Labels
- ለቤተ መጻሕፍቶዎ (2)
- ምልከታዎቼ (45)
- ቅንጭብጭብ (22)
- ተግሣጻትና ጸሎታት (26)
- ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች (78)
- ከቅዱሳን አባቶች ማዕድ (41)
- ኪን መንፈሳዊ (20)
- የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ከንባቡ ለወጡ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች (6)
Tuesday, July 31, 2012
St. Epherm said about us
25/11/2004
Labels:
ቅንጭብጭብ
Saturday, July 28, 2012
“ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት አይሁን”(በቅዱስ ኤፍሬም)የመጨረሻ ክፍል
ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
22/11/2004 ዓ.ም
ጌታችን “በሰገነት ላይ ያለ ወደ ኋላ አይመለስ”(ሉቃ.17፡31) በሚለው
ኃይለ ቃሉ በእነርሱ ላይ ቁጣው ምንም የነደደ ቢሆንም የእነርሱን ጥፋት
እንደማይወድ ያሳየበት ኃይለ ቃል ነው፡፡ “በዚያችም ወራት ለርጉዞች ለሚያጠቡ ወዮላቸው”(ማቴ.24፡19) ሲልም በጊዜው
ስለፀነሱት ሴቶች ልጆቻቸው እየተናገረ ሳይሆን በሮማዊያን ጭንቅ የሆነ መከራን ትቀበላላችሁ ሲላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም “ችግር
በምድር ላይ በዚህም ሕዝብ ላይ ይሆናል”(ሉቃ.21፡23)ብሎ ተናገረ፡፡ በዚህም ምክንያት “ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን
ጸልዩ” በማለት ከዚህ መከራ እንዲድኑ ጌታችን አስጠነቀቃቸው፡፡ እንዲህም ሲል የጽድቅን ሥራ የማትሠሩባት ቀን ትመጣለች፡፡ በዚያች ዕለት መብራታችሁን ከዘይታችሁ
ጋር ሳትይዙ እንዳትገኙ፤ ይህም ማለት ፍቅርን ከምጽዋትና ከንጽሕና ጋር ወይም እምነትን ከምግባር ጋር ሳትይዙ እንዳትገኙ ተጠንቀቁ
በዚያች በመጨረሻዋ ሰዓት ለመብራታችን ዘይት እንፈልግ በማለት ያም ማለት የትሩፋት ሥራዎችን እንሥራ ብትሉ አይቻላችሁም፤ ምክንያቱም
ጊዜው የሥራ ሳይሆን የፍርድ ጊዜ ነውና፡፡(ማቴ.25፡1-13) ስለዚህም ጽድቅን ሳትሠሩ ጊዜው ፈጥኖ እንዳይደርስባችሁና እንዳይፈረድባችሁ
በጸሎት ትጉ ሲል “ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ” አላቸው፡፡ በክረምት ፍሬ እንደሌለ በሰንበትም ሥራ
የለም፡፡ ስለዚህም ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት አይሁን ሲል እምነትንና ምግባርን ሳትይዙ ድንገት ምጽአቱ እንዳይደርስባችሁ
በጸሎት ትጉ ሲል ነው፡፡
Labels:
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች
“ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት አይሁን”(ትርጉም በቅዱስ ኤፍሬም)
ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
21/11/2004 ዓ.ም
ተወዳጆች ሆይ ዛሬ ጌታችን “እንግዲህ
በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል”(ማቴ.24፡15) የሚለውን ኃይለ ቃል ትርጉም እንማማራለን፡፡ እንደሚታወቀው ኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ
ጠፍታ በተደጋጋሚ መልሳ የተገነባች ከተማ ናት፡፡ ነገር ግን ይህ
የትንቢት ቃል በኢየሩሳሌም የአምልኮው ሥርዐቱና በሌዋውያን ካህናት የሚቀርበው መሥዋዕት ፈጽሞ እንደሚቋረጥ የሚያስረዳ ኃይለ ቃል
ነው፡፡ አስቀድሞ በነቢዩ ዳንኤል “የጥፋት ርኩሰት” የተባለውን አንዳንድ ተርጓሚያን “ሮማውያን በቤተመቅደሱ እሪያ በመሠዋት ጭንቅላቱን ይዘው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ
እንደሚገቡና መቅደሱን እንደሚያረክሱት፤ ይህ በተፈጸመ ጊዜ የኢየሩሳሌም ጥፋት እንደቀረበ አንባቢው ያስተውል ሲል ነው ብለው ይተረጉሙታል፡፡(ፍጻሜው
ግን ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ አምላክ ከተባለው ሁሉ
ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው” ብሎ የተናገረለት የሐሳዊው መሲህ መገለጥ ነው፡፡(2ተሰ.1፡4)
Labels:
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች
Thursday, July 26, 2012
Christian philosophy on women and men interaction.
By Shimelis Mergia
19/11/2004
The spiritual understanding has a
power to adjust the ideologies of secular thoughts. Those how are guading in natural law live like animals. Spiritual understanding for them foolihness. But
we Christian can see above this. Our undertanding is above natural laws. We understand any thing in the help of Holy Spirit who is the creator of all created beings. so our thinking can shape the secular thoughts which are focused on the natural law
only.
Women have more tendencies to spiritual things than men. Beside others, they want to learn spiritual things from men. Unless otherwise, if men are not learn them piritual things beside others, they may hate them suggesting as one of the fornicetors who desiring their flesh.
Their eyes looking from down to top but we men are looking from to down.
Or they pull us down to earthily things; we also pull up them to heavenly things. This is natural law. Then both of us become in medium. That is the correct place of human beings. Human being is mediator, to visible and invisible creation.
Women have more tendencies to spiritual things than men. Beside others, they want to learn spiritual things from men. Unless otherwise, if men are not learn them piritual things beside others, they may hate them suggesting as one of the fornicetors who desiring their flesh.
Their eyes looking from down to top but we men are looking from to down.
Or they pull us down to earthily things; we also pull up them to heavenly things. This is natural law. Then both of us become in medium. That is the correct place of human beings. Human being is mediator, to visible and invisible creation.
Do you see the gravity which planted
by God in our nature? Anybody cannot be escaped from the gravity of earth, until he
stops to live on earth. Such like things; we couldn’t escape from the gravity of that God planted inside our nature until we live on earth. We men and women are
pulling each other to live in the medium life.
Labels:
ቅንጭብጭብ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እስቲ ልጠይቅህ!
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
19/11/2004
ዛሬ የጌታችንንና የአፍቃሪያችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክና ግርማ ለብሶ በብሉይ ኪዳን ለቅዱሳን
መጽናናትን ይሰጥ የነበረውና(ዳን.10፡5-5 ከ ራእይ.1፡14-16 ካለው ጋር ያነጻጽሩ፤ እንዲሁም ሕዝ. 1፡26 ከ ዳን.8፡15፤9፡21፤10፡18 እንዲሁም 3፡25 ያነጻጽሩ)በሐዲስ ኪዳንም የድኅነት ብሥራትን ይዞ ወንድሞቻችንን መላእክትን ወክሎ እንዲሁም ነፍስን በደስታ በምታስጨንቅ ፍስሐ ተሞልቶ፣(ሉቃ፡15፡10) ወደ ድንግል በመምጣት ሕዝቡን ከኃጢአት የሚያድናቸው የስሙ ትርጓሜ መድኀኒት የሆነውን "ኢየሱስን በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽ"(ሉቃ፡1፡31) ብሎ ያበሠረ የተወዳጁ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ
በዓል ነው፡፡
ሰውና አምላክ ፍጹም እርቅን የፈጸሙባትን ያቺን ዕለት ሳስባት ነፍሴ በሐሴት ትሰክራለች፡፡ ልጅ ከእናትና ከአባት ጥምረት ይወለዳል ፡፡ ስለዚህ ልጅ የእናትና የአባት ውሕደት
አማናዊ መገለጫ ነው፡፡ እንዲሁ እግዚአብሔር አብ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ሊገልጥልን ስለወደደ ልጁን እግዚአብሔር ወልድን ከድንግል በሥጋ ይወለድ ዘንድ ላከው፡፡ ልጁም ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ በመወለድ ፍጹም እርቅ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል መፈጸሙን በልደቱ አበሠረን፡፡
ከአባት አብራክና ከእናት መኀፀን የተወለደን
ልጅ አካፍሎ ወደፊት ለአባትና ለእናት መስጠት እንዳይሞከር እንዲሁ እግዚአብሔር ወልድ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደ በኋላ አምላክ ወሰብእ ተብሎ ይኖራል እንጂ ወደፊት ተከፍሎ የለበትም፡፡
Labels:
ቅንጭብጭብ
Sunday, July 22, 2012
ሰው ማለት ምን ማለት ነው?
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
15/11/2004
(ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር የተለቀቀ)
(ከዚህ በፊት በማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር የተለቀቀ)
Labels:
ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች
Saturday, July 21, 2012
ለፍቅር መምህር የሆነ ፍቅር እና ወዳጄ ሆይ .....
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
14/11/2004
Labels:
ቅንጭብጭብ
Monday, July 9, 2012
መካከለኛ(አማላጅ) ለሚለው ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ፡፡
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
1/11/2004
እንደ ወረደ አቅርቤዋለሁ ያንብቡትና የራሶን አስተያየት ያኑሩበት
"What
is the role of your priest (pastor)? What is the job of him? Why do you want him led you to Christ your Lord? is that the bible said "እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን"? (2ቆሮ.5:20)
Christ our Lord is the Good shepherd. But He gave the power of shepherd to
Apostles.(Mtt.18:18, John.21:15-19 and 20:19 ) apostles also gave the power of shepherd
to their followers.(Act.20:28) they sat the rule how ordain the bishops,
priest and deacons.(1Tim.3:1-13) if they didn't play the mediator role, what is
the necessity of these all ordinations? Is it not biblical?
Labels:
ቅንጭብጭብ
ስለስብከት ወተግሣጽ መጽሐፌ በመጠኑ
መግቢያ
ኤፍሬም አጭር የሕይወት ታሪክ
ቅዱስ ኤፍሬም በሦስተኛው ክፍለ ዘመን በመጀመሪያዎቹ ሰባት
አሥርተ ዓመታት ውስጥ የኖረ የሥነ መለኮት ሊቅ ፣ የዜማ ደራሲ ፣ ባለቅኔ ፣ ሰባኪ ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ተርጓሚ የሆነ ጻድቅ
አባት ሲሆን ፣ በጊዜው በሮም መንግሥት ሥር በነበረችው በሶርያ ንጽቢን 1 በምትባለው ታላቅ ከተማ ከክርስቲያን ቤተሰብ በ፪፻፺፱
ዓ. ም ተወለደ ፡፡
በዘመኑ ሊቀ ጳጳስ በሆነው በቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን 2፣ ባደገባት ከተማ ፣ የዲቁና ማዕረግ ተሹሞ በከተማዋ በምትገኝ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን ሆነ ፡፡
Labels:
ለቤተ መጻሕፍቶዎ
Saturday, July 7, 2012
የቤተ ክርስቲያንን ለቤተ ክርስቲያን የገዳምን ለገዳማውያን
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
29/10/2004
Labels:
ቅንጭብጭብ
Wednesday, July 4, 2012
ዳግማዊቱ አዳም
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
28/10/2004
ክርስቲያኖች ሆይ ኑ ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር መንፈሳዊ ቅኔን እንቀኝ፡፡ እርሱ ስለቅድስት ድንግል ማርያም እንዲህ ይላል “አዳም ለሔዋን እናትም አባትም እንደነበር እንዲሁ
ቅድስት ድንግል ማርያም ለልጁዋ ለወዳጁዋ እናትም አባቱም ሆነች፡፡” ከዚህ ተነስተን አዳም የሚለው መጠሪያ ለድንግልም የሚያገለግል እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ስለዚህ አዳም ስንል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማለታችን እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ አዳም ስንል ቅድስት ድንግል ማርያም
ማለታችንም ነው፡፡በእርግጥ ጥንትም አዳም የሚለው መጠሪያ ስም ለወንዱ ብቻ የሚያገለግል መጠሪያ ሰም አልነበረም “እግዚአብሔር
አዳምን በፈጠረበት ቀን ወንድና ሴት አድረጎ ፈጠራቸው ባረካቸውም፡፡ ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው” ይላልና፡፡(ዘፍ.5፡2)
እነሆ አዳም የሚለው መጠሪያ ስም ለሴቶችም እንደሆነ እንረዳ ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ አዳም ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እናትም አባትም ሆና አሳደገችው፡፡
ይህ ምሥጢር ሌላም እውነታን በውስጡ አዝሎ ይዟል፡፡ እርሱም፡- በክርስቶስ አምነን የእርሱ የአካሉ ሕዋሳት ለሆነውና በእርሱ አካል ለምንገለጠው ክርስቲያኖችም( ሮሜ.12፡5) ቅድስት ድንግል ማርያም እናትም አባትም መሆኑዋን እንረዳለን፡፡ ኦ ጌታችን
ሆይ!!! ይህ እንዴት ድንቅ የሆነ ምሥጢር ነው!!!
Labels:
ቅንጭብጭብ
Tuesday, July 3, 2012
ስለድንግል ምልጃ ከመነገሩ በፊት የሚቀድመው ቁም ነገር!!!
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
27/10/2004
ቅድስት ድንግል ማርያም ነጻ ፈቃዷን
ተጠቅማ “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ” በማለት ለመዳናችን ምክንያት የሆነችን እናት ናት፡፡ እርሱዋ በአንደበቱዋ “ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል
መንፈሴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ሃሴትን ታደርጋለች” ብላ እንደገለጠችልን ሥጋዋን ብቻ ሳይሆን ነፍሱዋንና ሕሊናዋን ለጌታ ማደሪያ በማድረግ ለእኛ ክርስቲያኖች አብነት የሆነች የመጀመሪያይቱ ክርስቲያንና አማናዊቱ ቤተክርስቲያን ናት፡፡
እኛም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን
በሥጋችን ቤተ መቅደስ፤ ሕጉንና ፈቃዱን እንዲሁም መንፈሱን በነፍሳችንና በሕሊናችን ማኅደር በማሳደር እርሱዋን እንመስላታለን፡፡
ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ስለእርሱዋና ስለእኛ በአንድነት ሲናገር“እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ
አጭቻችኋለሁ”አለን(2ቆሮ.12፡2)
Labels:
ምልከታዎቼ
ጸሎት ዘአረጋዊ ዮሐንስ
ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
27/10/2004
“ከእኔ የተሰወርክና የተሸሸግህ ጌታዬ ሆይ! አንተነትህን ግለጥልኝ ፡፡ ከእኔ ውስጥ
ያለውን ያንተን ውበት አሳየኝ ፡፡ ሰውነቴ ለአንተ ማደሪያ ቤተ መቅደስ ይሆን ዘንድ የሠራኸው ጌታዬ ሆይ! (፩ቆሮ.፫፥፲፮-፲፯፤፪ቆሮ.፮፥፲፮)የክብርህ ደመና ቤተ መቅደስህ የሆነውን ሰውነቴን ይክደነው፤ የመሠዊያህም አገልጋይ የሆነችው ነፍሴ በፍቅር በመሆን አንተን ቅዱስ
እያሉ በአድንቆትና በአግርሞት፣ በፍጹም ትጋትና ቅድስና እንደሚያገለግሉህ ሕያዋንና መንፈሳውያን ኃይላት ታመሰግንህ ዘንድ እርዳት፡፡…
የይቅርታ ውቅያኖስ የሆንክ
ክርስቶስ ሆይ! ካንተ የሆነውን ብርሃናዊ ልብስ ተጎናጽፌ እንዳንጸባርቅ ባንተ ውኃነት በኃጢአት ያደፈውን ሰውነቴን እንዳጥብ
ፍቀድልኝ፡፡ ሕቡዕ በሆኑ ምሥጢራት የተሞላው የክብርህ ደመና(መንፈስ ቅዱስ) እኔን ይከድነኝ ዘንድ (በእኔ ያድር ዘንድ) በዐይኔ ከማላያቸው ጀምሬ ወደ አንተ ውበት
የሚወስዱኝን የጽድቅ ጎዳናዎች አስተውል ዘንድና ባንተ ግርማ ተማርኬ ያለማቋረጥ ክብርህን አደንቅ ዘንድ እንዲሁም በዓለም
ጉዳይ ዐይኖቼ ከመባከን ያርፉ ዘንድ ምንም ቢሆን ምን ከአንተ ፍቅር የሚለየኝ እንዳይኖር ከዚህ ይልቅ አንተን በመናፈቅ
እንድኖር ያለማቋረጥ ፊትህን እመለከት ዘንድ የልቡናዬን ዐይኖች ግለጥልኝ የልቡናዬንም እርሻ አለስልሰው ፡፡”
Labels:
ተግሣጻትና ጸሎታት
Subscribe to:
Posts (Atom)