Wednesday, December 11, 2019

ዳርዊን ቲዎሪውን ከየት አገኘው ?


በመ/ር ሽመልስ መርጊያ
ቀነን 01/04/2012


ወገኖቼ አንድ ነገር ልብ ብላችሁ አድምጡኝ፡፡ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ዳርዊን እርሱ የጻፈው ግልበጣ(ኩረጃ የራስ አስመስሎ ማቅረብ) መሆኑን ያስተዋለው ሰው ማን ነው? ከየት ብትሉኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ ገልብጦ ብላችሁ ምን ትሉኛላችሁ? ግን እርሱ እግዚአብሔር በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረውን የሰው ልጅ ገልብጦ ዝንጀሮ አድርጎ ሴኩላር ቀለም ቀባው፡፡ እስቲ አስተውሉ፤ አዳምን የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሔዋንን የዐሥራ አምስት ዓመት ኮረዳ አድርጎ የፈጠረ አምላክ ምድርና በውስጧ ያሉትን የቢልዮን ዓመታት ዕድሜ እንዲኖራቸው አድርጎ መፍጠር ይሳነዋል ብላችሁ ታስባላችሁን? እናም ወዳጆቼ ይህን ሐሳብ ከየት ስቦ እንዳመጣው ተገንዘቡ እርሱ መነኩሴ ነበር ማለት ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጠንቅቆ ያውቃል ማለት ነው፡፡

Thursday, December 5, 2019

ተዋሕዶ ይቺ ናት


ተዛማጅ ምስልየጌታችን ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)፣ ለቃል ድምፁ የሆነው ዮሐንስ መጥምቅ፡- “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” በማለት የቅድስት ድንግል እናታችን ምሳሌ በሆነች በንስሐ ማኅፀን ተወልደን “መንግሥተ ሰማያት” ወደ ተባለች የጌታ አካሉ እንገባ ዘንድ ሰበከን፡፡ ለጌታ ድምፁ የሆንኽ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ለአንተ በጊዜው ያልተፈጸመልህን ለእኛ የሰበክውን ይህን ድንቅ ዜና ይዘህ ስለመጣኽልን ፍጹም ደስ አለን፡፡ ይልቁኑ የኃጢአት ሥርየትን የመስጠት ስልጣን ያለው እርሱ ጌታችን “መንግሥተ ሰማያት ወደሆነች ሰውነቴ በጥምቀቴ ባርኬ በሰጠኋችሁ ጥምቀት ከጎኔ በፈሰሰው ውኃ ነጽታችሁ ከጎኔም የፈሰሰውን ደሜን ተቀብላችሁ በጦር በተዋጋው ጎኔ ሽንቁር ዓለማችሁ ወደ ሆነው ወደዚህ መለኮታዊ አካሌ ግቡ እያለ ሰበከን፡፡ 

Monday, February 25, 2019

ጸሎት በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትርጓሜ

በመ/ር ሽመልስ መርጊያ
18/06/2011 ዓ.ም  
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እኔስ ቅዱሳን ብላቸው እመርጣለሁ በአንድነት የተስማሙባት አንዲት ደግ ትርጉም አለች እርሷንም በሕሊናዬ ሳደንቃት ሳወጣ ሳወርድ አረፈድኩ፡፡ እርሷም ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ናት የምትለዋ ትርጓሜ ናት፡፡ እሊህ ሊቃውንት በአንድ ድምፅ ጸሎት ማለት ልመና፣ ምልጃ ወይም ምስጋና ማለት ነው ብለው አልተረጎሙልንም ነገር ግን ጻድቁ አብርሃም አምላኩን ሥላሴን በእንግድነት ተቀብሎ ያነጋገረውን ንግግር ዓይነት፣ ሎጥ ወንድሙንና ቤተሰቡን እንዲያድንለት ከአምላኩ ጋር የተነጋገረውን መነጋገር ዓይነት፣ ያዕቆብ በጵንኤል ከአምላኩ ጋር ታግሎ ካልባረከኝ አልለቅህም ያለውን ዓይነት መነጋገር፣ ሙሴ በደብረ ሲና ተራራ ላይ ዐራባ ቀንና ሌሊት ከፈጣሪው ጋር የተነጋገረበትን ዓይነት እና ክብርህን አሳየኝና እርሱ ይበቃኛል ብሎ የተነጋገረውን መነጋገር ዓይነት፣ ኤልያስ እና ኤልሳዕ ከአምላካቸው ጋር የተነጋገሩበትን መነጋገር ዓይነት፣ ነቢያት ሁሉ ከአምላክ ጋር የተነጋገሩትን መነጋገር ዓይነት ናት አሉን ወዳጆቼ፡፡