ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
27/05/2004
ይህ ጽሑፍ የደማስቆው ቅዱስ ዮሐንስ የአይሁድን የሰንበት አከባበር በመቃወም ከጻፈው ጽሑፍ የተመለሰ ነው፡፡
በአይሁድ ሰባተኛዋ ቀን ሰንበት ትባላለች እኛ ደግሞ ቀዳሚት ሰንበት እንላታለን፡፡ ትርጉሙም ዕረፍት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ እንዲል እግዚአብሔር በዚህች ቀን ከሥራው ሁሉ ዐርፎባታልና፡፡(ዘፍ.2፡2)ከዚህም የተነሣ ቀናት ሲቆጠሩ እስከ ሰባት ቀን ተቆጥረው ካበቁ በኋላ እንደገና አንድ ተብለው ይቆጠራሉ፡፡ ሰባተኛዋ ዕለት በአይሁድ ዘንድ ልዩ ስፍራ አላት፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰባተኛዋን ቀን ትከበር ዘንድ አዞአቸው ነበርና፡፡ ይህ ሕግ እንዳው ያለምክንያት የተሰጣቸው ሕግ አልነበረም፡፡ስለአይሁድ አመፅ የተሠራላቸው ሕግ ነው እንጂ፡፡ ይህን የመጻሕፍትን ምሥጢር መለየት ሀብቱ የተሰጣቸው መምህራን ይረዱታል፡፡

በሰሚዎቹ ዘንድ ያልተለመደ ነገር ግን ጠቃሚ የሆነ ሕይወትን ለማለማመድ ከተፈለገ ቀላል በሆነ ልምምድ መጀመር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እስራኤላውያን ሥጋውያንና ለምድራዊ
ብልጥግና ብቻ የሚተጉ እንዲሁም ከመንፈሳዊ እውቀት የራቁ እንደሆኑ ሲረዳ አስቀድሞ “ሰባተኛው ቀን ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ…
ሎሌህም ገረድህም በሬህም አህያህም ከብትህም ሁሉ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፡፡”ብሎ ትእዛዝን ሰጣቸው፡፡