በዲ/ን
ሽመልስ መርጊያ
05/12/2004
(እነዚህ ጽሑፎች በተለያዩ ጊዜአት ፖስት ያደረጉኋቸው ናቸው)
ክርስትናና ፍቅር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች
ፍቅርን የማያውቃት ክርስትናንም አያውቃትም ፡፡ ፍቅርን ሳያውቃት ክርስትናን አውቃታለሁ የሚል ሰው በእውነት እርሱ ሐሰተኛ ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ ላለ ሰው ክርስትና ትፈቀራለች እንጂ አትከብድም፡፡ ክርስትና በፍቅር ውስጥ በሚገኝ ማስተዋል የምትመራ፣ የማታሰለች፣ ሁሌም ጥበበኛ የሆነች፣ ርኅሪት፣ ታጋሽ፣ አዛኝ፣ ሰው በሰው ማንነት ውስጥ ሆኖ ሰውነቱን እንዲያጣጥም የምትረዳ፣ ውስጡዋ ሰላም፣ ፍስሐ፣ ፍጹም ፍቅር የሞላባት፣ በተመስጦ የምታኖር የሰው ሰውነት ትርጉም ናት፡፡So let's build our faith on
these, let's open our eyes with love and see all human beings with kindness. Don’t
judge on others but appreciate their good deeds. Help each other without
reward. In order to have pure mind, excellent thinking and healthy perspective,
let us know God our lover and love all human beings on the eyes of God and love
each other sincerely. Not in word but in deed.
ብሔርተኝነት
ፈላስፎቻችን ምን ነካቸው?
እናንተየ
አንድ ግርም የሚለኝ ነገር አለ፡፡
ኢትዮጵያዊያን ፈላስፎች ነን የምትሉ ቆይ ፍልስፍና
ማለት እግዚአብሔርን መቃወም ማለት ነው ያላችሁ
ማን ነው? እኔ እንደሚገባኝና ዓለምም
እንደሚመሠክረው ፍልስፍና ማለት እውነትን መፈለግ ማለት ነው፡፡
ወይም ሲብራራ እውነትን ከሕሊና ጋር የሚስማሙ አስረጂ ምክንያቶችን በማቅረብ አስረግጦ ማስረዳት መናገር ብሎም በእርሱ
የሕይወት ግብን ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡
ከዚህ የወጣ ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ እንዲያ ከሆነ እግዚአብሔር
ስለመኖሩና ስለአለመኖሩ ሕሊናን የሚማርክ በቂና አስረጂ ምክንያትን ሳያስቀምጥ እንዴት እግዚአብሔር የለም ብሎ
በጭፍን ከፍልስፍና ዲሲፕሊን ውጪ በሆነ መንገድ
አፍ ይከፈታል?
ለመሆኑ እንዲህ ብሎ የሚናገረው ወገኔ እርሱ
ስለተገኘበት ማኅፀን ክፉና ደጉን እስከሚያቅባት እድሜው
ድረስ እውቀቱ ነበረውን? የወጣበትን ማኅፀን ያልተረዳ እንዴት ከማኅፀን ሳለ የሠራውን አምላክ ተረድቶ እርሱን ለመቃወም ይነሣል? ፈላስፋ ሊሆን የሚወድ
ሰው ካለ መጀመሪያ እኔ ከየት
መጣው ብሎ ራሱን ይጠይቅ?ፍልስፍና የሚጀምረው ከራስ ነውና፡፡ የራሱን ከየት መጣነት
ሲጠየቅ ይህ ሰው ከእናቴ
ከአባቴ በተለይ ከእናቴ ብሎ ሊመልስ ይችላል፡፡ እናቱ ማኅፀን
ሳለስ እናቱ ትሆን መላ
አካሉን ፈጥራ ሰው ያደረገችው?
ይህንን ጥያቄ እኔ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ
ነኝ የሚለው ሰው ለእናቱ ያቅርብላት፡፡ ከዛም ወደ
ፍልስፍናው ይግባ በቃ ስለራሱ
አመጣጥ በቅጡ የማያውቅ እንዴት ፈላስፋ ይባል ዘንድ
ብቻ እግዚአብሔርን ለመናገር መንጋጋውን ያላቅቃል? ጉድ እኮ ነው
ጎበዝ!!!!
ይኼን ነው መሸሽ
ሰው ወዶህ ከእግዚአብሔር ጋር በጠብ ብትኖር ጥቂት ጊዜ ሰላም ይኖርህ ይሆናል ቢሆንም አኗኗርህ እንደውሻ የተጠላ ነው፡፡ ነገር ግን ከሞተው አንበሳ ይልቅ የንስሐ ጊዜ አለህና ተስፋ አለህ፡፡ ሰው ጠልቶ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር ብትሆን እንደሙሴ አንተን ሊያጠቁ ከተነሡ የበግ ለምድ ከለበሱ የተኩላ መንጋ አንተን ይታደግሃልና አትፍራ፡፡ በእጅጉ የሚያሳዝነው ግን ሰውም ጠልቶህ ከእግዚአብሔር ጋርም በጠብ ያለህ እንደሆነ ነው፡፡ እንዲህ ዐይነት ሰው ከሆንኽ በሕይወት ካለው ውሻ ይልቅ ጎስቋላ ስትሆን እጣ ፈንታህም ከሞተው አንበሳ ጋር ይሆናል፡፡ ለእንዲህ ያለ ሰው ምን ይባላል ጃል?
የአምባገነኖች ፍጻሜ
አንድ አምባገነን መሪ ሞቶ ከርሱ ቀድሞ የሞተው አንዱ ከሌሎች መሰል አምባገነኖች ጋር በመሆን እንዲህ ብሎ በሲኦል አቀባበል አደረገለት ይባላል፡-“ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች የሞቱትንም የምድርን ታላላቆች ለአንተ አንቀሳቀሰች ….. አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፤ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል፡፡ .. በውኑ ምድሪቱን ያንቀጠቀጠ (መንግሥቱንም) ያናወጠ ዓለሙን ባድማ ያደረገ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርኮኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ … ምድርን አጥፍተሃታልና ሕዝብህን ገድለሃልና ከእነርሱም ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም የክፉዎች ዘር ለዘለዓለም የተጠራ አይሆንም፡፡ …. ስምንና ቅሬታን ዘርንና ትውልድንም እቆርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር” (ኢሳ. 14፡10-23)
ሥጋንና ሴትን ማሳነስ ከክርስትና ለመሸሽ
አንድ
ነገር ግርም ይለኛል፡፡ እግዚአብሔር ለኖህ “የሰውን ደም የሚያፈስስ
ሁሉ ደሙ ይፈስሳል ሰውን በእግዚአብሔር መልክ
ፈጥሮታልና” (ዘፍ.9፡6)ብሎ
ተናገረ፡፡ ለመሆኑ ግን እግዚአብሔር የቱን ነው
የእግዚአብሔር መልክ ያለው? ሥጋችንን አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ይህን
አካል መልሶ መቅደስም ይለዋል “ማንም የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስን ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው
ያውም እናንተ ናችሁ”፡፡(1ቆሮ.3፡17)
ጌታችንም ከቅድስት እናታችን የነሣውን ሰውነት መቅደስ ብሎታል፡፡“ይህን ቤተ መቅደስ
አፍርሱት በሦስተኛው ቀንም አነሣዋለሁ”(ዮሐ.2፡19) እንዲያ ከሆነ በእውን የምትሞትና የምትፈርስ ተፈጥሮ ያላት ነፍሳችን ናትን? ወይስ
ሥጋችን? ሥጋችን ካልሆነች ማን ሊሆን ይችላል?
ስለዚህም ሥጋችን በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥራለች፤ በትክክልም አምላኩዋን ትመስላለች፡፡ እውነታው እንዲህ ሆኖ ሳለ አንድ እጅግ መጥፎ ጽንሰ
አሳብ ወደ ሕሊናችን ተጨምሮ ጎስቋሎች ሆነናል፡፡ በእርግጥ ሥጋችንን እንደ ርኩስ
ማየት ከየት እንደመጣ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን
ሥጋን አንኳሶ ለሚመለከት ሰው አንድ ጥያቄ
አለኝ፤ በእውነት ጌታችን ሥጋችንን በመልበስ አላከበራትምን? አምላክን ወደምትመስለበት መልኩዋ አልመለሳትምን? ጌታችንስ እንበላውና እንጠጣው ዘንድ የሰጠን ከእኛ የነሣውን
ሥጋና ደም አይደለምን? ነፍስስ በሥጋ ምክንያት
አልዳነችምን? ታዲያ ሥጋን ርኩስ
አድርገው እንደሚመለከቱት ማኒዎች የሆነ ትምህርትን ስለምን እንቀበላለን? የሚደንቀው ግን የሥጋን
ርኩስነት የሰበኩን ጎረቤቶቻችን የእኛን ቤተሰባዊ ሥሪት አበላሽተውና አጎስቁለው እነርሱ በምቾትና በደኅንነት መኖራቸው ነው፡፡ አይ ሞኝነታችን
እስካሁንም ከእነርሱ ትምህርት አለወጣንም፤ ይገርማል!!! የሚደንቀው ደግሞ እነዚህ ወገኖች በሥጋና በሴት ልጅ
ከብረው ሳለ እነርሱን አንኳሰውና አሳንሰው መመልከታቸው ነው!!! እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!!
የሕሊና
እስረኛው
ከእምነት
ውጪ የሆነ ሰው ይህ
ማለት ግን እምነት የለውም ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም “የለኝም”
የሚለው አስተሳሰቡ በራሱ እንደ አምላክ
ይገዛዋልና፤ እርሱ የሚያሳዝን የሕሊና እስረኛ ነው፡፡ ሰው ያለ ሃይማኖት
ሊኖር አይችልም፡፡ እንደውም ሰውን ሰው ያደረገው
እምነት ነው ቢባል ሐሰት
አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ሰው የሚዳኘው
በምድራዊውና በሕሊናው ውስጥ እግዚአብሔር በሠራለት ሕግ ነው፡፡
ነገር ግን እነዚህ ሕግጋት
ለእርሱ እንደ እስር ቤት
ስለሚሆኑበትና ሰዋዊ ባሕርይውን የሚሞሉለት ሆነው ስለማያገኛቸው ደስታ
የራቀው ሰው ሆኖ በሕይወቱ
ተሰላችቶ ይኖራል፡፡ ስለዚህም ከምንም በላይ ፍቅርን ይሻል፡፡ በፍቅር ወደእግዚአብሔር አምልኮ ማምጣት ይቻላል፡፡ ከላይ የገለጥናቸው
ሕግጋት ሰውን ወደሚበልጠው መንፈሳዊ ከፍታ ወይም
በጸጋ አምላክ ወደ መሆን የሚያደርሱ
መሰላሎች ናቸው፡፡ ይህ ነው የሰው
ተፈጥሮአዊ ጠባዩ፡፡ ነገር ግን በእነዚህ
ውስጥ ብቻ መመላለስ የሚወድ ወይም በእነዚህ
ሕግጋት ብቻ የሚኖር ሰው በመንፈሳዊ
እይታ እንደ ሕጻን ነው፤
ይህ ማለት ከሕግ በታች
እንጂ ከጸጋ በታች አይደለም፡፡
The ladder of the Kingdom of God
“The ladder of the Kingdom is within you, hidden in your soul. Plunge
deeply within yourself,(praying and reading bible deeply) away from sin.(which
destorts your meaning of life)Then inside your soul you will find steps by
which you will be able to ascend.”(St. Isaac the Syrian) all bible parts are
tell about you and christ. This is the true fact.
ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ኦርቶዶክሳዊነት አይታሰብም
መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ምክንያቱም የጽሑፉ ባለቤት እርሱ ነውና፡፡ መንፈሱ የሌለው ሰው መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት አይቻለውም፡፡ ምክንያቱ የመጽሐፉ ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ አላደረምና፡፡ የሚደንቀው ግን መንፈሱ አለን በውስጣችንም መንፈስ ቅዱስ አድሮአል የምንል አብዛኛዎቻችን ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን የማናቅ መሆናችን ነው፡፡ ነገር ግን የኦርቶዶክስ አስተምህሮ ማዕከሉና ሥሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት የማያደርግ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የኦርቶዶክስን እምነት አስተምህሮ አገኛለሁ ቢል በእውነት እየቀለደ ነው፡፡
The worst sin
It is very truth, especially in Ethiopia; Most of us are fault
finders. Not in Ethiopia only, but also all Christian religious sects are
practice this dirt game. They search the fault of their fathers, brothers,
mothers, sisters, not their strength. I know where it spring, but not from
poverty, nor from illiteracy. We are the other side of our neighbor country's
Dogmatic minded personality. Not only us but also all Christian sects are
involved in it. It is highly practices in Catholic Church. However, we also
focus only in Dogmatic Views not in moral. So we became fault finders. We
search the weakness of our body or relatives in Christ, and then we cruelly
judged upon them. Our eyes are blinded by this, but if you question me how? Search
your ground of thought. We will not show our weakness but we judge on others. I
believe Dogma is very necessary; however, equally we must focus on Moral also.
if we flow our God Jesus Christ foot step and the teaching of apostles we know
what moral is looks like.
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
የዚህን ዓለም መከራስ ክርስቶስም ተቀብሎታልና ብቸገር ክርስቶስን መሰልኩ እንጂ የተዋረድኩና የተናቅሁ አልሆንም፡፡ ነገር ግን ከመንግሥቱ ከቅዱሳን ኅብረት ከሚለይ በዚህም ዓለምም ከሰው ከሚያሳንስና ከሚያዋርድ ኃጢአት ይልቁኑ ቅዱስ ዳዊት እንዳለው ከተሰወረና ከድፍረት ኃጢአት ያድነን ዘንድ ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ አባቱም እናቱም ሆነሽ ያሳደግሽው ድንግል ሆይ ለምኝልን፡፡ የዚህን ዓለም መከራ ስልም እጅግም ሳይመቸኝ እጅግም ሳልደኸይ ማለቴ ነው፡፡ ይህም ሕይወት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የኖረውን ዓይነት ሕይወት የሚመስል ነው፡፡ ይህን ሕይወት ይሰጠኝና ገጸ ረድኤቱን ከእኔ እንዳያርቅ ቅድስት ሆይ ለምኝልኝ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማለት የቅዱሳን ኅብረት ማለት ነው፡፡ እናም ከቅዱሳን ነፍሳትም ጋር አንድ ቤተሰብ ሆነናልና ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል እንዲጨነቅና እንዲያስብ መልካምንም ሁሉ እንዲያደርግለት ቅድስት ሆይ እኛ በክርስቶስ ልጆችሽ ነንና ስለእኛ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢልን!!!
በሕግ አምላክ
“መለያየትን የሚወደድ ምኞቱን ይከተላል፡፡ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል” ይላል ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡(ምሳ.18፡1)
በምኞት ፈረስ ተቀምጦ በምኞት ብቻ ሊያጠግበን የሚመኝ የወሬ አቁማዳ እኛን እኮ ሥራ ፈት አደረግን ጃል!!! ክርስትና ማለት እኮ ክርስቶስ ማለት ናት!!! አሁን ክርስቶስን ማየት እንጂ ስለክርስቶስ መስማትን አልፈቅድም፡፡ወይም በቃል ሳይሆን በተግባር ክርስቶስን በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ ነው ማየት የምፈልገው፡፡ ማንም ምኞቱን በአእምሮዬ ሊጠቀጥቅ አልፈልግም በቃኝ፡፡ አንጀቴ እርሱ አምላኬን ናፍቆና ተርቦ፣ ሆዴ ከአጥንቴ ተጣብቆ ምግብ የማይሆነኝን ምኞቱን ሊሞላኝ ልዩነትን ሽቶ የሚተጋን ሰው ነፍሴ ተጸይፋዋለች፡፡ እረ ባክህ አንተ ልዩነትን የምትዘራ የሰይጣን ቅጥረኛ ድምፅህን መስማት አልሻምና አፍህን ከማላወስህ በፊት እባክህ ከእኔ ራቅ፡፡ በቃ አበቃሁ አልፈልግም!!!
አንገቴን ደፋሁ
ሰው እብድ ካልሆነ በቀር የራሱን አካል በሴንጢ እየጎረደ አይበላም፡፡ እኛ ግን በጥምቀት አንድ አካል ሆነን ካበቃን በኋላ ዐይን እግርን ያሰናክላል፡፡ እጅም የገዛ ዐይኑን ያፈርጣል፡፡ አፍንጫም ለሰውነት ክፉ የጥፋት ጠረንን ይመግባል፡፡ እግርም ሰውነትን ወደክፋት ይመራል፡፡በጠቅላላው አካላቱ ከገዛ አካላቸው ጋር በጠብ እየተኗኗሩ ነው፡፡ ግን በዚህ ጠብ ማን ይጠቀማል? ዐይን ወይስ እጅ ወይስ እግር ወይስ ሌላው ? በቤተ ክርስቲያናችንም እየሆነ ያለው ይህ ነው፤ አንዱ አንዱን ለማጠፋት ተሰልፎአል፤ እጅግ እጅግ እጅግ ከባድ ዘመን ውስጥ ደርሰናል ኦ
ኦ ኦ …
ምነው ፍቅርና እርቅ ቢሰበክ?
እኛ
ማንን እንደምንመስልና መምሰል እንዲገባን ሊያስተምረን እግዚአብሔር አምላክ አንድያ ልጁን ክርስቶስን በሥጋ እንድናየው
አደረገን፡፡ በእርሱ ትክክለኛውን መልካችንንና ባሕርያችንን እናየዋለን፡፡ ብዙዎች ቅዱሳን ክርስቶስን መስለው ፍቅርን ሰብከው አለፉ፡፡ አሁን ግን በኢትዮጵያችን እንደ
ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስን የመሰለ ሰው አልተገኘም፡፡ስለዚህም ክርስትናን እንደገና ልንጀምር እየተገደድን እንገኛለን፡፡ እርሱን ክርስቶስን በቀጥታ ለመመልከት ልክ እንደ
ጳውሎስ ቀና ብለን ልናይ
ይገባናል እንጂ በብዙ ስህተቶች
የታጠረውን፣ መንገዱ የጠፋበትን ሰው ስለምን እንመከታለን፡፡ ኢሳይያስ የአንድ ቤተሰብን ታሪክ ይነግረናል፡፡ “ሰውም”
አለና “በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን
ይዞ አንተ ልብስ አለህ
አለቃም ሁንልን፤ ይህችም ባድማ ከእጅህ በታች ትሁን፤
ሲለው በዚያ ቀን ጽምፁን
ከፍ አድርጎ እኔ በቤቴ ውስጥ
እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና
ባለ መድኀኒት አልሆንም በሕዝቡም ላይ አለቃ አታድርጉኝ
ይላል፡፡”(ኢሳ.3፡6)ይህ
ሰው ሹመት ጠልቶ ሳይሆን
ለሹመቱ የሚያበቃው እውቀቱ ስላልነበር ነበር እንዲህ ማለቱ፡፡ ይህም ዘመን
እንዲሁ ነው፡፡ ከሰማያዊው እውቀት ስለራቅን ወደ ቀድሞ ገዢያችን
ተመልሰናል፡፡ስለዚህም እንደ አውሬ አንዱ
በአንዱ ላይ ተነስቶአል፡፡ በጎች መሆናችን
ቀርቶ ተኩላዎች ስለሆንን የወንድማችንን ሥጋ ለመበጫጨቅ የብዕር ክራንቻችንን አሹለናል፡፡የጥፋት የብዕር ጥፍራችንም ከመቼውም ይልቅ አስለነዋል፡፡ እንደ
ርግብ የዋሃ የሆነው ማኅበረሰባችንን አንቀን ከደሙ ለመርካት
ተክለፍልፈናል፡፡ ማስተዋል ጎድሎናል፡፡ ጽንፍ ይዘን እንደበግና
እንደ ርግብ የሆነውን ማኅበረሰብ ለመቀራመት እርስ በእርሳችን
ተፋጥጠናል፡፡እነዚህ ጽንፈኞች ግን ሳያውቁት ወይም አውቀም
ሰውን በመለያየት ለሚገዛው ሰይጣን ባሮች ሆኑ እንጂ
አንዳች ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ይህ ቃል
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የሚሰተዋለው ግን መች ነው“እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርሱ በርሳችሁ
እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ”(ገላ.5፡15) ምነው
ፍቅርና እርቅ ቢሰበክ፤ ምነው ጽንፍ
ይዘን እኛ ተኩላዎች በመሆን በግ የሆነው
ይህ ምዕመን ደንብሮ ከተኩላዎች ጎሬ እንዳይገባ ብንስማማ !!! ምነው ግን
ምነው?
በእውን ይህ ይሆናል?
በእውን አምላካችን እኛን ጨክኖ ወደ ሲኦል ይጥለን ይሆንን? እንጃ እኔ ግን አይመስለኝም፡፡ እኛ ፈቅደን ራሳችንን ካልጣልን በቀር፡፡ ጌታችን ስለኢየሩሳሌም “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ … ዶሮ ጫጩቶቹዋን ከክንፎቹዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ አልወደዳችሁም”(ማቴ.23፡37)እንዳለው የእኛ ምርጫ እንጂ እርሱስ ወደ ሲኦል አይጥለንም፡፡ እንዴት አባት ልጁን ወደ እሳት ጨክኖ ሊጥለው ይችላል?
በሰባኪያን ይህ ቢስተዋል
ሰው በውስጥም በውጪም በሚታየውም በማይታየውም ባሕርይው አምላኩን ስለሚመስል ከመላእክት ንግግር ይልቅ የፈጣሪውን ቃል በትክክል ያውቀዋል ይለየዋል ይወደዋል፡፡ ችግሩ የመጣው ከእኛው ከሰባኪያኑ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ፍቅር ይገዛዋል፡ትሕትና ያሸንፈዋል፡፡ እነዚህ ደግሞ ዋነኞቹ የእግዚአብሔር መገለጫ ባሕርያቶቹ ናቸው፡፡ ራሳችንን እናስተካክል ፍቅር የሆነው የሰው ፍጥረት ሁሉ አምላኩን ይናፍቃል መንገዱን አንዝጋበት፡፡
The invitation of holy angels
"Did you see that they minister (angels) to us on God's behalf, and that they minister to us in the greatest matters? Wherefore Paul Says "All things are yours, whether life of death, or the world, or things present, or things to come"(1cor.3:20)
"Did you see that they minister (angels) to us on God's behalf, and that they minister to us in the greatest matters? Wherefore Paul Says "All things are yours, whether life of death, or the world, or things present, or things to come"(1cor.3:20)
For Christ stands at the door of your soul, hear Him
speaking, "Behold I stand at the door and knock: if anyone open to me, I
will come in to him and I will sup with him and he with me"(Rev.3:20)...
He stands -then but not alone, for before Him go the angles saying: "Lift
up the gates, O you, the princes," what gates? Even those of which the
Psalmist sings, in another place also "Open to me the gates of
righteousness." Open then the gates of righteousness, the gates of
chastity, the gates of courage and wisdom. (John Chrysostom)
ዘመናዊው ጣዖት
አንድ
ሁላችን ልናውቀው የሚገባ ነገር አለ፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን ባለማወቅ የሚኖር፣ ፖለቲካው ሃይማኖቱ የሆነ የምዕራባዊያንና የአሜሪካ
ፕሮፌሰሮች የሃይማኖት መሪዎቹ የሆኑለት ትውልድ በትክክል ግብረ ሰዶማዊ መሆኑ ወይም
ለዚህ የተጋለጠ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምዕራባዊያንና የአሜሪካ
መንግሥት ለግበረ ሰዶማዊነት እውቅና እየሰጡት ይገኛሉ፡፡ በአገራችም በየምሽት ዳንስ ቤቶች አደንዛዥ
ዕፅን በመጠቀም እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች፣ በተለይ የግል በተለየ ደግሞ ጾታ
ለይተው በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ለዚህ ግብረ
ሰዶማዊነት የተጋለጡ ሆነዋል፡፡ በእነዚህ ከፍተኛ ትምህርት ቤት የሚገኙ ልጃገረዶች ገንዘብን ሽተው ወይም
ዘመናዊነት መስሎአቸው ግብረሰዶምን ስለሚፈጽሙ ወይም ተታለው ስለሚፈጸምባቸው ብዙዎቹ በኤች አይ
ቪ ኤድስ ሳያውቁት የተያዙ ሆነዋል ፡፡ ወደው
የሚፈጽሙት አንስት ከዚህ በሽታና ከእርግዝና እናመልጣለን፣ ጎን ለጎንም
ጠቀም ያለ ገንዘብ እናገኛለን ብለው ነው፡፡
ነገር ግን ከአንዱ ቢያመልጡ ከአንዱ አላመለጡም፡፡ ሁላችን እንንቃ ሁሉን ነገር
በንቃት እንጠባበቅ ሃይማኖቻችንን እንማር እንኑርበትም፡፡ ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁ ከዚህ እጅግ
ሰቅጣችና አስነዋሪ ድርጊት እንዲጠበቁ ስለጉዳዩ ጎጂነት ሃይማኖታችሁ የሚያስተምረውን በግልጥ ንገሩዋቸው ፡፡ ሃይማኖትንና በጎ አድራጎትን
ታከው ወደ እናንተ የሚቀርቡትን ምዕራባዊያንንና በጎ አድራጎት
እናደርጋለን የሚሉትን መርምሮአቸው ከተቻለ ራቁዋቸው ፡፡ እንጠንቀቅ ከዚህ አስነዋሪና
አሳፋሪ ነገር እራሳችንን እንጠብቅ፣ በአሁኑ ጊዜ ስለኢትዮጵያ
ሕዝብ የሚቆረቆር የለምና፡፡
ለጥንቃቄ
ጠቢቡ ሰሎሞን በመክብቡ “እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ አስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘለዓለማዊነትን በልቡ ሰጠው” ብሎአል ፡፡መክ.3፡11
በእርግጥ ይህ የሚደንቅ እውነት ነው ፡፡ የሰውን ገጽታ ሲመለከቱት ዘለዓለማዊነት ስለሚነበብበት ይህ ምድራዊ ሞት እንኳ ሳይቀር የማይነካው ይመስለናልና እንሳሳታልን ፡፡
The true Love
Love is the true
way which our beloved Lord Jesus Christ walk on. it is sense but knowable.
inside it all lows are there. LOVE LOVE AND AGAIN LOVE BE OUR WAY. God created
humanbeings in the desty particles of LOVE. so the basic necessity of
humanbeings become LOVE.
Don’t worry women
Jews accounted the
woman after child birth polluted; and whosoever comes from the bed; it is said
" is not clean" . Those things are not polluted which arise from
nature, but which arise from Choice" (St. Chrysostom, Homilies on Hebrew
Page 516)
Faith without love
is nothing
Faith without love
and hope become nothing. Love and hope are revealed by doing. Like St. John
said "if anyone has material possessions and sees his brother in need but
has not pity on his, how can the love of God be in him? Dear children, let us
not love with words or tongue but with actions and in truth." (1john
3:17-18)
Faith needs a
generous and vigorous soul, and one rising above all things of sense, and
passing beyond the weakness of human reasoning’s. For it is not possible to
become a believer, otherwise than by raising one’s self above the common customs
of the world.(St. John Chrysostom)
No comments:
Post a Comment