Wednesday, October 16, 2013

ምንኩስናና ትዳር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች


05/02/2006
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ


ክርስትና ለሰይጣን ይገዛ ከነበረ ዓለም ወጥቶ እርሱ የጽድቅ ጸሐይ የሆነው ክርስቶስ ብርሃን ሆኖት በቀን እንጂ በጨለማ የማንመላለስበት የቀን ልጅ ተሁኖ የሚኖርበት ሕይወት ነው፡፡ ክርስትና ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለን ነፍስ በምትሰጠው ሕይወት ሳይሆን ለዘለዓለም አባ አባ ብለን የምንጠራበትን መንፈስ በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ሆነን የምንኖርበት ሕይወት ነው፡፡ ስለዚህም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር ራሳችንን ለጽድቅ ሥራ ያጨን ደናግላን ነን፡፡ አገባንም አላገባንም ለክርስቶስ የታጨን በመሆናችን ደናግላን ነን፡፡ ይህ ድንግልና የሚጠፋው ክርስቶስን ክደን በሰይጣን ሕያዋን ሆነን የኖርን ሰዓት ነው፡፡ቢሆንም ግን ይህም ቢሆን በንሥሐ የሚታደስ ድንግልና ነው፡፡ ጌታ ጠፍተን እንድንቀር የማይወድ ከኃጢአታችን ይልቅ መጥፋታችን የሚያሳዝነው በንስሐ በተመለስን ጊዜም በደስታ እጆቹን ዘርግቶ በፍቅር የሚቀበለን አምላክ ነው፡፡
ስለዚህ አንዳንዶች ይህ ፍቅር ማርኳቸው  ሕይወታቸውን ለእርሱ ሰጥተው ለመንግሥቱ ጃንደረቦች ሆነው ሲኖሩ እኛ ደግሞ እስከ ጋብቻ ድረስ በድንግል እንኖራል፡፡ ካገባንም በኋላ ሰውነታችን ለክርስቶስ ማደሪያነት ስላጨነው ደናግላን ሆነን እንቀጥላለን፡፡ ስለዚህ ይህ የምንኩስና ወይም ራስን ለክርስቶስ ጃንደረባ አድርጎ የመኖር ሕይወት  ያገባውም ያላገባውም ክርስቲያን በሕይወት ዘመኑ የሚያልፍበትና የሚያውቀው ሕይወት ነው፡፡ ምንኩስና ክርስቶስን መስሎ አንዲት ቤተ ክርስቲያንን ማለትም መንፈሳዊ ጋብቻን ከክርስቶስ ጋር የፈጸመችውን ቤተ ክርስቲያንን ማለትም ትዳርን ያም ማለት ክርስቲያን ማኅበረሰቡን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማበልጸግ የሚያገለግል ሲሆን በትዳር ያለው ደግሞ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን የተመሠረተውን አንድነት በተግባር የሚሰብክ መንፈሳዊ ተቋም ነው፡፡ ስለዚህ ምንኩስናና ትዳር አንድነት ተመጋግበው የሚኖሩ በክርስቶስ የተመሠረቱ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ አንድነትና አገልግሎት እንዲሁም የማዳን ሥራ የሚሰበክባቸው ተቋማት ናቸው፡፡     

2 comments:

  1. ፡ለዚህም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር ራሳችንን ለጽድቅ ሥራ ያጨን ደናግላን ነን፡፡

    ReplyDelete
  2. Kale hiywot yasemalen

    ReplyDelete