የጌታችን ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)፣ ለቃል ድምፁ
የሆነው ዮሐንስ መጥምቅ፡- “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” በማለት የቅድስት ድንግል እናታችን ምሳሌ በሆነች በንስሐ ማኅፀን ተወልደን “መንግሥተ ሰማያት” ወደ ተባለች የጌታ አካሉ እንገባ ዘንድ ሰበከን፡፡ ለጌታ ድምፁ የሆንኽ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ለአንተ በጊዜው ያልተፈጸመልህን ለእኛ የሰበክውን ይህን ድንቅ ዜና ይዘህ ስለመጣኽልን ፍጹም ደስ አለን፡፡ ይልቁኑ የኃጢአት ሥርየትን የመስጠት ስልጣን ያለው እርሱ ጌታችን “መንግሥተ ሰማያት ወደሆነች ሰውነቴ በጥምቀቴ ባርኬ በሰጠኋችሁ ጥምቀት ከጎኔ በፈሰሰው ውኃ ነጽታችሁ ከጎኔም የፈሰሰውን ደሜን ተቀብላችሁ በጦር በተዋጋው ጎኔ ሽንቁር ዓለማችሁ ወደ ሆነው ወደዚህ መለኮታዊ አካሌ ግቡ እያለ ሰበከን፡፡ Labels
- ለቤተ መጻሕፍቶዎ (2)
- ምልከታዎቼ (45)
- ቅንጭብጭብ (22)
- ተግሣጻትና ጸሎታት (26)
- ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች (78)
- ከቅዱሳን አባቶች ማዕድ (41)
- ኪን መንፈሳዊ (20)
- የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ከንባቡ ለወጡ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች (6)
Thursday, December 5, 2019
ተዋሕዶ ይቺ ናት
የጌታችን ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)፣ ለቃል ድምፁ
የሆነው ዮሐንስ መጥምቅ፡- “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” በማለት የቅድስት ድንግል እናታችን ምሳሌ በሆነች በንስሐ ማኅፀን ተወልደን “መንግሥተ ሰማያት” ወደ ተባለች የጌታ አካሉ እንገባ ዘንድ ሰበከን፡፡ ለጌታ ድምፁ የሆንኽ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ለአንተ በጊዜው ያልተፈጸመልህን ለእኛ የሰበክውን ይህን ድንቅ ዜና ይዘህ ስለመጣኽልን ፍጹም ደስ አለን፡፡ ይልቁኑ የኃጢአት ሥርየትን የመስጠት ስልጣን ያለው እርሱ ጌታችን “መንግሥተ ሰማያት ወደሆነች ሰውነቴ በጥምቀቴ ባርኬ በሰጠኋችሁ ጥምቀት ከጎኔ በፈሰሰው ውኃ ነጽታችሁ ከጎኔም የፈሰሰውን ደሜን ተቀብላችሁ በጦር በተዋጋው ጎኔ ሽንቁር ዓለማችሁ ወደ ሆነው ወደዚህ መለኮታዊ አካሌ ግቡ እያለ ሰበከን፡፡
Labels:
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች
Monday, February 25, 2019
ጸሎት በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትርጓሜ
በመ/ር ሽመልስ መርጊያ
18/06/2011 ዓ.ም
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እኔስ ቅዱሳን ብላቸው እመርጣለሁ በአንድነት የተስማሙባት አንዲት ደግ ትርጉም አለች
እርሷንም በሕሊናዬ ሳደንቃት ሳወጣ ሳወርድ አረፈድኩ፡፡ እርሷም ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ናት
የምትለዋ ትርጓሜ ናት፡፡ እሊህ ሊቃውንት በአንድ ድምፅ ጸሎት ማለት ልመና፣ ምልጃ ወይም ምስጋና ማለት ነው ብለው
አልተረጎሙልንም ነገር ግን ጻድቁ አብርሃም አምላኩን ሥላሴን በእንግድነት ተቀብሎ ያነጋገረውን ንግግር ዓይነት፣ ሎጥ
ወንድሙንና ቤተሰቡን እንዲያድንለት ከአምላኩ ጋር የተነጋገረውን መነጋገር ዓይነት፣ ያዕቆብ በጵንኤል ከአምላኩ ጋር
ታግሎ ካልባረከኝ አልለቅህም ያለውን ዓይነት መነጋገር፣ ሙሴ በደብረ ሲና ተራራ ላይ ዐራባ ቀንና ሌሊት ከፈጣሪው
ጋር የተነጋገረበትን ዓይነት እና ክብርህን አሳየኝና እርሱ ይበቃኛል ብሎ የተነጋገረውን መነጋገር ዓይነት፣ ኤልያስ
እና ኤልሳዕ ከአምላካቸው ጋር የተነጋገሩበትን መነጋገር ዓይነት፣ ነቢያት ሁሉ ከአምላክ ጋር የተነጋገሩትን
መነጋገር ዓይነት ናት አሉን ወዳጆቼ፡፡
Labels:
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች
Friday, February 22, 2019
ተዋሕዶ ኅትመት
መ/ር ሽመልስ መርጊያ
ቀን 14/06/2011 ዓ.ም
አምላክ በሕይወት ካቆየኝ አንድ በጎ እና ለቤተ ክርስቲያን ቅናቱ ያለው
ሰው ይህን ሐሳብ ከግብ ሊያደርሰው ይችላል ብዬ በማመን ይህን ሕልሜን ለአንባቢያን ላከፍለው ወደድሁ
ስያሜ፡- ተዋሕዶ ኅትመት
የስያሜው ምክንያት፡- ተዋሕዶ ማለት በሁለት አካላት መካከል የተደረገ ፍጹም የሆነ አንድነትን
የሚገልጽ ቃል ሲሆን አንዱ አካል እና የአካሉ ባሕርይ የሌላኛውን አካልና ባሕርይ ሳያጠፋ፣ ሳይመጥ፣ ሳይቀይር፣ ሳይቀይጥ፣ ሳይለውጥ
ነገር ግን አንዱ አካል ሌላኛውን አካል የራሱ አካልና ባሕርይ በማድረግ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን የሚገለጡበትን ምሥጢር
ለማስረዳት ቤተ ክርስቲያናችን በብቸኝነት የምትጠቀምበት ቃል ነው፡፡ ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሰው ሆኖ በመወለድ
የገለጠው ምሥጢር ነው፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ከአብ ጋር በመተካከል ሲኖር ሳለ ሰውን ለማዳን ሲል ከቅድስት ድንግል ማርያም
በጽንሰት ሥርዓት ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ በመንሳት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ በአንድ አካልና በአንድ ባሕርይ ለፍጥረት
ሁሉ ተገልጦአል፡፡ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ሰው የመሆን ምሥጢር ቤተ ክርስቲያናችን ተዋሕዶ ትለዋለች፡፡ ይህንንም ቃል የራሷ መገለጫ
ስም አድርጋም ትጠቀምበታለች፡፡ ይህንንም መጠሪያ ስሟ አድርጋ በመጠቀሟም ከሌሎች የክርስትና የእምነት ተቋማት ሁሉ ትለያለች፡፡
ስለዚህ ተዋሕዶ ስንል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ማለት እንደሆነ ማንም በቀላሉ ይገነዘበዋል፡፡ ለዚህም ነው ወደፊት እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንዲመሠረት ለምፈልገው የሕትመት ተቋም
ተዋሕዶ ኅትመት የሚል ስያሜ መስጠቴ፡፡
Labels:
ምልከታዎቼ
Subscribe to:
Posts (Atom)