በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
15/07/2004
መጽሐፍ ቅዱስን ቅዱስ ኤፍሬም እንዴት
መነበብ እንዳለበት ሲያስተምር እንዲህ ይላል፡- “ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በሦስት ዐይነት መንገድ ያነብቡታል፡፡ አንደኞቹ በስሜት
ሆነው የሚያነቡ(with passion) ሲሆኑ የእነዚህ ወገኖች አነባበብ ፀሐይ በተኮሰች ጊዜ ሥር ስላልነበረው ደርቆና ጠውልጎ
ፍሬ ሳያፈራ የቀረውን በጭንጫ መሬት ላይ የተዘራን ዘር ይመስላሉ፡፡(ማቴ.13፡20) ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእነዚህ
ወገኖች እንደገለጠው ለጊዜው መጻሕፍትን አንብበው እውቀትን በመጨበጣቸው ደስ የሚሰኙ ሲሆኑ፤ ነገር ግን በውስጡ ተጽፈው ያሉትን በጎ ምግባራት ለመፈጸም ከብዶአቸው ከማንበብ የተመለሱ ወይም ከንባብ ተሰላችተው ያቆሙ ናቸው፡፡
ሌሎቹ
ደግሞ አዋቂዎች ለመባልና ለመራቀቅ ሲሉ የሚያነቡ ናቸው፡፡ ጉድለት ለማግኘትም ብለው የሚያነቡ አሉ (without
Passion)፡፡ እነዚህ ወገኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ከሌሎች ጋር ሊሟገቱበት እንጂ በውስጡ የያዘውን በጎ ምግባር
ለመተግበር አስበው የሚያነቡ አይደሉም፡፡ ሦስተኞቹ ወገኖች ግን መጽሐፍ ቅዱስን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ሆነው የሚያነቡ ናቸው፡፡
እነዚህ ወገኖች እያንዳንዷን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሔርን በማፍቀር ሆነው የሚያነቡ ናቸው(with Love of God)"ይለናል፡፡
በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡ ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነቡበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እንደተገናኙ በመቁጠር ነው፡፡ እነርሱ እያንዳንዱን ኃይለ ቃል ሲያነቡ እርሱን ከጎናቸው እንደ መምህር በማስቀመጥ ነው፡፡ ስለዚህም ከሚያነቡት ምንባብ ያልገባቸው ኃይለ ቃል ካለ ደጋግመው ያነቡታል ነገር ግን ግልጽ ካልሆነላቸው “ጌታ ሆይ እንዲህ ስትል ምን ማለትህ ነው? ብለው ይጠይቁታል፡፡ የገባቸውና እነርሱ ያልፈጸሙት ከሆነ ደግሞ “ጌታ ሆይ የእኔን የባሪያህን ኃጢአት ይቅር በል፣ ይህን ትእዛዝህን ለመፈጸምም የበቃሁ አድርገኝ”ብለው ይማጸኑታል፡፡ የተደነቁ እንደሆነ ደግሞ “ጌታ ሆይ አንተ ድንቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ይህን ድንቅ የሆነ ምሥጢርህን ስለገለጥክልኝም አመሰግንሃለሁ” ብለው ያመሰግኑታል፡፡
ከቅዱስ ኤፍሬም ጽሑፎችም የምንረዳው ይህንን ነው፡፡ ለምሳሌ ዘፍጥረትን ሲያነብብ የተሰማውን ሲገልጥ፡-
“ጌታ
ሆይ የመጽሐፍህን መግቢያ ባነበብኩ ጊዜ ልቤ በሐሴት ተሞላ፤
በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡ ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነቡበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እንደተገናኙ በመቁጠር ነው፡፡ እነርሱ እያንዳንዱን ኃይለ ቃል ሲያነቡ እርሱን ከጎናቸው እንደ መምህር በማስቀመጥ ነው፡፡ ስለዚህም ከሚያነቡት ምንባብ ያልገባቸው ኃይለ ቃል ካለ ደጋግመው ያነቡታል ነገር ግን ግልጽ ካልሆነላቸው “ጌታ ሆይ እንዲህ ስትል ምን ማለትህ ነው? ብለው ይጠይቁታል፡፡ የገባቸውና እነርሱ ያልፈጸሙት ከሆነ ደግሞ “ጌታ ሆይ የእኔን የባሪያህን ኃጢአት ይቅር በል፣ ይህን ትእዛዝህን ለመፈጸምም የበቃሁ አድርገኝ”ብለው ይማጸኑታል፡፡ የተደነቁ እንደሆነ ደግሞ “ጌታ ሆይ አንተ ድንቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ይህን ድንቅ የሆነ ምሥጢርህን ስለገለጥክልኝም አመሰግንሃለሁ” ብለው ያመሰግኑታል፡፡
ከቅዱስ ኤፍሬም ጽሑፎችም የምንረዳው ይህንን ነው፡፡ ለምሳሌ ዘፍጥረትን ሲያነብብ የተሰማውን ሲገልጥ፡-
የምንባቡ ቁጥሮችና ኃይለ ቃላት እኔን ለመቀበል እጆቻቸውን ዘረጉ፤
ይዘውኝም በፍቅር አቀፉኝ ሳሙኝም ወደ ወዳጃቸውም መርተው አደረሱኝ፡”
ይላል፡፡
እኛም ወገኖቼ ቅዱስ ኤፍሬምን አብነት አድርገን መጽሐፍ ቅዱስን በፍቅር
ወደ ማንበብ እንምጣ፡፡ ለዚህ ጠዋትና ማታ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መርሐ ግብር አዘጋጅቼአለሁ፡፡
ይህን መርሐ ግብር በ1937 ዓ.ም ገደማ ከተዘጋጀ መጽሐፍ አግኝቼ ትንሽ ማሻሻያዎችን ጨምሬበት ያዘጋጀሁት ነው፡፡ ወደፊትም በየወሩ የሚነበቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አዘጋጅቼ አቀርብላችኋለሁ፡፡
ወደ ቅዱስ ኤፍሬም የንባብ ልምድ ቀስ በቀስ ስንመጣ ስንበላም ሆነ
ስንተኛ፣ ስንቀመጥም ሆነ ስንቆም፣ ከሰው ጋርም ሆንን ብቻችንን፤ ሁልጊዜም በጸሎት ውስጥ እንሆናለን፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊትም “ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም”
(መዝ.15፡8)ወደ ማለትም እንመጣለን፡፡
ወደዚህ የሕይወት ከፍታ እንድትመጡ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ ብቻ የሚያገለግል አንድ
ዳይሪ(የግል ማስታወሻ) ታዘጋጃላችሁ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችሁን በጸሎት በመጀመር የዕለቱን ምንባብ ታነባላችሁ፡፡ በመቀጠል ከንባቡ
የተማራችሁትን፣ የተደነቃችሁበትን፣ የተገሠጻችሁበትን፣ ያልገባችሁን፣ እንዲሆንላችሁ የምትመኙትን ሁሉ በጸሎት ከምስጋና ጋር በግል ማስታወሻችሁ ታሰፍሩታላችሁ፡፡
ጽፋችሁ ካበቃችሁ በኋላ በድጋሚ አንዴ የጻፋችሁትን ታነቡታላችሁ፡፡ በዚህ መልክ
ለሳምንት እንዲህ አድርጋችሁ ከቆያችሁ በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የጻፈችሁትን ድጋሚ ትመለከቱታላችሁ፡፡
በዚያን ጊዜ በእውነት እኔ ነኝን ይህ የጻፍኩት? በማለት በራሳችሁ ትገረማለችሁ፡፡ ይህን ሁል ጊዜ ጠዋትና ማታ ታደርጉታላችሁ፡፡
በጸሎታችሁ ግን እኔን ኃጥኡን ገብረ ኢየሱስን አስቡኝ፤ መልካም የንባብ ሳምንት ይሁንላችሁ፡፡
የዕለታት
ምንባብ
ለመስከረም
ወር የወጣ ፕሮግራም
በዚህ ወር ውስጥ ዘፍጥረትን፣ ማቴዎስን፣ ማርቆስን፣ የሐዋርያት ሥራን፣ ሮሜን፣ ይጨርሳሉ፡፡ ዘፀአትን፣ ሉቃስን፣ 1ኛ ቆሮንቶስን ይጀምራሉ
የጠዋት ምንባብ
|
የማታ ምንባብ
|
||||||
የቀን ቀጥር
|
ከብሉይ ኪዳን
|
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
|
ከወንጌል
|
የቀን ቁጥር
|
ከብሉይ ኪዳን
|
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
|
ከወንጌል
|
1
|
ኢሳ.61፡1-6
|
ዕብ.3፡1-19፤
|
ሉቃ.4፡16-27
|
1
|
ዘፍ.1
|
የሐዋ.1
|
ማቴ.1
|
2
|
ሚክ.3 በሙሉ
|
ዕብ፡ 11፡1-19
|
ማቴ.14፡1-11
|
2
|
ዘፍ.2
|
የሐዋ.2፡1-21
|
ማቴ.2
|
3
|
ዘፍ.3
|
የሐዋ.2፡22-47
|
ማቴ.3
|
3
|
ዘፍ.4
|
የሐዋ.3
|
ማቴ.4
|
4
|
ዘፍ.5
|
የሐዋ.4
|
ማቴ.5
|
4
|
ዘፍ.6
|
የሐዋ.5፡1-16
|
ማቴ.6
|
5
|
ዘፍ.7
|
የሐዋ.5፡17-42
|
ማቴ.6
|
5
|
ዘፍ.8
|
የሐዋ.6
|
ማቴ.8
|
6
|
ዘፍ.9 እና 10
|
የሐዋ.7፡1-39
|
ማቴ.9
|
6
|
ዘፍ.11 እና 12
|
የሐዋ.7፡35-60
|
ማቴ.10
|
7
|
ዘፍ.13
|
የሐዋ.8፡1-25
|
ማቴ.11
|
7
|
ዘፍ.14
|
የሐዋ.8፡26-40
|
ማቴ.12፡1-37
|
8
|
ኤር.26፡12-16
|
ዕብ፡7፡19-27
|
ማቴ.23፡34-39
|
8
|
ዘፍ.15
|
የሐዋ.9
|
ማቴ.12፡38-50
|
9
|
ዘፍ.16
|
የሐዋ.10፡1-29
|
ማቴ.13፡1-30
|
9
|
ዘፍ.17
|
የሐዋ.10፡30-48
|
ማቴ.13፡31-58
|
10
|
ዘፍ.18
|
የሐዋ.11
|
ማቴ.14
|
10
|
ዘፍ.19
|
የሐዋ.12
|
ማቴ.15፡1-20
|
11
|
ዘፍ.20
|
የሐዋ.13፡1-15
|
ማቴ.15፡21-39
|
11
|
ዘፍ.21
|
የሐዋ.13፡16-52
|
ማቴ.16
|
12
|
ዘፍ.22
|
የሐዋ.14
|
ማቴ.17
|
12
|
ዘፍ.23
|
የሐዋ.15፡1-12
|
ማቴ.18
|
13
|
ዘፍ.24
|
የሐዋ.15፡13-41
|
ማቴ.19፡1-15
|
13
|
ዘፍ.25
|
የሐዋ.16፡1-15
|
ማቴ.19፡16-30
|
14
|
ዘፍ.26
|
የሐዋ.17
|
ማቴ.20፡1-19
|
14
|
ዘፍ.27
|
የሐዋ.18
|
ማቴ.20፡20-34
|
15
|
ዘፍ.28
|
የሐዋ.19፡1-20
|
ማቴ.21፡1-32
|
15
|
ዘፍ.29
|
የሐዋ.19፡21-40
|
ማቴ.21፡33-46
|
16
|
ዘፍ.31
|
የሐዋ.21፡1-16
|
ማቴ.23
|
16
|
ዘፍ.30
|
የሐዋ.20
|
ማቴ›22
|
17
|
ዕንባ.2፡1-17
|
1ቆሮ.1፡14-24
|
ማቴ.27፡32-37
|
17
|
ዘፍ.32
|
የሐዋ.21፡17-40
|
ማቴ.24፡1-35
|
18
|
ዘፍ.33
|
የሐዋ.22
|
ማቴ.24፡36-51
|
18
|
ዘፍ.34
|
የሐዋ.23
|
ማቴ.25፡1-30
|
19
|
ዘፍ.35
|
የሐዋ.24
|
ማቴ.25፡31-46
|
19
|
ዘፍ.36
|
የሐዋ.25
|
ማቴ.26፡1-47
|
20
|
ዘፍ.37
|
የሐዋ.26
|
ማቴ.26፡47-75
|
20
|
ዘፍ.39
|
የሐዋ.27
|
ማቴ.28
|
21
|
ዘፍ.40
|
የሐዋ.28
|
ማር.1
|
21
|
ዘፍ.41
|
ሮሜ.1
|
ማር.2
|
22
|
ዘፍ.42
|
ሮሜ.2
|
ማር.3
|
22
|
ዘፍ.43
|
ሮሜ.3
|
ማር.4
|
23
|
ዘፍ.44
|
ሮሜ.4
|
ማር.5
|
23
|
ዘፍ.45
|
ሮሜ.5
|
ማር.6
|
24
|
ዘፍ.46
|
ሮሜ.6
|
ማር.7
|
24
|
ዘፍ.47
|
ሮሜ.7
|
ማር.8
|
25
|
ዘፍ.48
|
ሮሜ.8፡1-17
|
ማር.9፡1-32
|
25
|
ዘፍ.49
|
ሮሜ.8፡18-39
|
ማር.9፡33-50
|
26
|
ዘፍ.50
|
ሮሜ.9
|
ማር.10
|
26
|
ዘፀአ.1
|
ሮሜ.10
|
ማር.11
|
27
|
ዘፀአ.2
|
ሮሜ.11
|
ማር.12
|
27
|
ዘፀአ.3
|
ሮሜ.12
|
ማር.13
|
28
|
ዘፀአ.4
|
ሮሜ.13
|
ማር.14
|
28
|
ዘፀአ.5
|
ሮሜ.14
|
ማር.15
|
29
|
ዘፀአ.6
|
ሮሜ.15
|
ማር.16
|
29
|
ዘፀአ.7
|
ሮሜ.16
|
ሉቃ.1፡1-38
|
30
|
ዘፀአ.8
|
1ቆሮ.1
|
ሉቃ.1፡39-80
|
30
|
ዘፀአ.9
|
1ቆሮ.2
|
ሉቃ.2
|
የቅዱስ ኤፍሬምን አነባበብ ስልት ስንከተል ግን እንደሱም ጸሎቱን በሚገባው እያደረስንው መሆን ይኖርበታል፡፡ ''ግልጽ ካልሆነላቸው “ጌታ ሆይ እንዲህ ስትል ምን ማለትህ ነው? ብለው ይጠይቁታል” ከዚህም በላይ ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን በተለይ እንደ አባታችን ባኮስ “የሚረዳኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል” የምንልና ያልገባንን ጽፈን ቁጭ ሳይሆን ወይም ያልሆነ ዝርው መረዳት ውስጥ እንዳንገባ ወደ መምህራን ቀርበን ልንጠይቅ ያስፈልጋል፡፡
ReplyDeleteቅዱስ ኤፍሬም በየትኛው መጽሃፉ/ትምህርቱ/ ላይ እንደመከረን ምንጭ ብትጠቅስልንም ጥሩ ነው፡፡
ወንድሜ ሆይ በመጀመሪያ ላነሣህልኝ ጥሩ ሃሳብ ከልብ አመሰግንሃለሁ፡፡ እንደምትረዳውና አንተም እንደምታውቀው ባኮስ አስቀድሞ ትንቢተ ኢሳይያስን ሲያነብብ ነበር፡፡ መጽሐፉን የመረዳት ፍላጎቱን የተረዳ እግዚአብሔር አምላክ ስለሚያነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማብራሪያ ይሰጠው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሱ ፊልጶስን ልኮለታል፡፡ ባኮስ በውስጡ ጥያቄው መፈጠሩንና ነቢዩ ስለምን እየጻፈ እንደሆነ ለአምላኩም ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበር ለመረዳት “እባክህ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? የሚለውን ጥያቄውን ማስተዋል እንችላለን፡፡ ይህ ምንን ያስረዳናል የኢሳያይስን የትንቢት መጽሐፍ በሚያነበብት ጊዜ ይህ የንባብ ክፍል በውስጡ ጥያቄን እንደፈጠረበት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በውስጡ የተፈጠረበትን ጥያቄ ይመልስለት ዘንድ ፊልጶስን ላከለት እርሱም አብራርቶ ገለጠለት፡፡ ወንድሜ ሆይ ባኮስ በውስጡ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ባይፈጠርበትና በእርሱም ዘንድ ምሥጢሩን ለመረዳት መሻቱ ባይኖር ኖሮ እግዚአብሔርም መልእክተኛውን ፊልጶስን ባላከለት ነበር፡፡ ሌላውና ሊታሰበብት የሚገባው ጉዳይ ወንድሜ ሆይ እኛና ባኮስ የምንነጻጸር አይደለንም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ገና ሳይጠመቅና እውነትን የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ በሰውነቱ ሳያድር በፊት ነበር “በእውን የምታነበውን ታስተውለዋለህ” ብሎ ፊልጶስ በጠየቀው ጊዜ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? ብሎ የመለሰለት ፡፡ በእርግጥም ምሥጢርን የሚገልጥ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ሳያድርበት እንዴት ነው በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈን መጽሐፍ ሊረዳ የሚችለው? እንዲህም ሲባል ሁሉን መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ይገልጥልናል ማለት ሳይሆን እንደባኮስ ጠቅላላውን አይሁን እንጂ ከመምህራን ጠይቀን በእነርሱም ላይ ባደረው መንፈስ ቅዱስ መልሱን ልናገኝ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ይህን ከራሱ ከባኮስ ሕይወት መማር እንችላለን፡፡ እርሱ ከተጠመቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌልን በኢትዮጵያ ምድር የሰበከው ሰው ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን መምህራን አያስፈልጉም እያልኩ እንዳልሆነ ልብ ይደረግልኝ፡፡ እውቀቱን ከመምህራን ማግኘት ካለብን ወደ እነርሱ በምክንያት ይመራናል ወይም ልክ እንደባኮስ ወደእኛ ያቀርባቸዋል፡፡ ሌላኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስንመለከት መልሱን ከዚያው እናገኘው እንችላለን፡፡ ለሁሉም ግን ይህን ከልቤ አመንጭቼ የጻፍኩት እንዳልሆነ ትረዳኝ ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ መጽሐፍ ቅዱስን ስለማንበብ የጻፈውን በእንግሊዘኛው እንዳለ ከታች ጽፌልሃለሁ፡፡ “… let us not be satisfied with arriving speedily at the gate, but rather let us knock hard, so that the door of the bridal chamber may be opened to us and we may behold the beauties within. Now, the gate is the letter, but the bridal chamber within the gate is the beauty of the thoughts hidden behind the letter, which is to say, the spirit of truth. Let us knock hard, let us read once, twice, many times. By thus digging through we shall find the treasure of knowledge and take delight in the wealth of it. Let us seek, let us search, let us examine, and let us inquire. “for every one that asks receives: and he that seeks, find: to him that knocks, it shall be opened;”(Matt.7:8) and `Ask your father, and he will declare to you: your elders in knowledge and they will tell you.(Deut.32:7)….(Selected writings of St. John the Damascus Page. 7-10 ) ቀሪውን አንተ መጽሐፉን አግኝተህ አንብበው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በየትኛው መጽሐፉ ላይ ነው እንዲያ ብሎ የጻፈው ላልከኝ፡፡ Kees den Biesen የሚባል ጸሐፊ Simple and bold: Epherm’s art of symbolic thought በሚለው መጽሐፉ ላይ Page 47-49 አስፍሮት ታገኛለህ፡፡ በዚህ ላይ ግን እኔ እንደጻፍኩት አድርጎ ሳይሆን ያቀረበው ቅዱስ ኤፍሬም መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብብ እንዲህ ነው በማለት ነው የሚገልጠው፡፡ ጠቅላላውን ከመጽሐፉ ማግኘት ትችላለህ እኔ ግን ሳቀርበው ለአንባቢ በሚገባ መልኩ ማለት በውርስ ትርጉም ሥልት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ
DeleteEgziabhere yestelene wondimachen betam des yemil new yakerbekelelen tsehufe.
ReplyDeleteHow can i get the rest months to read the Holy Bible?
already the next part is ready. I will post it soon. but read constantly and contineuly. The bible is wrote for orthodox christian who recieved Holy Spirit in baptism.
Delete