ትርጉም ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
(ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ)
30/02/2005
ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብን በተመለከተ እንዲህ ብሎ ጽፎልናል፡፡ “ከመንፈሳዊ እውቀት በላይ እጅግ አስደሳችና ጠቃሚ የሆነ እውቀት ምን አለ? እውቀት ለአንድ ለባዊት ነፍስ ብርሃኑዋ ነው፡፡ የእውቀት ተቃራኒ
የሆነው አላዋቂነት ደግሞ በጨለማ ይመሰላል፡፡ የብርሃን አለመኖር ጨለማን እንዲያመጣ እንዲሁ የእውቀት ጉድለት ድንቁርናን ያመጣል፡፡
ስለዚህም አላዋቂነት ለእንስሳት እንጂ ለሰው ልጅ አይደለም፡፡ አንድ በተፈጥሮ የማወቅና የማገናዘብ ችሎታ የተሰጠው ፍጥረት ከእውቀት
የራቀ ከሆነ ቁጥሩ ከእንስሳት ይሆናል፡፡ እውቀት ስል ግን እውነተኛውን እውቀት ማለቴ ነው፡፡ እውነተኛ እውቀትን የምናገኘው ከራሱ
ከእግዚአብሔር ወይም እርሱ ካለመኖር ወደመኖር ካመጣቸው ፍጥረታት ነው፡፡ ሀሰተኛ እውቀት የሚባለው ግን በሥነፍጥረቱ ለእኛ ያልተሰጠ
ወይም ጨርሶ ካልተፈጠረ ነገር የሚመነጨውን እውቀት ነው፡፡ እርሱ ሐሰተኛ እውቀት ይባላል፡፡
በዚህ ምድር ነፍስ ከሥጋ ተነጥላ መኖር አይቻላትም ሥጋችንን ለብሳት
ትኖራለች እንጂ፡፡ ለነፍሳች ደግሞ እንደ ዓይን የሚያገለግላትና እግዚአብሔር ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ የፈጠራቸውን ፍጥረታትን
የምትመረምርበትና የምታገናዝብበት አእምሮ አላት፡፡ ይህ አእምሮ እውቀትን ተቀባይ እንጂ በራሱ ፍጹም አዋቂ ሆኖ አልተፈጠረም፤ በዚህም
ምክንያት ለሰው አስተማሪና መንገድ መሪ አስፈለገው፡፡
እውነተኛውን እውቀት የምናገኘው ደግሞ ሀሰት ከሌለበት ፍጥረታትን ካለመኖር
ወደመኖር ካመጣቸው ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ነው፡፡ እውነትና ጥበብ የተባለው እርሱ ነው፡፡ የእውቀት መዛግብት
ሁሉ በእርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ የአብ ጥበቡና ኃይሉ የሆነውን ክርስቶስን እንስማው፡፡ እውነተኛውን እውቀት
ከእርሱ ዘንድ እንማር፡፡ በማስተዋልና ከልባችን ሆነን ሥጋዊ አስተሳሰባችንን ከእኛ በማራቅ በትጋት መጻሕፍትን እንመርምር፡፡
በእኛ ውስጥ ያለው ብርሃን ማለትም አእምሮአችን ጨለማ ከሆነ፡፡ የዚህ
ዓለም ገዢ ሆነው በእኛ ላይ እንዴት አይበረታ!!! ስለዚህም በፍጹም ነፍሳችንና በፍጹም ማስተዋል ሆነን መጻሕፍትን ለመመርመር እንቅረብ፡፡
የነገሮችን ምንነት ለመረዳት ዐይናችንን ገልጠን በአትኩሮት መመልከት እንደሚገባን እንዲሁ፡፡ መጻሕፍትን ስናነብ በፍጹም ማስተዋል
ሊሆን ይገባል፡፡
ወደ ሰርጉ አዳራሽ በር በመድረሳችን ብቻ ሁሉን እንዳገኘን ቆጥረን
አንዘናጋ፡፡ ነገር ግን የሰርግ ቤቱን በር ደጋግመን እናንኳኳው እንዲህ ያደረግን እንደሆነ የሰርግ ቤቱ በር ተከፍቶልን የውስጡን
ውበት ማየት እንችላለን፡፡ በሩ ቃሉ ነው የሰርግ ቤቱም በቃሎቹ ውስጥ ተሰውረው ያሉት ውብ የሆኑ ሰማያዊ እውነታዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ
ደጋግመን እናንኳኳ አንዴ ወይም ሁለቴ አይደለም ደጋግመን ደጋግመን እናንኳኳ፡፡ ደጋግመን በማንኳኳታችን ሰማያዊው ጀድ ተከፍቶልን
በውስጡ በሚሰጡን ሀብታት ደስተኞች እንሆናለን፡፡ ስለዚህም እንሻ፣
እፈልግ፣ እንመርምር፣ እንጠይቅ፡፡ እርሱንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ለምኑ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ መዝጊያውን አንኳኩ
ይከፈትላችሁማል፡፡ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል”በማለት
አስተምሮናልና፡፡(ማቴ7፡7-8)
በሌላ ቦታ “አባትህን ጠይቅ ያስታውቁህማል ሽማግሌዎችንም ጠይቅ ይነግሩህማል” እንዲል መጽሐፍ እኛም ያልተረዳነውን በእውቀትና በመንፈሳዊው ልምምድ የቀደሙንን መምህራንን እንጠይቃቸው፡፡ እንዲሁም የቅዱሳን አባቶችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱትን ትንታኔአቸውን እንመልከት፡፡(ዘዳግ.32፡7... ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” ብሎ እንዳስተማረው መጻሕፍትን ሁሉ እንመርምር፡፡ የሚጠቅመንን እንያዝ፡፡ በመንፈስም ወደ ሰርጉ ቤት ገብተን ደስ ይበለን፡፡ አሜን ይሁንልን ይደረግልን፡፡
በሌላ ቦታ “አባትህን ጠይቅ ያስታውቁህማል ሽማግሌዎችንም ጠይቅ ይነግሩህማል” እንዲል መጽሐፍ እኛም ያልተረዳነውን በእውቀትና በመንፈሳዊው ልምምድ የቀደሙንን መምህራንን እንጠይቃቸው፡፡ እንዲሁም የቅዱሳን አባቶችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱትን ትንታኔአቸውን እንመልከት፡፡(ዘዳግ.32፡7... ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” ብሎ እንዳስተማረው መጻሕፍትን ሁሉ እንመርምር፡፡ የሚጠቅመንን እንያዝ፡፡ በመንፈስም ወደ ሰርጉ ቤት ገብተን ደስ ይበለን፡፡ አሜን ይሁንልን ይደረግልን፡፡
የኅዳር
ወር የወጣ ፕሮግራም
በዚህ ወር ምንባብ ዘዳግምን፣1ኛና
2ኛ ተሰሎንቄን፣ ማቴዎስን፣አንብበን እንፈጽማለን፡፡ኢያሱን፣ 1ኛና 2ኛ ጢሞቴዎስን፣ ቲቶን፣ሩትን፣ ያዕቆብን፣ ማርቆስን፣1ኛና
2ጴጥሮስን፣ መሳፍንትን፣ዕብራውያንን አንብበን እናጠቃልላን፡፡ ኢሳይያስንና ሉቃስን እንጀምራለን፡፡
የጠዋት ምንባብ
|
||||
ቀን
|
መዝ.ዳዊት
|
ከብሉይ ኪዳን
|
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
|
ከወንጌል
|
1
|
መዝ.1-4
|
ዘዳ.16
|
1 ተሰ.2
|
ማቴ.10
|
2
|
መዝ.9-10
|
ዘዳ.18፡1-12
|
1 ተሰ.4፡1-12
|
ማቴ.12፡1-8
|
3
|
መዝ.15-17
|
ዘዳ.19፡109
|
1 ተሰ.5፡1-10
|
ማቴ.12፡22-37
|
4
|
መዝ.19-20
|
ዘዳ.20
|
2ተሰ.1
|
ማቴ.13፡1-30
|
5
|
መዝ.23-25
|
ዘዳ.22
|
2ተሰ.3
|
ማቴ.14
|
6
|
መዝ.30-31
|
ኢሳ.11፡1-16
|
ራእ.12፡7-12
|
ማቴ.2፡13-23
|
7
|
መዝ.34-35
|
ዘዳ.26
|
1ጢሞ.3
|
ማቴ.16
|
8
|
መዝ.38-39
|
ዘዳ.28
|
1ጢሞ.5
|
ማቴ.18
|
9
|
መዝ.42-44
|
ዘዳ.30
|
2ጢሞ.1
|
ማቴ.19፡16-30
|
10
|
መዝ.47-49
|
ዘዳ.32
|
2ጢሞ.3
|
ማቴ.20፡20-34
|
11
|
መዝ.53-55
|
ዘዳ.34
|
ቲቶ.1
|
ማቴ.21፡33-46
|
12
|
መዝ.59-60
|
ዘፍ.32፡
|
ራእ.12፡7-12
|
ማቴ.18፡1-10
|
13
|
መዝ.64-66
|
ኢያ.3
|
ፊልሞ.1
|
ማቴ.24፡1-35
|
14
|
መዝ.69-70
|
ኢያ.5
|
ዕብ.2
|
ማቴ.25፡1-30
|
15
|
መዝ.73-74
|
ኢያ.6፡15-27
|
ዕብ.3፡12-19
|
ማቴ.26፡1-29
|
16
|
መዝ.78
|
ኢያ.8
|
ዕብ.5
|
ማቴ.26፡47-75
|
17
|
መዝ.80-82
|
ኢያ.10
|
ዕብ.7
|
ማቴ.28
|
18
|
መዝ.86-88
|
መሳ.1
|
ዕብ.9
|
ማር.2
|
19
|
መዝ.90-92
|
መሳ.4
|
ዕብ.10፡19-32
|
ማር.4
|
20
|
መዝ.96-98
|
መሳ.6
|
ዕብ.11፡17-40
|
ማር.6
|
21
|
መዝ.103-104
|
መሳ.8
|
ዕብ.13፡17-25
|
ማር.8
|
22
|
መዝ.106
|
መሳ.10፤11
|
ያዕ.2
|
ማር.9፡33-50
|
23
|
መዝ.108-110
|
መሳ.14፤15
|
ያዕ.4
|
ማር.11
|
24
|
መዝ.116-118
|
መሳ.17፤18
|
1ጴጥ.1፡1-12
|
ማር.13
|
25
|
መዝ.119፡57-120
|
መሳ.20
|
1ጴጥ.2
|
ማር.15
|
26
|
መዝ.120-124
|
ሩት.1
|
1ጴጥ.4፡1-11
|
ሉቃ.1፡1-38
|
27
|
መዝ.129-132
|
ሩት.4
|
1ጴጥ.5
|
ሉቃ.2
|
28
|
መዝ.136-137
|
ኢሳ.2
|
2ጴጥ.2
|
ሉቃ.4
|
29
|
መዝ.140-142
|
ኢሳ.4
|
1ዮሐ.1
|
ሉቃ.6
|
30
|
መዝ.145-147
|
ኢሳ.6
|
1ዮሐ.3
|
ሉቃ.8
|
የማታ ምንባብ
|
||||
ቀን
|
መዝ.ዳዊት
|
ከብሉይ ኪዳን
|
ከመጻሕፍተ ሐዲሳት
|
ከወንጌል
|
1
|
መዝ.5-8
|
ዘዳ.17
|
1 ተሰ.3
|
ማቴ.11
|
2
|
መዝ.11-14
|
ዘዳ.18፡13-22
|
1 ተሰ.4፡13-18
|
ማቴ.12፡9-21
|
3
|
መዝ.18
|
ዘዳ.19፡10-21
|
1 ተሰ.5፡11-28
|
ማቴ.12፡38-50
|
4
|
መዝ.21-22
|
ዘዳ.21
|
2ተሰ.2
|
ማቴ.13፡31-58
|
5
|
መዝ.26-29
|
ዘዳ.24
|
1ጢሞ.1
|
ማቴ.15፡1-20
|
6
|
መዝ.32-35
|
ዘዳ.25
|
1ጢሞ.2
|
ማቴ.15፡21-39
|
7
|
መዝ.36-37
|
ዘዳ.27
|
1ጢሞ.4
|
ማቴ.17
|
8
|
መዝ.40-41
|
ዘዳ.29
|
1ጢሞ.6
|
ማቴ.19፡1-15
|
9
|
መዝ.45-46
|
ዘዳ.31
|
2ጢሞ.2
|
ማቴ.20፡1-19
|
10
|
መዝ.50-52
|
ዘዳ.33
|
2ጢሞ.4
|
ማቴ.21፡1-32
|
11
|
መዝ.56-58
|
ኢያ.1
|
ቲቶ.2
|
ማቴ.22
|
12
|
መዝ.61-63
|
ኢያ.2
|
ቲቶ.3
|
ማቴ.23
|
13
|
መዝ.67-68
|
ኢያ.4
|
ዕብ.1
|
ማቴ.24፡36-51
|
14
|
መዝ.71-72
|
ኢያ.6፡1-14
|
ዕብ.3፡1-11
|
ማቴ.25፡31-46
|
15
|
መዝ.75-77
|
ኢያ.7
|
ዕብ.4
|
ማቴ.26፡30-46
|
16
|
መዝ.79
|
ኢያ.9
|
ዕብ.6
|
ማቴ.27
|
17
|
መዝ.83-85
|
ኢያ.23፤24
|
ዕብ.8
|
ማር.1
|
18
|
መዝ.89
|
መሳ.2፤3
|
ዕብ.10፡1-18
|
ማር.3
|
19
|
መዝ.93-95
|
መሳ.5
|
ዕብ.11፡1-16
|
ማር.5
|
20
|
መዝ.99-102
|
መሳ.7
|
ዕብ.13፡1-17
|
ማር.7
|
21
|
መዝ.105
|
መሳ.9
|
ያዕ.1
|
ማር.9፡1-32
|
22
|
መዝ.107
|
መሳ.12፤ 13
|
ያዕ.3
|
ማር.10
|
23
|
መዝ.111-115
|
መሳ.16
|
ያዕ.5
|
ማር.12
|
24
|
መዝ.119፡1-56
|
መሳ.19
|
1ጴጥ.1፡13-25
|
ማር.14
|
25
|
መዝ.119፡121-176
|
መሳ.21
|
1ጴጥ.3
|
ማር.16
|
26
|
መዝ.125-125
|
ሩት.2፤3
|
1ጴጥ.4፡12-25
|
ሉቃ.1፡39-80
|
27
|
መዝ.133-135
|
ኢሳ.1
|
2ጴጥ.1
|
ሉቃ.3
|
28
|
መዝ.138-139
|
ኢሳ.3
|
2ጴጥ.3
|
ሉቃ.5
|
29
|
መዝ.143-144
|
ኢሳ.5
|
1ዮሐ.2
|
ሉቃ.7
|
30
|
መዝ.148-150
|
ኢሳ.7
|
1ዮሐ.4
|
ሉቃ.9
|
እውነተኛውን እውቀት የምናገኘው ደግሞ ሀሰት ከሌለበት ፍጥረታትን ካለመኖር ወደመኖር ካመጣቸው ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ነው፡፡ እውነትና ጥበብ የተባለው እርሱ ነው፡፡ የእውቀት መዛግብት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ የአብ ጥበቡና ኃይሉ የሆነውን ክርስቶስን እንስማው፡፡ እውነተኛውን እውቀት ከእርሱ ዘንድ እንማር፡፡ በማስተዋልና ከልባችን ሆነን ሥጋዊ አስተሳሰባችንን ከእኛ በማራቅ በትጋት መጻሕፍትን እንመርምር፡፡
ReplyDelete