በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
10/04/2012
ወገኖቼ
ሞትን ማሰብ ደጉ እንዴት መረጋጋትን የሚሰጥ እሳቤን ይሰጠናል መሰላችሁ፡፡ ሞት ደጉን ስታስቡ በዚህ ዓለም የዘመን ቀመር ነገሮችን መቀመር ታቆሙና ነገሮችን በዘለዓለማዊው ዘመን ቀመር ይህም ትናንት ያይደለ ነገም ያልሆነ ለዘለዓለም አሁን ሆኖ በሚኖር
ፀሐይ በማትወጣበትና በማትጠልቅበት በአምላክ ጊዜ ውስጥ ሆኖ አሁን አእምሮአችንን ሰቅዘው የያዙትን በሐሳብም፣ በቃልም፣ በተግባርም
ያሉ ነገሮችን የምንመዝነበት ስለሆነ ሞት ደጉን አመስግኑት፡፡ እርሱን ማሰብ ባይኖር ኖሮ መች አምላክን መፍራት፣ ማፍቀር፣ መናፈቅ
የዚህን ዓለም መከራ መዘንጋት መታገሥ እንዴት ገንዘብ እናደርጋቸው ነበር? ሞት ማሰብ ደጉ ሁሉን የሚያስተካክል፣ ትሑቱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ፣
በትዕቢት የታጀረውን ማንም ሳያሰገድደው የሚያዋርድ፣ ባለሥልጣንንና ጦረኛን የሚያርድ ደፋሩን ፊሪ የሚያደርግ እንደ ሞትን ማሰብ ከቶ ምን አለ? ሞትን ማሰብ
በስውር በሚያይ አምላክ ፊት በቅድስና ለመኖር አንቀጽ፣ የእውነተኛ ትሕትና እናት፣ የእውነተኛ ጸሎት መፍለቂያ ምንጭ ነው፡፡ ለዚህች መገኛ የገነት አምሳልነና በሯ ጾም ናት፡፡ አቤቱ አምላካችን ሆይ ሁሌም ቢሆን በፊትህ መሆናችንን እንድናስብ እርዳን፤
በሞት ወደ አንተ በጠራኸን ጊዜ እንዳናፍር በአንተ ዘንድ በጎ የሆኑትን ከማሰብ እስከ መፈጸም አብቃን፤ ወደ አንተም ስትጠራን “ኑዑ
ኀቤየ ቡርካኑ ለአቡየ" ብለህ ተቀበለን፡፡
Kale hiwote Ya'semalen Memehere. Memeher, I was need your book called "Ene'huwat Kiristna", but I could not get it in the market. And How could i get it.
ReplyDeleteThank you in advance
you can get it Amist Killo Birana Metsihaf Medebir
DeleteYes, i have found it at this book store; thank you very much.
ReplyDelete