Monday, July 9, 2012

መካከለኛ(አማላጅ) ለሚለው ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ፡፡


በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
1/11/2004
እንደ ወረደ አቅርቤዋለሁ ያንብቡትና የራሶን አስተያየት ያኑሩበት

"What is the role of your priest (pastor)? What is the job of him? Why do you want him led you to Christ your Lord? is that the bible said "እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን"? (2ቆሮ.5:20) Christ our Lord is the Good shepherd. But He gave the power of shepherd to Apostles.(Mtt.18:18, John.21:15-19 and 20:19 ) apostles also gave the power of shepherd to their followers.(Act.20:28) they sat the rule how ordain the bishops, priest and deacons.(1Tim.3:1-13) if they didn't play the mediator role, what is the necessity of these all ordinations? Is it not biblical?

ስለስብከት ወተግሣጽ መጽሐፌ በመጠኑ


ከዚህ መጽሐፍ የተቀነጨቡ

መግቢያ

ኤፍሬም አጭር የሕይወት ታሪክ

ቅዱስ ኤፍሬም በሦስተኛው ክፍለ ዘመን በመጀመሪያዎቹ ሰባት አሥርተ ዓመታት ውስጥ የኖረ የሥነ መለኮት ሊቅ ፣ የዜማ ደራሲ ፣ ባለቅኔ ፣ ሰባኪ ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ተርጓሚ የሆነ ጻድቅ አባት ሲሆን ፣ በጊዜው በሮም መንግሥት ሥር በነበረችው በሶርያ ንጽቢን 1 በምትባለው ታላቅ ከተማ ከክርስቲያን ቤተሰብ  በ፪፻፺፱ ዓ. ም ተወለደ ፡፡
በዘመኑ ሊቀ ጳጳስ በሆነው በቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን 2፣ ባደገባት ከተማ ፣ የዲቁና ማዕረግ ተሹሞ በከተማዋ በምትገኝ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን ሆነ ፡፡



Saturday, July 7, 2012

የቤተ ክርስቲያንን ለቤተ ክርስቲያን የገዳምን ለገዳማውያን



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
29/10/2004
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ …ትወደኛለህን? ብሎ ከጠየቀውና እርሱም አዎን ብሎ ከመለሰ በኋላ “... ግልገሎቼን አሰማራ…ጠቦቶቼን ጠብቅ … በጎቼን አሰማራ” ብሎ መንጋውን እንዲጠብቅ አደራ እንደሰጠው እናውቃልን፡፡(ዮሐ.19፡15-17)ይህ ሓላፊነት ምንም እንኳ ለእርሱ ይነገረው እንጂ ለሐዋርያት ሁሉ የተሰጠ ሓላፊነት ነበር፡፡ እነርሱም የክርስቶስን መንጋ ከሥጋና ከመንፈስ ርሃብ ጠብቀው የድርሻቸውን ተወጥተው አልፈዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕጻናት፣ ወጣቶችና አረጋዊያን በአንድነት የሚኖሩባት፣ በምድር ያለች ግን ሰማያዊት፤ ቅዱሳን መላእክት፣ ቅዱሳን ነፍሳትና በምድር ያለነው በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር በሞቱ ለዚህ ዓለም ኃጢአት የሞትን፤ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠን ሕይወት ሕያዋን የሆንንና በትንሣኤ ሕይወት የምንመላለስ የምንኖርባት፤ ጌታችን መድኀኒታችን የሚገዛትና የሚመራት ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለች ዘለዓለማዊት መንግሥት ናት፡፡ ገዳም ግን መነኩሳት በፈቃድ የብሕትውናን ሕይወት መርጠው የሚኖሩባትና ለእነርሱ ብቻ የምትስማማ ሆና ሥርዐት የተበጀላት መንፈሳዊት ሥፍራ ናት፡፡