Friday, October 12, 2012

የጥቅምት ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብና ከምንባብ በፊት የሚጸለይ ጸሎት



ትርዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
01/02/2005
ከምንባብ በፊት የሚጸልይ ጸሎት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በዚህ ምድር በምኖርበት ዘመን ሁሉ ቃልህን አንብቤ እረዳና ፈቃድህን እፈጽም ዘንድ የልቡናዬን ዐይኖች አብራልኝ፡፡ የሕግጋቶችን ምሥጢር ከእኔ አትሰውር ይልቁኑ የትእዛዛትህን መልእክታት ተረድቼ በሕግህ እደነቅ ዘንድ የልቡናዬን ዐይኖቼን አብራልኝ፡፡ በመጽሐፍህ ውስጥ የተሰወረውን የአንተን ጥበብ ግለጥልኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ በአንተ የእውቀት ብርሃንነት ለልቡናዬን ማስተዋልን ትሰጥ ዘንድ ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ በሠፈሩት መልእክቶችህ ደስ ይለኝ ዘንድ ብቻ አይደለም ነገር ግን ሕግጋቶችህንም ፈጽሜ እገኝ ዘንድ ተስፋዬን በአንተ ላይ አኑሪያለሁ፡፡  ቅዱስ በሆነው መጽሐፍህ ውስጥ የማነባቸው የቅዱሳኖችህ  ሕይወትና ትምህርቶች እኔን ወደ ኃጢአት የሚመሩኝ አይደሉም ይልቁኑ ለንስሐ፣ ለአእምሮዬ ብሩህነት ፣ ለነፍሴ ድኅነት እንዲሁም የርስትህ ወራሽ  እንድሆን የሚያበቁኝ ናቸው እንጂ፡፡ በጨለማ ላሉት ብርሃናቸው የሆንክና ባንተ መልካምን ሥራ እንዲሠሩ ከጸጋህ ያደልካቸው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ምስጋና ለአንተ ይሁን አሜን፡፡
የጥቅምት ወር የወጣ ፕሮግራም
  በዚህ ወር ምንባብ ዘፀአትን፣ ሉቃስን፣ ዮሐንስን፣ 1ኛና 2ኛ ቆሮንቶስን፣ ገላትያን፣ ኤፌሶንን፣ፊልጵስዩስን፤ ቆላስይስን አንብበን እናጠናቅቃለን፡፡ ዘዳግምን፣ ማቴዎስን፣ 1ኛተሰሎንቄን እንጀምራለን፡፡
የጠዋት ምንባብ
ቀን
መዝ.ዳዊት
ከብሉይ ኪዳን
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
ከወንጌል
1
መዝ.1-4
ዘፀአ.10
1ቆሮ.3
ሉቃ.3
2
መዝ.9-10
ዘፀአ.12
1ቆሮ.5
ሉቃ.5
3
መዝ.15-17
ዘፀአ.14
1ቆሮ.7
ሉቃ.7
4
መዝ.19-20
ዘፀአ.16
1ቆሮ.9
ሉቃ.9፡1-27
5
መዝ.23-25
ሲራ.21
ያዕ.1-1-12
ማቴ.10-1-15
6
መዝ.30-31
ዘፀአ.19
1ቆሮ.11፡1-16
ሉቃ.11፡1-20
7
መዝ.34-35
ዘፀአ.21
1ቆሮ.12
ሉቃ.12
8
መዝ.38-39
ዘፀአ.23
1ቆሮ.14፡1-25
ሉቃ.14
9
መዝ.42-44
ዘፀአ.32
1ቆሮ.15፡1-32
ሉቃ.16
10
መዝ.47-49
ዘፀአ.34
1ቆሮ.16
ሉቃ.18
11
መዝ.53-55
ዘሌዋ.19
2ቆሮ.2
ሉቃ.20
12
መዝ.59-60
ሲራ.38
2ቆሮ.4፡1-6
ማቴ.9፡9-13
13
መዝ.64-66
ዘኁል.11
2ቆሮ.5
ሉቃ.22፡32-74
14
መዝ.69-70
ሲራ.9
የሐዋ.8፡5-13

15
መዝ.73-74
ዘኁል.14
2ቆሮ.8
ዮሐ.1
16
መዝ.78
ዘኁል.17
2ቆሮ.10
ዮሐ.3
17
መዝ.80-82
ዘኁል.21
2ቆሮ.11፡16-33
ዮሐ.5
18
መዝ.86-88
ዘኁል.23
2ቆሮ.13
ዮሐ.7
19
መዝ.90-92
ዘኁል.25
ገላ.2
ዮሐ.9
20
መዝ.96-98
ዘኁል.30
ገላ.3፡13-29
ዮሐ.11
21
መዝ.103-104
ዘኁል.32
ገላ.4፡12-31
ዮሐ.13
22
መዝ.106
ሲራ.51
2ጢሞ.4፡5-15
ሉቃ.10፡1-11
23
መዝ.108-110
ዘዳግ.1
ኤፌ.1
ዮሐ.16
24
መዝ.116-118
ዘዳግ.3
ኤፌ.3
ዮሐ.18
25
መዝ.119፡57-120
ዘዳግ.5
ኤፌ.5
ዮሐ.20
26
መዝ.120-124
ሕዝ.34፡ 1-6
2ጢሞ.1፡1-9
ማር.19፡7-13
27
መዝ.129-132
ዘዳግ.8
ፊልጵ.2
ማቴ.2
28
መዝ.136-137
ዘዳግ.10
ፊልጵ.4
ማቴ.4
29
መዝ.140-142
ዘዳግ.12
ቆላ.2
ማቴ.6
30
መዝ.145-147
ዘዳግ.14
ቆላ.4
ማቴ.8



  
የማታ ምንባብ
ቀን
መዝ.ዳዊት
ከብሉይ ኪዳን
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
ከወንጌል
1
መዝ.5-8
ዘፀአ.11
1ቆሮ.4
ሉቃ.4
2
መዝ.11-14
ዘፀአ.13
1ቆሮ.6
ሉቃ.6
3
መዝ.18
ዘፀአ.15
1ቆሮ.8
ሉቃ.8
4
መዝ.21-22
ዘፀአ.17
1ቆሮ.10፡1-13
ሉቃ.9፡28-62
5
መዝ.26-29
ዘፀአ.18
1ቆሮ.10፡14-33
ሉቃ.10
6
መዝ.32-35
ዘፀአ.20
1ቆሮ.11፡17-34
ሉቃ.11፡27-54
7
መዝ.36-37
ዘፀአ.22
1ቆሮ.13
ሉቃ.13
8
መዝ.40-41
ዘፀአ.24
1ቆሮ.14፡26-40
ሉቃ.15
9
መዝ.45-46
ዘፀአ.33
1ቆሮ.15፡33-58
ሉቃ.17
10
መዝ.50-52
ዘሌዋ.18
2ቆሮ.1
ሉቃ.19
11
መዝ.56-58
ዘሌዋ.20
2ቆሮ.3
ሉቃ.21
12
መዝ.61-63
ዘሌዋ.26
2ቆሮ.4
ሉቃ.22፡1-30
13
መዝ.67-68
ዘኁል.12
2ቆሮ.6
ሉቃ.23
14
መዝ.71-72
ዘኁል.13
2ቆሮ.7
ሉቃ.24
15
መዝ.75-77
ዘኁል.15እና16
2ቆሮ.9
ዮሐ.2
16
መዝ.79
ዘኁል.19እና20
2ቆሮ.11፡1-15
ዮሐ.4
17
መዝ.83-85
ዘኁል.22
2ቆሮ.12
ዮሐ.6
18
መዝ.89
ዘኁል.24
ገላ.1
ዮሐ.8
19
መዝ.93-95
ዘኁል.26እና27
ገላ.3፡1-14
ዮሐ.10
20
መዝ.99-102
ዘኁል.31
ገላ.4፡1-11
ዮሐ.12
21
መዝ.105
ዘኁል.34እና35
ገላ.5
ዮሐ.14
22
መዝ.107
ዘኁል.36
ገላ.6
ዮሐ.15
23
መዝ.111-115
ዘዳግ.2
ኤፌ.2
ዮሐ.17
24
መዝ.119፡1-56
ዘዳግ.4
ኤፌ.4
ዮሐ.19
25
መዝ.119፡121-176
ዘዳግ.6
ኤፌ.6
ዮሐ.21
26
መዝ.125-125
ዘዳግ.7
ፊልጵ.1
ማቴ.1
27
መዝ.133-135
ዘዳግ.9
ፊልጵ.3
ማቴ.3
28
መዝ.138-139
ዘዳግ.11
ቆላ.1
ማቴ.5
29
መዝ.143-144
ዘዳግ.13
ቆላ.3
ማቴ.7
30
መዝ.148-150
ዘዳግ.15
1ተሰ.1
ማቴ.9
                                                       

Friday, September 28, 2012

ስለንስሐ የተላከ መልእክት



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
18/01/2005
ውድ እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ሕብረት በእጅጉ የምናፍቅልህ ወገኔ ሆይ እንደምን አለህልኝ? ውድ ክርስቲያን ወገኔ ሆይ ንስሐ ማለት ሕመምን ለዶክተር እንደ መናገር ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ሕመሙን ቢደብቅ ሕመሙ ወደማይደን ደረጃ ይለወጥና ነፍሱንም ሥጋውንም ያጠፋል፡፡ እንዲሁ በንስሐ መድኀኒትነት ከኃጢአት ቁስል ራሱን የማይፈውስ ክርስቲያንም ነፍሱንና ሥጋውን በገሃነም እሳት ያጠፋል፡፡ ውድ ክርስቲያን ወገኔ ሆይ! በክርስቶስ አምላክነት አምነን በመጠመቃችን ክብር ይግባውና ሁላችንም የክርስቶስ ወታደሮች ሆነናል፡፡ ስለዚህም ከኃጢአት ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ልንቆስል እንችላለን፡፡ አንድ ቁስለኛ ደግሞ የሐኪም እርዳታ በእጅጉ ያስፈልገዋል፤ ያለበለዚያ ሕመሙን ቢደብቅ ቁስሉ ወደ ጋንግሪንነት ተለውጦ የማይድን ይሆንና በሞት ይወሰዳል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው አንዴ ሞቷልና ሊድን አይችልም፡፡ ክርስቲያን ወገኔ ሆይ! ኃጢአት ለነፍሳችን እንደ በሽታ ነው፡፡በሽታ ጋር ደግሞ እንዲኖር የሚፈቅድ ሰው የለም፡፡ ስለዚህ ወደ ነፍሳችን መድኃኒት ወደ ክርሰቶስ ቅረብ፡፡ እርሱ ሕመምተኞችን እንጂ ጤነኞችን ሊፈውስ አልመጣምና፡፡(ማቴ.912) 
ወገኔ ሆይ ንስሐ ለመግባት አትፍራ፡፡ ወደ ካህን ስትቀርብ ወደ ክርስቶስ እንደቀረብክ ተረዳ፤ በእነርሱ አድሮ ይቅር የሚለን እርሱ ነው፡፡ ይህንን በምን እናረጋግጣለን ካልከኝ? ከታች እንደሚከተለው በጥቅስ አስደግፌ አቅርቤልሃለሁ፡፡

Monday, September 24, 2012

መስቀል ለእኛ ኦርቶዶክሳውያን



በዲ/ን ሽመልስ መርጊ
14/01/2005
ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር የተለቀቀ
መስቀል ለእኛ ኦርቶዶክሳውያን ልዩ የሆነ መንፈሳዊ አንድምታ አለው፡፡ በመስቀሉ እነሆ አሮጌው ሰዋችንን ሰቅለን ከጐኑ በፈሰሰው ውኃ በጥምቀት በመቅበር አዲሱን ሰው ክርስቶስን ለብሰን ተነሥተናል(ኤፌ.422-24)፡፡ 
 በመስቀሉ እርግማናችን ተወግዶ የኃጢአት ስርየትን አግኝተናል፡፡ በመስቀሉ ላይ ከተሰዋው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ በመመገብ ከሚያፈቅረን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ፍጹም የሆነ ተዋሕዶን መሥርተናል(ማቴ.2626) እርሱ በእኛ እኛም በእርሱ የሆንበት ሰማያዊ ማዕዳችን በመስቀሉ ላይ የተሠዋው መሥዋዕት ነው፡፡ (ዮሐ.656) 
በመስቀሉ በአዳምና በሔዋን መተላለፍ ምክንያት በእኛ ላይ ጸንቶ የነበረው የፍርድ ትእዛዝ ተሽሯል፡፡(ቆላ.214) በብሉይ ለሙሴና ለእስራኤል ዘሥጋ እግዚአብሔር አምላክ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ባለችው የቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ  ሆኖ በደመና አምድ ይገለጥላቸው ነበር፡፡(ዘጸአ.339) ቢሆንም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የምታገባዋ ጎዳና ተዘግታ ነበር፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ስለ ራሱና ስለሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳየናል”(ዕብ.96-) ብሎ ተናገረ፡፡