዱሳን ሁሉ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰውነት አንድ አካል ሆኑ፡፡ በእርሱዋም እርሱ የአብርሃም ልጅ፣ የሣራ ልጅ፣
የዳዊት ልጅ፣ እንዲሁም በእምነታቸውና በቅድስናቸው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙት ሁሉ ልጅ ተባለ፡፡በእርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ተባሉ፡፡
ከእርሱዋም በነሣው ሰውነት ልጁዋ ክርስቶስ እኛን ከእነዚህ ቅዱሳን ኅብረት ደመረን፡፡ አብረንም ከርስቱ ተካፋዮች ሆንን ፤ ከዘርዋም ተቆጠርን፡፡ በእርሱም
የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር
ቤተ ሰዎች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም” ተባለለን፡፡(ኤፌ.2፡19) እንዲህም ስለሆነ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ብሉዩንና ሐዲሱን በልጁዋ አንድ ያደረገች አማናዊቱ ቤተክርስቲያን እንደሆነች ለሁላችን የተረዳ ነገር ሆነ፡፡
ልጁዋ
መንግሥትንና ክህነትን ጠቅልሎ ለእርሱ እንዳደረገ እንዲሁ የሥጋ አባትነትና እናትነት ተጠቅለለው ለእርሱዋ ሆኑ፡፡ ስለዚህም ቀዳማዊው
አዳም ለሔዋን እናትም አባትም እንደነበረ፤ ቅድስት ድንግል ማርያምም ለጌታችን በሥጋ እናትም አባትም ሆና እንዳሳደገችው፤ እንዲሁ
ለእኛ በክርስቶስ ላመንነው ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ እናትም አባትም ሆነችን፡፡
ከእንግዲህ ከአብርሃም የሚልቅ እምነት፣ ከሣራ የሚልቅ በእምነት መታዘዝ፣
ከዳዊት የሚልቅ የልብ ንጽሕና ያላትን ቅድስት ድንግል ማርያምን በሕይወታችን ሁሉ አብነት አድርገን እንመላለስ፡፡ ስለዚህም እርሱዋ
“ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኀኒቴ ሐሴትን ታደርጋለች” እንዳለች እኛም እንደ እርሱዋ አምላካችንን ከነፍሳችን
ልንወደው፣ ልናከብረውና በእርሱ ደሰ ሊለን ይገባል፡፡ እርሱዋ እርሱን በሥጋ ጸንሳ እንደወለደችው በዚህም ሰውነቱዋንና ነፍሱዋን
የጌታ ቤተመቅደስ እንዳደረገች እኛም “እርሱ በእኛ እኛም በእርሱ” ከምንሆንበት ከታላቁ ምሥጢር ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ በመቀበል
ሥጋችንንና ነፍሳችንን የእርሱ ቤተመቅደስ ልናደርገው ይገባናል፡፡ ይህን በረጋ መንፈስና በተመስጦ ሆኖ ለሚያስተውለው እጅግ ግሩምና
ድንቅ የሆነ ምሥጢር ነው፡፡ አምላካችን ሆይ! ይህን ድንቅ ግን እውነት የሆነውን ሕይወት እያንዳንዳችን እንድናስተውለውና ለብሰነው
እንድንመላለስበት የበቃን አድርገን፡፡ ለአንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን አሜን!!!
This comment has been removed by a blog administrator.
ReplyDeleteወንድሞቹ ዮሴፍን መጥላታቸው፤ ልብሱን መግፈፋቸው፤ ለነጋዴዎች በሃያ ብር መሸጣቸው፤ የሐሰት ምስክር
ReplyDeleteመመስከራቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በመከራው ሰዓት ያጋጠሙትን ነገሮች ስለሚመስል ዮሴፍ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ
ይቆጠራል።
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ
አልቻሉም።..ወንድሞቹም። በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ
ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት። ዘፍ.ßÎ፡፬ እና ፰
ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም
አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል። ነገር ግን በሕጋቸው። በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም
ዘንድ ነው። ዮሐ.“¯፡µ»µ¯
እንዲህም ሆነ፤ ዮሴፍም ወደ ወንድሞቹ በቀረበ ጊዜ የለበሳትን በብዙ ኅብር ያጌጠቺቱን ቀሚሱን ገፈፉት፤
ዘፍ.ßÎ፡µÌ
ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ
ወሰዱ።...ስለዚህ እርስ በርሳቸው። ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም። ልብሴን እርስ
በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
ዮሐ.“ ¯፡µÌµ»
ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ ዘፍ.ßÎ፡µ•
በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ። ምን ልትሰጡኝ
ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት። ማቴ. µ”፡“ »“¯
ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን፣ በበር፣ በፀሐይ፣ በእንጀራ፣ በቤተ መቅደስ፣ በመንገድ፣ በማዕዘን ራስ፣ በሥር፣ በወይን ግንድ፣
ReplyDeleteበሕይወት ውኃ፣ በንጋት ኮከብ ይመሰላል። ከዚህ በታች የተገለጹትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ልብ ብለን እንመልከት።
ደግሞም ኢየሱስ። እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ
አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው። ዮሐ.፰፡“Òደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቤዛኲሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት
ክፍል ስለ ጾመ ድኅነት የተዘጋጀ ትምህርት።
አብርሃም ሰሎሞን/ብሥራተ ገብርኤል/
Debreselam Medhanealem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church MPLS, MN 55406 Tel. 612-721-1222 www.debreselam.net Page 6
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ዮሐ.፲፡፱
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና
የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ። ራእ.µÒ፡፭
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም
ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።...ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም
ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። ዮሐ.፮፡߯ እና áÃ
ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው። ስለዚህ አይሁድ። ይህ
ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን
ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ዮሐ.፪፡“®µÃ
ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐ.“ »፡፮
በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ኤፌ.፪፡፳
እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ
የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ
የተመደቡ ናቸው። ፩ጴጥ.፪፡፯፰
እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ። ራእ.µÒ፡“”
እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። ዮሐ.“¯፡፩
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ ለዘላለም ሕይወት
የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ዮሐ.፬፡“»