ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
14/05/2004
ልጄ ሆይ የአእምሮህን ምንጭ ንጹሕ አድርገው ፤
ከቁጣና ከነቀፋ ቃልም አጽዳው ፤
እንደ አዘቅት ጭቃ የሆነውን ቅናትን ከውስጥህ አስወግድ ፤
አስተሳሰብህ
ሁሉ ንጹሕ ይሁን፡፡
እግዚአብሔርን
ለማየት በጸሎት ወደ እርሱ በቀረብክ ጊዜ፤
አንተን በሚጠባበቁህ በእግዚአብሔር የምሕረት እጆች ፊት ጸሎትህ ንጹሕና ቅዱስ ካልሆነ፤
ሥላሴ በአንተ አይታመንምና እንዲህ ሆነህ ከፊቱ አትቅረብ፡፡
ከበከተው ለእርሱ መሥዋዕት አታቅርብ፤
ለኃያሉ አምላክ ከአንተ ዘንድ የሚቀርበው መሥዋዕት፤
በቅናት የተቃኘ ጸሎት ከሆነ፤
የበከተ መሥዋዕት ማለት ይህ ነው፡፡
ስለዚህ በአንተ ላይ በተቃጣው የቁጣ ቀስት ላይ ተጨማሪ ክብደትን አትጨምርበት፤
የተመረጥከው
ወዳጄ ሆይ ! በሚያቃጥል ፍቅር የተቀመመ መሥዋዕትን አቅርብ፤
ለእርሱ እንደ መሥዋዕት አድርገህ የምታቀርበው ጸሎትህ ነው፤
እንዲህ ዓይነት መሥዋዕትን የሚያቀርቡት መንፈሳውያን ናቸው፤
ከአምላክ ዘንድ የሚቀርብ ይቅርታን የሚያሰጥ የጣፈጠ መሥዋዕት ይህ ነው፡፡
ስለዚህም በጥናህ ውስጥ ጠብ ካለ እርሱ ባዕድ ፍም ነው፤
እርሱንና እርሱን የመሰሉትን ፍሞች ከጥናህ ውስጥ አስወግዳቸው፤
ልጄ ሆይ ባዕድ ፍምን በጥናህ ውስጥ በመጨመርህ ምን እንደሚመጣብህ አስበህ ፍራ፤
የአሮን ልጆች በድፍረት ያልታዘዙትን ፍም ከጥናቸው ውስጥ ጨምረው ነበርና፤ በእግዚአብሔር ቁጣ ጠፉ (ሌዋ.፲፥፩-፪)
የመሥዋዕቱ
ፍም ፍቅር ነው፤ በዚህም ፍም ላይ መሥዋዕት አድርገህ የምታቀርበውን ጸሎት አዘጋጅ፤
እንዲህ በማድረግህ ጸሎትህ የተወደደ መልካም መዓዛ ያለው ዕጣን ሆኖ ከእግዚአብሐር ዘንድ ይደርስልሃል፤
የፍቅር ፍም አመድ የለውም ፣ በመቀጣጠሉም ምንም ጭስ አይገኝበትም፤
በውስጡ ዘለዓለማዊና ጣፋጭ መዓዛ ያለው መሥዋዕትን ይዞአል፤
ደስ ከሚያሰኙ መሥዋዕቶችም በላይ እጅግ የላቀና የከበረ መሥዋዕት ይህ ነው፤
No comments:
Post a Comment