ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
19/08/2006
ቅዱስ ኤፍሬም ዘኬዎስ ጌታን ሲቀበል የነበረውን ምናባዊ በሆነ መንገድ
እንዲህ ብሎ ጽፎልናል፡፡ በነገራችን
ላይ እንዲህ ዓይነት ስዕላዊ አጻጻፍ ስልት የሴማዊያን የአጻጻፍ ስልት ነው፡፡
ዘኬዎስ በልቡ“ ይህን ጻድቅ ሰው በእንግድነት በቤቱ የተቀበለ ሰው ብፁዕ ነው” ብሎ በልቡ ጸለየ፡፡ ልብ ያሰበውን ኩላሊት
ያመላለሰውን የሚያውቅ ጌታ ደግሞ የልቡን ጸሎት ሰምቶ “ዘኬዎስ ሆይ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ” አለው፡፡
ዘኬዎስም በልቡ ሲያመላልስ የነበረውን ጌታ እንዳወቀበት ተረድቶ “ይህ ያሰብሁትን ያወቀ የሠራሁትንስ ሁሉ እንዴት አያውቅ? በማለት
ለጌታችን መልሶ “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ ብሆን ዐራት እጥፍ እመልሳለሁ” አለ፡፡
ጌታውም “ፈጥነህ ውረድ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ብሎ መለሰለት፡፡” በኋለኛው የበለስ ተክል ምክንያት በአዳም በለስ ምክንያት
የሚታወሰው በለስ ተረሣ፡፡ ዘኬዎስ በበደሉ ምክንያት “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች አሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ ብሆን
ዐራት እጥፍ እመልሳለሁ” በማለቱ ለዚህ ቤት መዳን ሆነለት፡፡
ተቃዋሚዎች በዚህ ሰው እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ይደነቁ፡፡
አስቀድሞ ሌባ የነበረ አሁን ግን መጽዋቾች ሆነ አስቀድሞ ቀራጭ የነበረ ዛሬ ግን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ ዘኬዎስ ቅን የሆነውን
ሕግ ወደ ኋላ ትቶ ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ላለመስማቱ ምልክት ወደሆነችው ወደማትሰማውና ወደማትለማው ዛፍ ተወጣጣ፡፡
ነገር ግን የእርሱ መዳን በዛፉ ላይ ከመውጣቱ ጋር የተገናኘ ነበረ፡፡ ከታች ከምድር በመለየት ወደ ላይ ከፍ ከፍ በማለት በከፍታ የሚኖረውን መለኮትን ለመረዳት በቃ፡፡ ጌታም ደንቆሮ ከሆነችው የበለስ ዛፍ ፈጥኖ እንዲወርድ አዘዘው ይህ በምሳሌ ይከተለው ከነበረው የጥፋት መስመር ፈጥኖ እንዲመለስ ስለመጠየቁ የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅን ከሆነች ሕግ ወጥቶ ደንቁሮ ሆኖ ይኖር ዘንድ ስላልፈቀደ ነው፡፡ ጌታም የቀድሞውን የጥፋት መንገድ እንዲተው ፍቅሩ በእርሱ ላይ እንዲቀጣጠልበት አደረገ ለዚህም ምክንያቱ በፍቅሩ አዲሱን ሰው ሆኖ ዳግም እንዲፈጠር ለማድረግ ነው፡፡ ዘኬዎስም ሌላ አዲስ ልደት እንዳለ ይረዳ ዘንድ ጌታችን “እርሱ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ በዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” ብሎ የምስራችን ዜና ለዘኬዎስ አበሰረው፡፡ ጌታ ሆይ መተላለፋችንን ይቅር በል፡፡ ፍቅርህ እኛን ይለውጠን፤ በፍቅርህም ከኃጢአት መንገድ እንድንወጣ አርዳን ፍቅርህን በእኛ ልቡና እንደ ዘኬዎስ አቀጣጥለው ያኔ ከኃጢአት ለፈቃድህ በመትጋት መራቅ ይቻለናል፡፡ ጌታ ሆይ እባክህ እርዳን፡፡

Amen kale hiewot yasemalen.
ReplyDeleteጥሩ ትምህርት ነው ግን..ዘኬዎስ ቅን የሆነውን ሕግ ወደ ኋላ ትቶ? የሚለውን ኣልተረዳሁህም
ReplyDeleteብታብራራልኝ ኣመሰግናለሁ።
Deleteብታብራራልኝ ኣመሰግናለሁ።
Deleteቅን የሆነው ሕግ የተባለው እርሱ ለሙሴ የተሰጠችው ሕግ ነው።
Deleteቅን የሆነው ሕግ ያለው በእርሱ የተሰጠችውን ሕጉን ነው።
ReplyDelete