Friday, July 10, 2015

ክርስቶስ የማይታየው አምላክ ምሳሌ የመባሉ ምክንያት



በዲ/ን   ሽመልስ መርጊያ
3/10/2007
ሕዝቅኤል እግዚአብሔር ለእርሱ እንዴት እንደተገለጠለት ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር "በራሳቸውም ላይ ካለው ጠፈር በላይ ድምፅ ተሰማ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።  በራሳቸውም በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ። ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ አየሁ፤ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት ምስያ አየሁ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ። በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደ ቀስተ ደመና አምሳያ፥ እንዲሁ በዙሪያው ያለ ፀዳል አምሳያ ነበረ። የእግዚአብሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። ባየሁም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ፥ የሚናገርንም ድምፅ ሰማሁ።"(ሕዝ.1:26-28)

Monday, July 6, 2015

የዘፍ.1፡1-4 ልዩ ምልከታ



በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ 
29/10/2007

ተወዳጆች ሆይ ሌላም ግሩም የሆነውን በቅዱሳን አባቶች ዘንድ ያለውን ትርጓሜ  ልንገራችሁ፡፡ አባቶች ዘፍ.1፡1-4 ያለው ነቢዩ ሙሴ  ስለክርስትና በምሥጢር የተናገረባት ነው ብለው ይተረጉሙታል፡፡ “ቀንም ሆነ ሌሊትም ሆነ አንድ ቀን” የሚለውም ስምንተኛዋ ቀን ናት ይሏታል፡፡ ይህቺ ቀን ፀሐይና ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት ለምድር ብርሃንን ከመስጠታቸው በፊት የነበረች ቀን ነች፡፡
በእርግጥ እንዲህ ሲሉ አንዳች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ሳይዙ አይደለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይለናል “ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ ፡- በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና” (2ቆሮ.4፡6፤ዘፍ.1፡3) ይለናል።

Tuesday, May 5, 2015

ወገኖቼ አንድ እውነት ልንገራችሁ



ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

27/08/2007

 እውነቱም ይህ ነው፡- ደስታና እረፍት አይደለም በምድራዊ ሕይወታችን ውስጥ ይቅርና በመንፈሳዊው ምልልሳችን እንኳ ሁሌ የምናገኘው አይደለም፡፡ በምድር የምናጣጥማቸው ደስታና እረፍት መገኛቸው ከእግዚአብሔር ስጦታዎች እንጂ ከሌላ ከምንም አናገኛቸውም። ቢሆንም እነዚህ የሚታወኩበት ጊዜ ስለሚመጣ ያኔ ደስታህና እረፍትህ ለጊዜውም ቢሆን ሊወሰዱብህ ይችላሉ፡፡ እንዲህም ቢሆን ተፈጥሮውያኑ የእግዚአብሔር ስጦታዎች እየተጤኑ ካልሆኑ በቀር ከወይኒ ቤትም በላይ የከፉ የስቃይ እስር ቤት ሊሆኑብህ ይችላሉ፡፡
ስለዚህ ወገኔ በእነዚህ የእግዚአብሔር ስጦታዎች ሙሉ ለሙሉ ባይሆን እንኳ የደስታህና የእረፍትህ እርሾ ከአንተ ፈጽሞ እንዳይወሰድ ከፈለግህ አስቀድመህ ይሉንታን ከራስህ አርቅ ፡፡ ይሉንታ የደስታንና የእረፍትን እርሾ ፈጽሞ ከሰውነትህ የሚያስወግድና በምትኩ የማይጠፋ የቁጭት ፍም አኑሮ የሚያልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ወዳጄ ሕሊናህ የሚልህን ስማው ፤ ሕሊና የአንተን ደስታና እረፍት ጠንቅቆ የሚያውቅና የቁጭት ፍምን ከአንተ የሚያርቅ መለኪያህ ነው፡፡
 ወዳጄ እንደ ምሳሌ እናንሣ ብንል እንኳ ተፈጥሮአውያን ስጦታዎች ከሆኑት መካከል አንዱና ዋነኛው ፆታዊ ፍቅር ነው።
  ወገኔ ሆይ ትዳር መልካም ነው፤ ነገር ግን ለትዳር ጓደኝነት ከውጫዊ ቁሳቁሶች በፊት ፍቅርን አስቀድም፡፡ ከዚያ በኋላ በትዳርህ ደስታና እረፍትን ታገኛለህ፡፡